
#ፕሮፌሰር_የሺጌታ_ገላው በአመራር ሰልጣኞቻቸው ሽልማት ተበረከተላቸው።
16 Jun, 2025
ባሕር ዳር ኅዳር 19፣ 2017፦ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር የሺጌታ ገላው በኮሌጁ በሚሰጠው የአመራር ማበልፀጊያ ፕሮግራም ሁለተኛ ዙር ሰልጣኞች ሽልማት ተበረከተላቸው።
ሰልጣኞች ለፕሮፌሰሩ ሽልማቱን ያዘጋጁበት ምክኒያት እርሳቸው ቃልን በተግባር በመኖር የአመራርነት ብቃታቸውን በተግባር ስለቀየሩላቸው እንዲሁም በከፍተኛ ብቃት፣ብስለትና ጥበብ ስልጠናውን በመስጠት የተሻሉ መሪዎች እንዲሆኑ ስላደረጓቸው እንደሆነ ገልፀዋል።
ሰልጣኞች አክለውም ምንም እንኳ ፕሮፌሰሩ እያበረከቱት ላለው ጉልህ አስተዋፅዖ ምንም አይነት ሽልማት በቂ ባይሆንም ያላቸውን አክብሮት ለመግለፅ እንዳዘጋጁት ተናግረዋል።
የሽልማት መርሀግብሩ የተካሄደው የዩኒቨርሲቲያችን ፕሬዝዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ በተገኙበት ሲሆን ስለ አመራር ማበልፀጊያ ፕሮግራሙ እና ለተመራቂዎች ቁልፍ መልዕክት አስተላልፈዋል። ስልጠናቸው በስራ ላይ እንዲገልጥና ቀጣይነት ባለው ለውጥ ውስጥ እራሳቸውን ሁልጊዜ ማሳደግ እንደሚገባ ፕሬዝዳንቱ አስገንዝበዋል።
የዩኒቨርሲቲያችን የአካደሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር እሠይ ከበደን ጨምሮ የኮሌጁ ከፍተኛ አመራሮችና የሰኔት አባላትም ሥነ-ሥርዓቱን ታድመዋል።
#Dedicated to #excellence #committed to #care!!!
Follow us on:
Facebook: https://www.facebook.com/cmhsbdu?mibextid=ZbWKwL
Website:
bdu.edu.et/cmhs/
Telegram: https://t.me/Information_office_CMHS_BDU
Twitter:
twitter.com/medicine_bdu?t…
LinkedIn:
https://www.linkedin.com/company/college-of-medicine-and-health-sciences-bahir-dar-university-ethiopia/