ኮሌጁ በጤናው ዘርፍ ከተሰማሩ የግል ድርጅቶች ጋር በትብብር ለመስራት በሚያስችሉ ሁኔታዎች ዙሪያ ውይይት አካሄደ።

20 Jul, 2025

ሐምሌ 12፣ 2017 ዓ.ም፤ ባሕር ዳር፦  በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ  በጤናው ዘርፍ ከተሰማሩ የግል ድርጂት ተዎካዮች ጋር የማህበረሰቡን ጤና ለመጠበቅና የተሻለ የሕክምና አገልግሎት ለመስጠት በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ሁኔታዎችና የአሰራር ማዕቀፎች ዘሪያ በጥበበ ግዮን ግቢ ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ በተለይም የኩላሊት እጥበት ሕክምና አገልግሎት እና የላቀ የላቦራቶሪ አገልግሎት እንደ የትብብር መነሻ ዘርፎች ትኩረት ተሰጥቶባቸዋል።

በመጨረሻም እንግዶቹ የኮሌጁን የተለያዩ የሥራና የአገልግሎት ክፍሎችን ጎብኝተዋል። ከተጎበኙት መካከልም ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የላቦራቶሪ አገልግሎት ክፍል፣ የጣና የምርምርና ዳይግኖስቲክ ማዕከል የ3ዲ ቴክኖሎጅ ማዕከል እንዲሁም የአማራጭ ሕክምና አገልግሎት የሚጀመርበት ማዕከል ይገኙበታል።

#Dedicated to #excellence #committed to #care!!!

Follow us on:

Facebook: https://www.facebook.com/cmhsbdu?mibextid=ZbWKwL
Website: 
bdu.edu.et/cmhs/
Telegram: https://t.me/Information_office_CMHS_BDU
Twitter:
twitter.com/medicine_bdu?t…
LinkedIn:
https://www.linkedin.com/company/college-of-medicine-and-health-sciences-bahir-dar-university-ethiopia