በባሕር ዳር ዩንቨርሲቲ የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት 924 ተማሪዎችን አስመረቀ [June 27, 2026 | Bahir Dar, ISC/BiT]

Poly Campus

27 Jun, 2026

Event Content

በባሕር ዳር ዩንቨርሲቲ የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት 924 ተማሪዎችን አስመረቀ
[June 27, 2026 | Bahir Dar, ISC/BiT]

***********************************************************************************
ዛሬ በዩንቨርሲቲው በተካሄደው ምርቃት የባህር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በመጀመሪያ ዲግሪ 702 ተማሪዎችን (513 ወንድ እና 189 ሴት) በተለያዩ የምህንድስና እና የኮምፒዩቲንግ ፕሮግራሞች አስመርቋል፡፡ እንዲሁም 206 የሁለተኛ ዲግሪ (168 ወንድ እና 38 ሴት) ተማሪዎችን ሲያስመርቅ፤ በ3ኛ ዲግሪ 16 ተማሪዎችን (2ሴት እና 14 ወንድ) አስመርቋል፡፡ ከነዚህ ውስጥ በ Chemical Engineering, Electrical Engineering, Civil Engineering, and Mechanical Engineering ፕሮግራም የተመረቁ ተማሪዎች በአለም አቀፍ የጥራት ስታንዳርድ ABET accredited በሆኑ ፕሮግራሞች ትምሀርታቸውን አጠናቀው እንደተመረቁ ታውቋል፡፡ በተጨማሪም ኢንስቲትዩቱ የዘመኑን የዲጅታላይዜሽን ፋላጎት በሚያሟሉ በርካታ ፕሮግራሞች (Cyber Security, Software Engineering, Computer Engineering, Computer Science, Information Technology, Information Systems, Electromechanical Engineering) ተማሪዎችን አስተምሮ ማስመረቁ ታውቋል፡፡
ኢንስቲትዩቱ በአምስት ፋኩልቲዎች ማለትም ሲቪል እና የውሃ ሃብት ምህንድስና ፋኩልቲ፣ ኮምፒውቲንግ ፋኩልቲ፣ ኤሌክትሪካል እና ኮምፒውተር ምህንድስና ፋኩልቲ፣ መካኒካል እና ኢንዱስትሪያል ምህንድስና ፋኩልቲ፣ ኬሚካል እና ምግብ ምህንድስና ፋኩልቲ እና በሁለት ትምህርት ቤቶች ማለትም የማተርያል ሳይንስ እና ምህንድስና ት/ቤት እና ኤሮስፔስ ሳይንስና ኢንጂነሪንግ ት/ቤት የተለያዩ የቅድመ ምረቃ እና የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞችን በመስጠት ላይ ይገኛል።
ኢንስቲትዩቱ ሀገራዊ ፍይዳና የፈጠራ ክህሎት የታከለባችው ፕሮግራሞችን ማለትም ኢ-ሞባይል ምህንድስና፣ ኑክሌር ምህንድስና፣ ባዮሜዲካል ኢንጂነሪንግ፣ ሳይበር ደህንነት ምህንድስና፣ ኮምፒውተር ኢንጂነሪንግ፣ ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ እና ኤሮስፔስ ኢንጂነሪንግ ያሉ ልዩ ፕሮግራሞችን በማካተት በኢትዮጵያ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ፈር ቀዳጅ የሆነ ተግባራትን በማከናወን ላይ ይገኛል። በተጭማሪም አራት ፕሮግራሞችን (Civil Engineering, Electrical Engineering, Chemical Engineering and Mechnical Engineering ) በABET አክርዴት በማስደረግ በሀገር አቀፍ ደረጃ ፈር ቀዳጅ የሆነ ተግባር አከናውኗል፡፡
በአሁኑ ወቅት ኢንስቲትዩቱ በተለያዩ የሳይንስ፣ ምህንድስና እና ቴክኖሎጂ ዘርፎች በ21 የቅድመ ምረቃ (BSc)፣ በ43 የድህረ ምረቃ (MSc) እና በ33 የዶክትሬት (PhD) ፕሮግራሞች ብቁ ባለሞያዎችን በማፍራት ላይ ይገኛል። ከ3,100 በላይ የቅድመ ምረቃና ከ500 በላይ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች፣ ከ600 በላይ የአካዳሚክ ባለሙያዎች፣ ደረጃቻውን የጠበቁ የመማር ማስተማር መሠረተ ልማቶች፣ ከ65 በላይ የማማሪያ ክፍሎች፣ ከ78 በላይ ላቦራቶሪዎችና ወርክሾፖች፣ እና ከ35 በላይ የኮምፒውተር ላብራቶሪዎችን ጨምሮ፣ ኢንስቲቱዩቱ ለሁለገብ ቴክኖሎጂ ትምህርት እና ለተግባር ስልጠና ምቹ ሁኔታን በመፍጠር ላይ ይገኛል።
ኢንስቲትዩቱ ከአካዳሚክ ባሻገር ጠንካራ ምርምር እና ፈጠራ ስነ-ምህዳር በመፍጠር ሶስት የምርምር ማዕከላትን (በታዳሽ ኢነርጂ፣ በአይሲቲ 4D እና ምግብ እና ስነ-ምግብ ዘርፍ) እና በቢዝነስ፣ ፈጠራ እና ቴክኖ-ኢንተርፕረነርሺፕ ማእከል (BiTec) ጠንካራ ተግባራትን እያከናወነ ይገኛል። በተጨማሪም የተማሪዎችን የቴክኒካልና ተግባቦት ክህሎት የሚያበረታታ የሙያ ልማት እና የስራ እድል ማዕከል (BiT-CEED) በማቋቋም ከፍተኛ ተግባር እያከናወነ ይገኛል። በዚህም በአምስት ዓመታት ውስጥ ከ1000 በላይ ማህበረሰብን ያማከሉ ፕሮጄክቶች እና ለሀገራዊ ልማት የሚውሉ ስራዎችን ማለትም እንደ መንገድ እና ድልድይ ዲዛይን፣ በፀሐይ ሀይል የታገዘ የመስኖ ቴክኖሎጆችን፣ የዲጅታል ትራንስፖርቴሽን፣ የዲጂታላይዜሽን ሲስተም ልማት ፕሮጄክቶች እና ሀገራዊ የፖሊሲ ማዕቀፎችን በማዘጋጀትና ማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
ኢንስቲትዩት ከአለም አቀፍ ተቋማት፣ ከአልሙናይ እና ከአለምአቀፍ አውታረ መረቦች ጋር በመተባበር አለም አቀፍ ኮንፈረንሶችን (ICAST and IC4D) ያዘጋጃል፣ በ Scopus-indexed ጆርናሎች ላይ የምርምር ውጤቶች ያሳትማል እንዲሁም በእውቀት ልውውጥ መድረኮች ላይ በንቃት ይሳተፋል። በዚህም በኢትዮጵያ የቴክኖሎጂ፣ ዲጅታላይዜሽን እና የኢንዱስትሪ ለውጥ ግንባር ቀደም ማዕከል ለመሆን አካዳሚዎችን፣ ምርምሮችን፣ ፈጠራዎችን እና የማህበረሰብ አገልግሎትን በመተግበር መሪ ተቋም የመሆን ግቡን ለማሳካት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።
Information and Strategic Communication Office
Facebook፡-- https://www.facebook.com/bitpoly
Telegram፡- https://t.me/bitpoly
Website፡- https://www.bdu.edu.et/bit
Twitter: - https://twitter.com/BiT_BDU
LinkedIn: - https://www.linkedin.com/company/bitpoly/