(ግንቦት 5፣2014 ዓ.ም፣ ባሕር ዳር)፦ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአንገት በላይ ሕክምና ትምህርት ክፍል አሜሪካን ሀገር ከሚገኝ Children’s Surgery International ከተሰኘ ድርጅት ጋር በመተባበር ከግንቦት 5-12፣2014 ዓ.ም የከንፈርና የላንቃ መሰንጠቅ ችግር ያለባቸዉን ሰዎች የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅቱን እንዳጠናቀቀ ማሳወቃችን ይታወሳል፡፡
በመሆኑም ችግሩ ያለባቸሁ ሰዎች ከዛሬ ጀምሮ በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመምጣት የእድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
#Dedicated to #excellence #committed to #care!!!
Follow us on:
(ግንቦት 4፣2014 ፣ባሕር ዳር)፦ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመሰረታዊ የድንገተኛና የጽኑ ሕሙማን ሕክምና አሰጣጥ ዙሪያ ላይ በአዋቂዎች እና በህጸናት ጽኑ ሕሙማን ሕክምና አገልግሎት ክፍሎች ለሚሰሩ ነርሶች ስልጠና እየሰጠ ነዉ።
የስልጠናዉ ዓላማ የነርሶችን ክህሎት ለማዳበር ያለመ ሲሆን በስልጠናዉም ከ24 በላይ ነርሶች እተሳተፉ ይገኛሉ።
ስልጠናዉን እየሰጡ የሚገኙት የድንገተኛና ጽኑ ሕሙማን፣ የሳንባ ጽኑ ሕሙማን እና የሰመመን ጽኑ ሕሙማን ስፔሻሊሰት ሐኪሞች በጋ በመተባበር ነዉ። ስልጠናዉም ለ10 ቀናት የሚቆይ ይሆናል።
(ግንቦት 4፣2014 ዓ.ም፣ ባሕር ዳር)፦በባሕር ዳር ዩንቨርስቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ/ ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የነርሲንግ አሶሴሽን ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት ከኢትዮጵያ ነርሶች ማህበር ጋር በመተባበር አመታዊዉን አለም-አቀፍ የነርሶች ቀን በዛሬው እለት በተለያዩ ዝግጅቶች እያክበረ ይገኛል::
በእለቱ በርካታ ከረጤት ደም ከሆስፒታሉ/ኮሌጁ ማህበረሰብና የሆስፒታሉ ደንብኞች እየተሰበሰበ ሲሆን የደም ግፊት፣ ሙቀት ልኬትና መሰል አገልግሎቶችን በነፃ እየሰጠ ይገኛል::
በአሉን በሆስፒታሉ የሚሰሩ ነርሶችና የኮሌጁ መምህራን ነርሶች በጋራ እያስተባበሩት ይገኛል::
Bahir Dar University
Bahir Dar, Ethiopia
Phone:- +251-0582-9 99275
P.o.box:- 79
e-mail:- collegehealthscience@gmail.com
Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2017- Bahir Dar University