Latest News

አዲስ ለሚከፈቱ የሁለተኛ እና የሦስተኛ ዲግሪ የስርዓተ ትምህርት ግምገማ አውደጥናት ተካሄደ
***********************************************************************
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የስነ-ምድር ሳይንስ ትምህርት ቤት በያዝነው 2015 ዓ.ም በሦስተኛ ዲግሪ (PhD) በሃይድሮጂኦሎጂ እና በሁለተኛ ዲግሪ (MSc) በኢኮኖሚክጂኦሎጂ በሚከፍታቸው ትምህርት ክፍሎች ስርዓተ-ትምህርቶችን በማዘጋጀት በሃገራችን የካበተ ልምድ ባላቸው ሙሁራን መስከረም 21/2015 ዓ.ም አስገምግሟል፡፡
በስርዓተ-ትምህርቱ ግምገማ ላይ ንግግር ያደረጉት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የስነ-ምድር ሳይንስ ትምህርት ቤት ዲን ዶ/ር ምንያህል ተፈሪ የፕሮግራሞች መከፈት በአማራ ክልል እና በሀገሪቱ ያለውን የማዕድን ሃብት በውል ለማወቅ በተለይም ደግሞ ከሌሎች ክልሎች አንፃር ሲታይ የአማራ ክልል የከርሰ ምድር ውሃ ክምችትን አስመልክቶ በግልፅ የማይታወቅ እና የጂኦሎጂ ካርታም ያልተሰራለት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ በጣም ወደኋላ የቀረ በመሆኑ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥናቶችን በማድረግ የትምህርት ክፍሎችን መከፈቱ አሁን ላይ በሃገሪቱ በማዕድኑ ዘርፍ የሚታዩ ችግሮችን ለመፍታት እና የሰለጠኑ ባለሙያዎችን ለማፍራት ዘርፈብዙ አበርክቶ እንደሚኖረው ተናግረዋል፡፡
እንደ ዶ/ር ምንያህል ገለፃ ትምህርት ክፍሎች እንዲከፈቱ ከመወሰኑ በፊት በሀገሪቱ ብሎም በክልሉ በማዕድን እና በውሃው ዘርፍ ያለውን የሰለጠነ የሰው ሃይል እንዲሁም ወደፊት የሚያስፈልገውን የስልጣና ፍላጎት የዳሰሳ ጥናት ማድረጋቸውን እና ለዚህም የሚያስፈልጉ የመርጃ መሳሪያዎች እንዲሁም ቤተሙከራዎችን በከፍተኛ ወጭ ማደራጀታቸውን ተናግረው ለትምህርት ክፍሉ መከፈት ጠንካራ ድጋፍ ላደረጉ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
በስርዓተ-ትምህርቱ ግምገማ ላይ ዶ/ር ዝይን እንደገለፁት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የምርምር ዩኒቨርሲቲ ከሆኑት በሀገሪቱ ውስጥ ካሉ ስምንት ተቋማት አንዱ እንደመሆኑ መጠን ከሁሉም በላቀ መልኩ የክልሉን ብሎም የሀገሪቱን ችግር ሊፈቱ የሚችሉ ምርምሮችን ከማድረግ በተጨማሪ በሁሉም ዘርፍ የሰለጠነ የሰው ሃይል ለማፍራት የድህረ ምረቃ ፕሮግረሞችን ማብዛት እና ተደራሽ ማድረግ ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዕለቱ የስነ-ምድር ሳይንስ ትምህርት ቤት በማዕድኑ እና በውሃው ዘርፍ ባለሙያዎችን ለማሰልጠን የስረዓተ -ትምህርት ቀርጾ በሙያው የታወቁ ሙሁራንን በማሳተፍ ግምገማ ባካሄደው አውደጥናት ላይ ጥሩ ተሞክሮችና ግብዓቶች የተገኙበት እንደነበር ተናግረው ወደፊት አዳዲስ ፕሮግራሞች መክፍት ብቻ ሳይሆን ከጠቀሜታቸው አንፃር ጥራታቸውንም መከታተል ተገቢ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
በአውደጥናቱ ላይ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሃይድሮጂኦሎጂ እና የውሃ አስተዳደር ፕሮፌሰር ጤናዓለም አየነው፣ ዶ/ር ደሴ ንዳው፣ ዶ/ር ዋጋሪ ፉሪ እና ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ዶ/ር ተስፋዬ ተገኝተው ስርዓተ-ትምህርቱን ገምግመዋል፡፡
በፈጠራ እና ስራ ፈጣሪዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ጉባኤ ተካሄደ
*************************************************
መስከረም 20/2014 ዓ/ም [ባዳዩ]
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት አስተባባሪነት ፈጠራና ሥራ ፈጣሪዎች ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በባሕር ዳር ከተማ ተካሄደ።
በውይይት መድረኩ ላይ ቁልፍ መልእክት ያስተላለፉት የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር የተከበሩ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል እንደገለጹት መንግስት ዘርፉን የሚመራ ተቋም ከማቋቋም ጀምሮ ፓሊሲ በመቅረጽ እና ማስፈጸሚያ ስትራቴጂዎችን በመንደፍ ፈጠራንና ሥራ ፈጣሪዎችን ለመደገፍ በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል፡፡
በጉባኤው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ በዘርፉ የሰለጠነ የሰው ሃይል በማፍራት፣ በምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት የታገዙ የፈጠራ ሥራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ዶ/ር ፍሬው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በፈጠራ የተካኑ ባለተሰጦዎችን በማሰልጠን እራሳቸውንና አገራቸውን ተወዳዳሪና ተጠቃሚ የሚያደርጉ ዜጎችን እያፈራ መሆኑንም ጨምረው ገልፀዋል፡፡
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ቢምረው ታምራት በበኩላቸው ተማሪዎችን ብቁ ከማድረግ ባሻገር የቢዝነስ ሀሳብ ላላቸው ተማሪዎች የቻልነውን በመደገፋችን ዛሬ ላይ እንዳየናቸው የፈጠራ ስራ ባለቤቶችን በማፍራት ማሳየት ተችሏል ብለዋል፡፡ ይህን ተከትሎ የሚመለከታቸው አካላት ጉዞውን ማሰቀጠል እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት የቢዝነስ ኢንኩቤሽን እና ቴክኖ-ኢንተርፕረነርሺፕ ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር አማረ ካሳው የመካከለኛ እና የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በአዳዲስ የፈጠራና ሥራ ፈጣሪዎች ልዩ ትኩረት ሰጥተው መወያየታቸው ዋና አላማው የስራ ፈጠራ ማዕከላት ለአገር ብልፅግና እና እድገት ያላቸው ሚና ምን ያክል ነው፣ እነዚህን የስራ ፈጠራ ማዕከላት በቋሚነት እንዲደራጁ አስቻይ ሁኔታዎችን በምን መልኩ መፍጠር ይቻላል፤ ከአጋር አካላት ጋር እንዴት መስራት ይቻላል በጋራ ብንሰራ ደግሞ ምን አይነት ውጤት ይመጣል፤ ሴቶችን በስራ ፈጣራ እና በመሪነት ዘርፍ ወደፊት እንዴት ማምጣት ይቻላል፣ ምን ዓይነት ችግር አለ እንዴትስ መፍታት ይቻላል የሚሉ ሀሳቦች ላይ ያለመ ነው ብለዋል፡፡
በፈጠራና ሥራ ፈጣሪዎች ላይ አተኩሮ ለሁለት ቀን በተካሄደው ጉባኤ ላይ የስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ባለሙያዎች፣ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አመራሮችና መምህራን እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ- ባዳዩ-BDU
ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ
Wisdom at the source of Blue Nile
Thank you for visiting, inviting and sharing our Pages!
Thank you for your likes and comments!
ለተጨማሪ መረጃዎች፡-
Telegram ፡- t.me/BDU_ISC_Official
Website: - www.bdu.edu.et
ባህላዊ የሽመና ስራ ቴክኖሎጅ ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥር ተገለፀ
*************************************************************************
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጅ ተቋም መምህር የሆኑት አለማየሁ አሰፋ በባህላዊ የሽመና ቴክኖሎጅ ዘርፍ የተለያዩ የምርምር ስራዎችን መስራት ለበርካታ ዜጎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥር ገልጸዋል፡፡
በባህላዊ የሽመና ቴክኖሎጅ ዘርፍ የተለያዩ የምርምር ስራዎችን በመስራት እና ስራዎቹን በማስተዋወቅ ከፍተኛ ተቀባይነትን ያገኘ ወጣት ተመራማሪ ነዉ መምህር አለማየሁ አሰፋ፡፡ መምህሩ በባህላዊ የሽመና ቴክኖሎጅ በርካታ ግለሰቦችን በማሰልጠን ዉጤታማ ስራ እየሰራ ይገኛል፡፡
የአቶ አለማየሁ በጣም ቀላል እና ምቹ የሆነ የአልባሳት መስሪያ ፕሮጀክት በ2012 ዓ.ም እንደተጀመረ ተናግረዉ፤ በ2013 ዓ.ም በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት እና ቴክኖሎጅ ሽግግር ቢሮ አስተባባሪነት በተዘጋጀ ኤግዚቪሽን ላይ በፕሮጀክቱ የተከናዎኑ አዳዲስ የአልባሳት አሰራሮች ቀርበዉ ጥሩ ተቀባይነት አግኝተዋል ብለዋል፡፡
መምህር አለማየሁ አሰፋ የእጅ ስራ ቴክስታይል ዘርፉ በጣም ቀላል እና ምቹ የሆነ የአልባሳት መስሪያ ቴክኖሎጅን በመፍጠርና ከሌሎች ሀገራት ቴክኖሎጂዉን በማምጣት ከሚያስተምራቸዉ ተማሪዎች ባለፈ ለአካባቢዉ ማህበረሰብ የስራ እድል በመፍጠር ለብዙዎች ተስፋ የሆነ ወጣት መምህርና ተመራማሪ ሲሆን ቴክኖሎጂዉን ለታራሚዎች፣ለአካል ጉዳተኞች፣ለቤት እመቤቶችና ለገዳማዉያን ስልጠና በመስጠት ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል ፡፡
ቴክኖሎጅ ስንል ብዙ ገንዘብ ወይንም ብዙ እዉቀት የሚጠይቁትን ብቻ አይደለም የሚለዉ መምህር አለማየሁ ዋናዉ መታወቅ ያለበት የተሰራዉ ምርምር ወይንም ቴክኖሎጅ ምን ያህል አዋጭ ነዉ ወይም ችግር ፈች ነዉ የሚለዉ መሆን አለበት ሲል ያናገራል፡፡
በቴክኖሎጅዉ በፋብሪካ ሊመረቱ የማይችሉና ከፍተኛ ተቀባይነት ያላቸዉ ሹራቦች፣ ኮፍያዎች፣ የአንገት ልብሶች (ፎጣዎች) እና መጋረጃዎችን በቀላሉ በማምረት ለተጠቃሚዎች ማቅረብ እንደሚቻል ለማወቅ ችለናል፡፡
ቴክኖሎጅዉ በበርካታ የምዕራባዉያንና ኤስያ ሀገሮች እየተሰራበት ያለ ነዉ የሚለዉ መምህር አለማየሁ በሀገራችን ቀደምት የሽመና ጥበብ መኖሩ እና በርካታ ስራ ፈላጊዎች መኖራቸዉ ዘርፉን አዋጭ ያደርገዋል የሚል እምነት አለኝ ብሏል፡፡

ዩኒቨርሲቲው 60ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን አከባበር በተመለከተ ከአጋር አካላት ጋር ተወያየ

*****************************************************************

መስከረም 19/2015 ዓ/ም [ባዳዩ] የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ ዓመት የምስረታ በዓል አከባበርን በተመለከተ ከአጋር አካላት ጋር በዩኒቨርሲቲው ጥበብ ሕንፃ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ውይይት አካሄደ፡፡

የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዘዳንት ዶ/ር እሰይ ከበደ ጥሪውን አክብረው ለመጡ አጋር አካላትና ታዳሚዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈው፤ ለዩኒቨርሲቲው ምስረታ መነሻ የሆኑት የአሁኑ የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (የቀድሞው ፖሊ ቴክኒክ) የዛሬ 60 ዓመት እና የዛሬ 50 ዓመት አካባቢ ደግሞ የፔዳ ጎጂ መምህራን ኮሌጅ መሆናቸውን አስታውሰዋል፡፡

ዶ/ር እሰይ አክለውም ዩኒቨርሲቲው ከጊዜ ወደ ጊዜ ከፍተኛ ለውጥ በማስመዝገብና ለአካባቢው ማህበረሰብም ዘርፈ ብዙ የማህበረሰብ አገልግሎቶችን በመስጠትና ለአገር ውስጥም ሆነ ለውጭ  ዜጎች ነፃ የትምህርት እድል በመስጠት የራሱን ድርሻ እያበረከተ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በተጨማሪም የዩኒቨርሲቲውን 60ኛ ዓመት ለማክበር የተለያዩ ግብረ ኃይሎች መቋቋማቸውን ተናግረው በተደረገው ምልከታ ከ13 በላይ የሚሆኑ የአገር ውስጥ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንቶች የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ምሩቃን መሆናቸው እንደታወቀ ዶ/ር እሰይ ገልፀዋል፡፡

የመክፈቻ ንግግሩን ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ ከተለያዩ ተቋማት ለመጡና ለአገር ሽማግሌዎች እንዲሁም ለመላው ታዳሚ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈው፤  ማህበረሰቡ ለዩኒቨርሲቲው ያለው አመለካከት በአንጻራዊነት ጥሩ ቢሆንም የሚታዩ ክፍተቶችን ለመሙላት ጠንክሮ መስራትን እንደሚጠይቅ ተናግረዋል፡፡

ፕሬዘዳንቱ በማስከተልም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለባሕር ዳር ከተማ በርካታ ተግባራትን በማበርከቱና በአራቱም አቅጣጫዎች አድማሱን በማስፋቱ ባሕር ዳር ከተማ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ያለ አስመስሎታል ብለዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ለአካባቢው ማህበረሰብ ከመደበኛው ተማሪ በእጥፍ የሚበልጥ የኢ- መደበኛ ተማሪ በማስተማር ላይ ያለ ግዙፍ ተቋም መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ፕሬዘዳንቱ አክለውም ባሕር ዳር ከተማ አምራና ተውባ የቱሪስት መስሕብ ትሆን ዘንድ በዩኒቨርሲቲው ምሁራንና በውጭ ባለሙያዎች ርብርብ 100 ሚሊዮን ብር ይፈጅ የነበረውን በ30 ሚሊዮን ብር የከተማዋን መዋቅራዊ ፕላን ሰርቶ የአገር ሽማግሌዎች በተገኙበት ለሚመለከተው አካል ማቅረቡን እንዲሁም በአሁኑ ወቅት 35 ሺህ የ12ኛ ክፍል ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስፈተን ዝግጅቱን ያጠናቀቀ ጠንካራ ተቋም መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ለውይይት መነሻ የሆነውን ፅሁፍ ያቀረቡት የዩኒቨርሲቲው ኢንፎርሜሽንና ስትራቴጅ ኮሚዩኒኬሽን ም/ፕሬዘዳንት ዶ/ር ዘውዱ እምሩ ዩኒቨርሲቲው ከአመሰራረቱ ጀምሮ ያለውን እድገት በወፍ በረር ያቀረቡ ሲሆን የምስረታ በዓሉ መከበር ዓላማዎች፣በዓሉ የሚከበርባቸው መንገዶች እና በበዓሉ አከባበር ላይ የባለድርሻ አካላት ሚና ምን እንደሚመስል አስገንዝበዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው ዋና ዋና እሴቶች ጥራት፣ጥበብን መሻት፣ልሕቀት፣ፈጠራ፣ ማሕበረሰባዊ ኃላፊነት፣ብዝኃነት እና ዓለም አቀፋዊነት እንደሆኑ ብሎም ባሕር ዳር ከተማ የዘንባባ ከተማ ሆና በአፍሪካ ከሚገኙ ተጠቃሽ ጤናማ ከተሞች አንዷ እንድትሆን እንዲሁም የትምህርት ከተማም በመሆን በዩኒስኮ ትመዘገብ ዘንድ ዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አስተዋፅኦ እያበረከተ  መሆኑን ከቀረበው ፅሁፍ ለመረዳት ተችሏል፡፡ 

የውይይቱ ተሳታፊዎች ከተለያዩ ተቋማት የተውጣቱ አጋር አካላት፣ ጥሪ የተደረገላቸው የአገር ሽማግሌዎችና የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ሲሆኑ በዶ/ር ፍሬውና በዶ/ር ዘውዱ አወያይነት ሰፊ ውይይትና ገንቢ አስተያየቶች፤ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ ተሳታፊዎችም የበዓሉ አከባበር ንድፈ ሃሳባና የውይይቱ መድረክ ይበል የሚያሰኝ ተግባር መሆኑን ተናግረው መድረኩን ላዘጋጀው አካል ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ዶ/ር ዘውዱም በውይይቱ ወቅት ለተነሱት ጥያቄዎች ተገቢውን መልስ ሰጥተው ከተሳታፊዎች ለተነሱት ገንቢ አስተያየቶችና ሰፊ ውይይቶች እንዲሁም በዓሉን አብሮ ለማክበር አጋር አካላት ፍቃደኛ በመሆናቸው ምስጋና አቅርበው ዩኒቨርሲቲው በሰራው ልክ እየተዋወቀ እንዳልሆነ የሚያሳምን ጉዳይ ስለሆነ ለወደፊት ተጠናክሮ እንደሚሰራ አስገንዝበዋል፡፡

ፕሬዘዳንቱ በማጠቃለያ ንግግራቸው ዩኒቨርሲቲው በአገሪቱ ካሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በምርምር ዘርፉም ሆነ በበጀት አጠቃቀም  ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቀጥሎ እንደሚገኝ እና 60 ዓመት የሚሞላው ሰኔ 4 ቀን 2015 ዓ.ም እንደሆነ አውስተው የበዓሉ መከበር ዋና ዓላማ ዩኒቨርሲቲው እዚህ ደረጃ እንዲደርስ ጉልህ ፋይዳ ላበረከቱ አካላት እውቅና ለመስጠት እንዲሁም በዚህ እርሾ በመነሳት የወደፊት የትኩረት አቅጣጫዎችን በመንደፍ አሁን ካለበት ደረጃ ልቆ እንዲታይ ታልሞ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ- ባዳዩ-BDU

ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ

Wisdom at the source of Blue Nile

Thank you for visiting, inviting and sharing our Pages!

Thank you for your likes and comments!

ለተጨማሪ መረጃዎች፡-

Telegram ፡- t.me/BDU_ISC_Official

Facebook: - https://www.facebook.com/bduethiopia

YouTube ፡- www.youtube.com/c/BduEduEt

LinkedIn ፡- www.linkedin.com/school/bahir-dar-university

Twitter: - https://twitter.com/bdueduet

Tiktok:-https://vm.tiktok.com/ZMLgRxdfL

Website: - www.bdu.edu.et

Bahir Dar University and the University of Naples L’Orientale sign MoU
26 September 2022, Bahir Dar
Bahir Dar University has signed a memorandum of understanding with the University of Naples L’Orientale (UniOr), Italy. 
Opening the brief signing ceremony of the MoU at the Wisdom Tower, Dr. Manendante Mulugeta, Director of External Relations and Partnership at Bahir Dar University, introduced the  institutional profile of Bahir Dar University and commended the Department of Ge'ez for its contribution to the university’s growing connections especially as a research university.  
Entailing focus areas of student and staff exchange, joint research, program, and platform organization, as well as exchange of scientific materials, the MoU was reported to have involved the Department of Ge'ez and Faculty of Humanities at Bahir Dar University.
Representing UniOr, Professor Gianfrancesco Lusini expressed the partnership between his university and Bahir Dar University as invaluable both in terms of UniOr’s international relations activities and the Ethio-Italy longstanding friendship. 
Dr. Firew Tegegne, President of Bahir Dar University, on his part reminded the assembly of the university’s priority areas and its undertakings towards being a research-intensive university. Dr. Firew also expressed that the partnership would be an additional force in the university’s already ongoing efforts to explore what Ethiopian forefathers have left to today’s generation. 
Professor Lusini also remarked that Ge'ez manuscripts are entangled with the Ethiopian identity and the partnership will enable the new generation of philologists to read, translate, and learn from old Ge'ez manuscripts.
The agreement entered between the two universities will be effective for a period of five years.

Staff at STEM-BDU discuss the performance of the previous academic year and share the major tasks planned for the current academic year.
A team of teachers, directors and admin staff of STEM-BDU went to Gondar town to discuss about the performance of the 2014E.C. academic year. The refreshing retreat to Gondar also aims at beginning the new academic year afresh through sharing the major tasks planned for the current academic year of the center. The Director of the center Dr Tesfa Tegegne presented the performance of the center in 2014 E.C academic calendar. The Director mentioned all the programs and the competitions STEM beneficiary students have participated and the success achieved.
Questions and concerns raised by the teacher participants of the discussion such as students’ disciplinary issues were emphasized in the discussion. Dr Tesfa, the Director and Dr. Alemu Tesfaye,V/Director of the center responded to the questions and highlighted what the center did regarding the issues raised in the meeting They mentioned that some students were penalized trespassing disciplinary protocols. The directors added the center never tolerates very few students who may potentially mar the healthy teaching learning process. It is learnt that the center is producing students who score the highest in the EHEECE (Ethiopian Higher Education Entrance Certificate Examination). The participants said the discussion was critical of the areas of further intervention, informative of what has been done and rejuvenating.
After the discussion, the team paid a visit to STEM center at Gondar University from which the visiting team has appreciated the laboratory setup. As refreshing trip, the retreat took the team to two historical places- The Fasil Castle and the ancient Debrebirhan Holy Trinity Church both situated in the historical Gondar town making their brief stay at Gondar not only fruitful but memorable.

በሰለጠነ ዘመን ላይ ሆነን ጥንታዊና የድህነት በሽታዎችን ተሸክመን ልንጓዝ አይገባም።

https://www.facebook.com/EthiopiaFMoH/posts/pfbid02TwbaQ61NdQGRk1bzuMQNV...

Bahir Dar University College of Medicine and Health Sciences in collaboration with Ministry of Health, and Amhara Regional Health Bureau holds the third National Research Symposium on 'Neglected Tropical Disease in Ethiopia' in Bahir Dar, Ethiopia.

የእድገት በስራ ማህበር ወላጆቻቸውን ላጡ ችግረኛ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

***************************************************************

መስከረም10/2015 ዓ/ም [ባዳዩ] የእድገት በስራ ማህበር በኤች አይ ቪ ኤድስ ወላጆቻቸውን ላጡ 25 ችግረኛ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ፡፡

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከኤች አይ ቪ/ኤድስ ጋር በሚኖሩ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች በተቋቋመው የእድገት በስራ ማህበር  አማካኝነት  በኤች  አይ ቪ ኤድስ ወላጆቻቸውን ላጡ ከ25 በላይ ችግረኛ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡ ድጋፉ የተደረገላቸው የአንደኛ ደረጃ ተማሪዎች ሲሆኑ በድል ችቦ፣ እውቀት ፋና፣ ሹም አቦ፣ መስከረም 16 እና ፈለገ አባይ ትምህርት ቤቶች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ወላጅ አልባ ልጆች እና ችግረኛ ህፃናት ናቸው፡፡ ማህበሩ  ለእያንዳዳቸው  ዘጠኝ ባለ 50 ቅጠል ደብተር እና እስክርቢቶ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን ከአንድ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ይዘው ላጠናቀቁ ተማሪዎች ደግሞ ተጨማሪ ሽልማት አበርክቶላቸዋል፡፡

በድጋፍ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኤች አይ ቪ ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሲ/ር ምህረት ጌታቸው የእድገት በስራ ማህበር ከተመሰረተበት 2006 ዓ.ም ጀምሮ በኤች አይ ቪ ኤድስ ወላጆቻቸውን ላጡ እና ለችግረኛ ሕፃናት ተከታታይ ድጋፎችን ሲያደርጉ መቆየታቸውን ተናግረዋል፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ማህበራቱን ለመደገፍ በተለያዩ ግቢዎች ውስጥ የፎቶ ኮፒ እና የሸቀጣ ሸቀጥ ሱቅ መስሪያ ቦታ በመስጠት እየደገፋቸው መሆኑንም ሲ/ር ምህረት ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኤች አይ ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ዳይሬክቶሬት በተለያዩ ግቢዎች የሚሰሩ መምህራን፣ ሰራተኞችን እና ተማሪዎችን በበጎ ፈቃደኛነት በማሳተፍ በየወሩ ከደምወዛቸው በመቁረጥ በሚያገኘው የገንዘብ ድጋፍ ወላጆቻቸውን በኤች አይ ቪ ኤድስ ላጡ ከ38 በላይ ለሚሆኑ ችግረኛ ተማሪዎች በየወሩ ከ300-500 ብር በቋሚነት ከመርዳቱም በተጨማሪ የደብተር፤ዩኒፎርም እና ቦርሳ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ሲ/ር ምህረት ጌታቸው ተናግረዋል፡፡

እንደ ሲ/ር ምህረት ገለፃ በሃገር አቀፍ ደረጃ ለበሽታው የሚሰጠው ትኩረት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ መምጣቱ በህብረተሰባችን ላይ የሚፈጥረውን ዘርፈ ብዙ ጫና ገልፀው፤ የህብረተሰቡን የግንዛቤ አቅም ከመጨመር አንፃር ተከታታይ የግንዛቤ ፈጠራ ስራዎች መሰራት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ 

 

ብሉ ናይል የውሃ ተቋምና ኢነርጂ ማዕከል በውሃ ዲፕሎማሲና ተግባቦት ላይ ጉባኤ አካሄደ

መስከረም 06/2015 ዓ/ም፤ [ባዳዩ] የብሉ ናይል የውሃ ተቋምና ኢነርጂ ማዕከል ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ካሉት አምስት የልህቀት ማዕከላት አንዱ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የውሃ ዲፕሎማሲና ተግባቦት መማክርት መድረክ (WHDCF) በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበብ አዳራሽ አካሂዷል፡፡

በምክክር መድረኩ ላይ በመገኘት ለተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያቀረቡት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ በአፍሪካ ከሚገኙ ጤናማና ውብ ከተሞች አንዷ ወደ ሆነችዉ እና በዩኔስኮ የትምህርት ከተማ ተብላ ወደተመዘገበችዉ ባሕር ዳር ከተማ እንኳን በሰላም መጣችሁ ብለዋል፡፡

ዶ/ር ፍሬዉ ዩኒቨርሲቲዉ እየሰራቸዉ ካላቸዉ ስራዎች ዋና ዋናዎቹን የገለፁ ሲሆን ከአጋር አካላት ጋር በጋራ በመስራትም ከፍተኛ እምርታ እያሳየ ያለ ዩኒቨርሲቲ ነው ብለዋል፡፡ በዚህም በአሁኑ ሰዓት ዩኒቨርሲቲዉ ወደ 200 ገደማ ከሚሆኑ አጋር አካላት ጋር በጋራ እየሰራ ሲሆን ይህንንም አጠናክሮ ለመቀጠል ተግቶ እንደሚንቀሳቀስ አክለዉ ገልፀዋል፡፡ ለዚህም ጠንካራ ተቋማትና ማዕከላትን በመገንባት ላይ መሆኑን ጠቅሰው  የብሉ ናይል የውሃ ተቋምና የኢነርጂ ማዕከል ዩኒቨርሲቲው ካሉት አምስት የልህቀት ማዕከላት አንዱ እና ጠንካራዉ ተቋም ነዉ ብለዋል፡፡

በምክክር መድረኩ ላይ በመገኘት ለተሳታፊዎች የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢፌዲሪ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ ኢትዮጵያ በምስራቅ አፍሪካ ከሚገኙ ሀገራት በአንፃራዊነት ሰፊ የሚባል የዉሃ ሀብት ያላት ሀገር መሆኗን ገልፀዋል፡፡ ሀገሪቱ 12 ተፋሰሶች እንዳሏት የገለፁት ሚኒስትር ደኤታዉ ከነዚህ ተፋሰሶች 80℅ የሚሆነዉ የዉሃ ሀብታችን የኢትዮጵያን ድንበር አቋርጠዉ  የሚፈስና ከጎረቤት ሀገሮች ጋር የምንጋራቸዉ ናቸዉ ብለዋል፡፡ ድንበር አቋርጠዉ ለሚፈሱ የሀገራችን ዉሃ ሀብቶች ከጎረቤት ሀገሮች ጋር በሚደረጉ የትብብርና የድርድር ተግባራት ላይ የሀገራችንን ጥቅም ለማስከበር በጥንቃቄ እየተሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል፡፡

በምክክር መድረኩ ላይ አምስት ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበዉ በተሳታፊዎች ዉይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ ዉይይቱም በገፅ ለገፅ እና በበይነ መረብ (ኦን ላይን) በቀጥታ ስርጭት የተካሄደ ሲሆን በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የዉሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር አማካሪ አቶ ሞቱማ መቃሳ፣ የተወካዮች ም/ቤት አባልና የታላቁ ህዳሴ ግድብ አምባሳደር የሆኑት የተከበሩ ሙሀመድ አላሩሲ፣ ታዋቂዉ ተመራማሪና የታላቁ ህዳሴ ግድብ ተደራዳሪ ፕሮፌሰር ያዕቆብ አርሳኖን ጨምሮ በርካታ የክብር እንግዶች፣ ምሁራንና የዉሃና የሚዲያ ዘርፍ ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ- ባዳዩ-BDU

ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ

Wisdom at the source of Blue Nile

Thank you for visiting, inviting and sharing our Pages!

Thank you for your likes and comments!

ለተጨማሪ መረጃዎች፡-

Telegram ፡- t.me/BDU_ISC_Official

Facebook: - https://www.facebook.com/bduethiopia

YouTube ፡- www.youtube.com/c/BduEduEt

LinkedIn ፡- www.linkedin.com/school/bahir-dar-university

Twitter: - https://twitter.com/bdueduet

Tiktok:-https://vm.tiktok.com/ZMLgRxdfL

Website: - www.bdu.edu.et

Pages