በባህርዳር ዩንቨርስቲ ሳይንስ ኮሌጅ የበጎ አድራጎት ስራ

በህልውና ዘመቻው ላይ ተሳትፈው ጉዳት ደርሶባቸው በፈለገ ህይወት ሆስፒታል፤በቀበሌ 14 ማገገሚያ ማዕከልና በጥበበ ጊዮን ሆስፒታል በመታከምና በማገገም ላይ ያሉትን የሰራዊት አባላት ለመርዳት በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ሳይንስ ኮሌጅ ማኔጅመንትና የኮሌጁ የህልውና ዘመቻ አስተባባሪ ኮሚቴዎች ባደረጉት ጥረት የተገኘውን 344,000 ብር  የገንዘብ ድጋፍ የአልባሳትና ሌሎች ቁሳቁሶችን ግዢ ተፈፅሞ ለሠራዊቱ አባላት እንዲደርስ የኮሌጁ አካዳሚክ ካውንስልና ከዓብይ ኮሚቴው በሰጠው አቅጣጫ መሠረት ስራዎች ተሰርተዋል፡፡

Subscribe to College of Science RSS