
(መጋቢት 8፣2015 ዓ.ም፣ባሕር ዳር)፦በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የዓይን ሕክምናና ትምሕርት ክፍል Fight Blindness in Ethiopia ከተባለው ግብረሰናይ ድርጅት ጋር በመተባበር ከመጋቢት 17/2015 እስከ መጋቢት 22/2015 ዓ.ም ነፃ የዓይን ምርመራና የሞራ ቀዶ ጥገና አገልግሎት ለባሕር ዳር እና አካባቢዋ ነዋሪዎች ይሰጣል፡፡
የቀዶ ሕክምና አገልግሎቱም በሞራ ግርዶሽ ምክኒያት ለማየት የተቸገሩ ታካሚዎችን እይታ ለመመለስ ያለመ ነዉ።
በዚሁ መሠረት ችግሩ ያለባችሁ ሰዎች ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የዓይን ሕክምና ክፍል በስራ ሰዓት በመገኘት ያለባችሁ ችግር ተለይቶ ወረፋ በመያዝ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ሆስፒታሉ ጥሪ ያቀርባል።
#Dedicated to #excellence #committed to #care!!!
Follow us on:
Facebook: https://www.facebook.com/cmhsbdu?mibextid=ZbWKwL
Website:
bdu.edu.et/cmhs/
Telegram: https://t.me/Information_office_CMHS_BDU
Twitter:
twitter.com/medicine_bdu?t…
LinkedIn:
https://www.linkedin.com/company/college-of-medicine-and-health-sciences...
06/07/2015 ዓ.ም
ድጋሚ የወጣ ማስታወቂያ
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዩኒቨርሲቲው ባወጣው አዲስ የመካከለኛ አመራሮች መመደቢያ መመሪያ መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር (Director, Operations Services) ቦታ መተካት ይፈልጋል፡፡
የማወዳደሪያ መስፈርት
=============
1ኛ. የትምህርት ደረጃ ስፔሻሊስት ሐኪምና ረዳት ፕሮፌሰር እና ከዚያ በላይ ማዕረግ ያለው/ያላት፣
2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በሆስፒታልና መሰል ተቋማት፣ በምርምር ተቋማት በመማር ማስተማር፣ ማኅበረሰብ አገልግሎት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት እርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከተ/ች፣
3ኛ. በሚያመለክቱበት ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የጤና አገልግሎትን ተደራሽነት፣ ፍትሃዊነት፣ ጥራትንና ደኅንነት፣ ተገቢነትና ዓለም አቀፋዊነትን ለማሳካት፣ ኮሌጁንና ሆስፒታሉን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለም አቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ለማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል አጭር ስትራቴጅያዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/የምትችል፣
4ኛ. ከኮሌጁና ሆስፒታሉ የሚሰጠውን ዝርዝር ሃላፊነት በቅንነት በትጋትና በታማኝነት ተቀብሎ የሚፈፅም፣
5ኛ. የኮሌጁ አመራሮች፣ የሆስፒታሉ ማኔጅመንት አባላትና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለፃ መስጠት የሚችል/የምትችል፡፡
አመልካቾች፡- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን (06/07/2015 ዓ.ም) ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት የትምህርትና የሥራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጅያዊ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ዳይሬክተር ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
የመመዝገቢያ ቦታ
==========
ጥበበ ግዮን ካምፓስ
ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
06/07/2015 ዓ.ም
ድጋሜ የወጣ ማስታወቂያ/Vacancy/
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዩኒቨርሲቲው ባወጣው አዲስ የመካከለኛ አመራሮች መመደቢያ መመሪያ መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የእናቶችና ሕጻናት ሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር (Director, MCH Services) ቦታ መተካት ይፈልጋል፡፡
የማወዳደሪያ መስፈርት
=============
1ኛ. የትምህርት ደረጃ ስፔሻሊስት ሀኪምና ረዳት ፕሮፌሰር እና ከዚያ በላይ ማዕረግ ያለው/ያላት፣
2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በሆስፒታልና መሰል ተቋማት፣ በምርምር ተቋማት በመማር ማስተማር፣ ማህበረሰብ አገልግሎት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በልዩ ልዩ ሀላፊነት እርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከተ/ች፣
3ኛ. በሚያመለክቱበት ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የጤና አገልግሎትን ተደራሽነት፣ ፍትሃዊነት፣ ጥራትንና ደህንነት፣ ተገቢነትና ዓለም አቀፋዊነትን ለማሳካት፣ ኮሌጁንና ሆስፒታሉን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለም አቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ለማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል አጭር ስትራቴጅያዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/የምትችል፣
4ኛ. ከኮሌጁና ሆስፒታሉ የሚሰጠውን ዝርዝር ሃላፊነት በቅንነት በትጋትና በታማኝነት ተቀብሎ የሚፈፅም፣
5ኛ. የኮሌጁ አመራሮች፣ የሆስፒታሉ ማኔጅመንት አባላትና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለፃ መስጠት የሚችል/የምትችል፡፡
አመልካቾች፡- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን (06/07/2015 ዓ.ም) ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት የትምህርትና የሥራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጅያዊ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ዳይሬክተር ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
የመመዝገቢያ ቦታ
==========
ጥበበ ግዮን ካምፓስ
ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
Bahir Dar University
Bahir Dar, Ethiopia
Phone:- +251-0582-9 99275
P.o.box:- 79
e-mail:- collegehealthscience@gmail.com
Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2017- Bahir Dar University