All Interested are cordially invited!
Latest News
Geospatial Data & Technology Center (GDTC) of Bahir Dar University in partnership with the Geographic Information Systems Society of Ethiopia offers a three-day hands-on GEE training August 15-17, 2022) for its staff.
This training which runs from August 15 – 17 , 2022 covers the GEE Code Editor, hands-on exercises on change detection, time series analysis, NDVI calculation, land use/ Land cover classification, and accuracy assessment of optical imagery.
Google Earth Engine (GEE) for resource management is becoming one of the most essential tools in the scientific and decision-making community. GEE provides unparalleled access to large-scale data analysis through cloud computing technology without the need for any locally stored data or software.
ቀን፡-04/12/2014ዓ.ም
ማስታወቂያ
ለ ባሕር ዳር ከተማ የታዳጊ እግር ኳስ ፕሮጀክት ማሰልጠኛ ጣቢያዎች
ባህር ዳር
ጉዳዩ፡- የውድድር ተሳትፎ ጥሪ ስለማድረግ፤
እነሆ በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ሁለተኛው ዙር የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የታዳጊ እግር ኳስ ፕሮጀክት ማሰልጠኛ ጣቢያዎች ውድድር ሊጀመር ነው፡፡ ሁለተኛው አመት የታዳጊ ወጣቶች ውድድር ከ 16 አመት በታች የወንድና ከ 17 አመት በታች የሴት ውድድር ብቻ ያካተተ ሲሆን በእነዚህ የእድሜ እርከን የምታሰለጥኑ የስልጠና ጣቢያ አሰልጣኞች ከ 5/12/2014 ዓ/ም እስከ 7/12/2014 ዓ/ም ድረስ ብቻ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ ቢሮ ቁጥር 1 በመምጣት እንድትመዘገቡ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡
ማሳሰቢያ
1. አንድ ማሰልጠኛ ጣቢያ 1 ቡድን ብቻ ያሳትፋል፤
2. የእድሜ ምርመራ ማለፍ ይጠበቅባችዋል ፤
3. ሁሉም ቡድኖች በማሰልጠኛ ጣቢያ ወይም በ ፕሮጀክት ተይዘው እየሰሩ መሆኑን ማረጋገጫ ማቅረብ አለባችው፡፡
ለውሃ አካሚ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጠ
(ሀምሌ 28/2014ዓ.ም፣ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ-BDU) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከዩኒቨርሲቲው ስልጠና ዳይሬክቶሬት ጋር በመተባበር ከ30 በላይ ለሚሆኑ የውሃ አካሚ ባለሙያዎች ለ3 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ በተግባር ላይ የተመሰረተ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ ሙላቱ ጠብቀው እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው ካሁን በፊት ንፁህ የመጠጥ ውሃ ያገኝ የነበረው ከባሕር ዳር ከተማ ውሃ አገልግሎት ነበር፡፡ ከአንድ አመት በፊት የዩኒቨርሲቲውን የስነ-ምድር ት/ቤት መምህራን ጥናት መሰረት በማድረግ ሰባታሚት አካባቢ ከ127 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ አድርጎ ያስገነባውን ውሃ አክሞ ለተጠቃሚው የዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ ጥቅም እንዲውል የሚያስችል የባለሙያዎች ስልጠና እንደሆነ ተገልጿል፡፡
ኃላፊው አክለውም ስልጠናው ከሁሉም ግቢዎች ለተውጣጡ ከ30 በላይ ለሚሆኑ የውሃ አካሚ ባለሙያዎች በተግባር ላይ ተመስርቶ ለ3 ተከታታይ ቀናት ይሰጣል፡፡ ሠልጣኞችም በሰለጠኑበት ሙያ መሰረታዊ ዕውቀት ይዘው ወደ ስራ እንደሚገቡ ይጠበቃል ብለዋል፡፡
ስልጠናውን የሰጡት የባሕር ዳር ከተማ ውሃ አገልግሎት ከፍተኛ የጥራት ባለሙያ አቶ ኃይለእየሱስ ጓዴ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ብዙ ቁጥር ያለው ማህበረሰብን አቅፎ እንደመያዙ እና የራሱን ውሃ ማስተዳደር በመጀመሩ የውሃ አቅርቦቱ ጥራቱን የጠበቀ ይሆን ዘንድ ሙያዊ ድጋፍ ለማድረግ ስልጠናውን ሊሰጡ እንደቻሉ ተናግረዋል፡፡ የሚሰጡትም ስልጠናዎች የውሃ ጥራትን መለካት እና ውሃውን ከብክለት ለመከላከል የሚያስችል ሲሆን ባለድርሻ አካላትም ሆነ ኃላፊዎች ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጡ አሳስበዋል፡፡ የስልጠናውም ዓላማ ብቁ እና ጤናማ የሆነ ማህበረሰብ በዩኒቨርሲቲው ላይ መገንባት ነው፡፡
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ-ባዳዩ-BDU
ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ
Wisdom at the source of Blue Nile
Thank you for Inviting, like, share & visiting BDU page!
ለተጨማሪ መረጃዎች፡-
Telegram ፡- t.me/BDU_ISC_Official
Facebook: - https://www.facebook.com/bduethiopia
YouTube ፡- www.youtube.com/c/BduEduEt
LinkedIn ፡- www.linkedin.com/school/bahir-dar-university
Twitter: - https://twitter.com/bdueduet
Tiktok:- https://vm.tiktok.com/ZMLgRxdfL
website :- www.bdu.edu.et
የኢትዮጵያ ጨርቃጨርቅና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (EiTEX) እና ምህረት ሜዲካል አቅርቦት ግሩፕ በጋራ ለመስራት ተስማሙ
Foe the details click on : https://www.facebook.com/eitex.et/posts/pfbid0oB3UrTFaB6KT8b2eLqo4YRCAwP...
BDU’s alumni, current presidents of local universities
Former graduates of Peda and Poly of the current Bahir Dar University currently serving as presidents of Debre-Markos (Dr.Tafere), Ambo (Dr. Beyissa), Arbaminch (Dr. Damtew), Kotebe Education (Dr. Berhanemeskel), Assosa (Dr. Kemal), Debre-Tabor (Dr. Anegageregn), Adama (Dr. Lemmi), Gondar (Dr. Asrat), Worabe (Dr. Tofiq) and Wollo (Dr. Mengesha) universities having a group photo together with BDU's president Dr. Firew Tegegne along the shore of lake Tana and Peda's auditorium.