Latest News

አድዋ ብሔራዊ የድላችን አርማ

ኑ አብረን እናክብር !!

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 126ኛው የአደዋ ድል በዓል የካቲት 23/2014ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ጀምሮ በጥበብ ሕንጻ አዳራሽ በደማቅ ሥነ-ሥርዓት ይከበራል፡፡

በዕለቱ፡-

Ø  አድዋን የተመለከቱ ምሁራዊ ጽሁፎች በዩኒቨርሲቲው የታሪክ ምሁራን ቀርበው ውይይት ይደረግባቸዋል፡፡

Ø  ተጋባዥ ታዋቂ አርቲስቶችና ከያኒያን ኪነ-ጥበባዊ ስራቸውን ያቀርባሉ፤

 

አድዋ ለእኛ ኢትዮጵያዊያን ብሔራዊ የድላችን አርማ ብጫ ሳይሆን የጥቁር ህዝቦች የኘጻነት ብርሃን ሲሆን  ሲሆን የቐኝ ገዥዎች፣ሹምባሽ ሰላቶ ፣የባንዳና እብሪተኞች የውርደት ልክ ማሳያ በመሆኑ ይህን የአገራችን ብሄራዊ የድል ቀን በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ልዩ ትርጉም ሰጥተን ላማክበር ዝግጅታችን ተጠናቋል፡፡

በመሆኑም የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች፣ መምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች፣ የድህረ ምረቃ ተማሪዎቻችን በመገኘት በዓሉ ታካፋይ እንድትሆኑ ጥሪ እናስተላልፋለን፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዘመናዊ የግብርና መሳሪያዎችን በማስገባት ላይ ነዉ

 

ዩኒቨርሲቲዉ ከዚህ በፊት በክልሉ ያልነበረ ዘመናዊ ኮምባይነርን ጨምሮ ትራክተሮች፣ የዘር መዝሪያ፣ የማዳበሪያ መጨመሪያና መኮትኮቻ ማሽኖችን የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ም/ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አልማዝ ጊዜዉ እና የዩኒቨርሲቲዉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የመሳሪያዎች ርክክብ አካሂዷል፡፡

 

የተገዙትን የግብርና መሳሪያዎች አስመልክተዉ ማብራሪያ የሰጡት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ የምርምረና ማህበረሰብ አገልግሎት የድህረ ምረቃ ም/ዲን እና የአስቸኳይ ጊዜ የስንዴ ምርት ማምረት የዩኒቨርሲቲዉ አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር ተስፋዬ መላክ መሳሪያዎቹ ለምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ከፍተኛ አስተዋፅኦ አላቸዉ ብለዋል፡፡

 

የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዘዳንት ዶ/ር ፍሬዉ ተገኘ በበኩላቸዉ የሀገርም ሆነ የተቋም መሪዎች አጋጣሚዎችን ለመልካም ነገር መጠቀም አለባቸዉ፤ በሀገራችን የተፈጠረዉ ግጭትም መሰል መፍትሄዎችን እንድናይ አድርጎናል ብለዋል፡፡ ዶ/ር ፍሬዉ አክለዉም መጥፎ አጋጣሚዎች ለመልካም ነገር መጠቀም ምን ያህል ለስኬት እንደሚያበቃ የጀርመንን ተሞክሮ ማየት ይቻላል ብለዋል፡፡ የተገዙት መሳሪያዎች ለታለመላቸዉ አላማ እንዲዉሉ ከፍተኛ ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ ገልፀው ይህን ስራ ለሰሩ የዩኒቨርሲቲዉ ምሁራን ምስጋና አቅርበዋል፡፡

 

      ዘጋቢ፦ ሸጋዉ መስፍን

 

 

“ቤተሰባዊ መማማር፣ ሀገር-በቀል አስተምህሮ እና በማህበረሰብ መማማሪያ መዕከላት አመሰራረት” ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተካሄደ፡፡

 

በስልጠናው ከሁሉም የኢትዮጱያ ክልልና ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮዎች፣ከ12ቱ ዩኒቨርሲቲዎች የመጡ ባለሙያዎች፣ ከትምህርት ሚኒሰቴር የዘርፉ ባለሙያዎችና ተጋባዥ እንግዶች ተሳትፈዉበታል፡፡

 

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የትምህርትና ስነ ባህሪ ኮሌጂ ዲን ተወካይ አቶ ቆየ ካሳ ለስልጠናዉ ተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ አቶ ቆየ ስልጠናዉ ለማህበረሰቡ ከቀለም ትምህርት ባለፈ የህይወት ክህሎት ትምህርት መሰጠት አለበት ብለዋል፡፡

 

በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ የጎልማሶች ትምህርትና ማህበረሰብ ልማት መምህርና የምርምር ቡድኑ አባል አቶ ኤርሚያስ ፀሐይ ስለ ቤተሰባዊ መረዳትና ተስተምህሮ ምንነት ፣ ይዘት፣ ዋና ዋና አላማዎችና ጠቀሜታዉ ዙሪያ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ተሳታፊዎችም በርዕሰ ጉዳዩ ላይ በጋራ በመወያየት የየራሳቸዉን ተሞክሮ በማንሳት በርዕሰ ጉዳዩ ዙሪያ አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

 

በትምህርት ሚኒስቴር የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ ሐረጓ ማሞ በበኩላቸዉ በአሁኑ ሰዓት ትምህርት ሚኒስቴር ዘርፉን ለማሳደግ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ገልፀዉ የሁሉም ክልል የስራዉ ባለቤቶች በስልጠናዉ በመታገዝ ከወትሮዉ በተለየ መልኩ ከፍተኛ እንቅስቃሴ እንዲያደርጉ በሚኒሰቴር መ/ቤቱ ስም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 

የዩኒስኮ ቼር ኢትዮጱያ አስተባባሪና የጥናት ቡድኑ መሪ ረ/ፕሮፌሰር ጥሩወርቅ ዘላለም በዉይይቱ ላይ በመገኘት “ በአፍሪካ የጎልማሶች ትምህርት እናት ” በመባል የሚታወቁትን የፕሮፌሰር ላላግ ባዉን የህይወት ተሞክሮ በማንሳት ፕሮፌሰሯ ላበረከቱት በጎ አስተዋፅኦ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ የፕሮፌሰር ላላግ ባዉን ስራዎችና የህይወት ተሞክሮም ለተሳታፊዎች ቀርቦ ዉይይት ተደርጎበታል፡፡

 

በዉይይቱ ማጠቃለያ ተገኝተዉ ንግግር ያደረጉት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዘዳንት ዶ/ር እሰይ ከበደ ዩኒቨርሲቲዉ የጎልማሶችን ትምህርት ለማጠናከር ከቅድመ ምረቃ እስከ ድህረ ምረቃ እያስተማረ ይገኛል ብለዋል፡፡

 

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ም/ፕሬዘዳንት ዶ/ር ተስፋዬ ሽፈራዉ በበኩላቸዉ የጎልማሶች ትምህርት ሁሉም ሰዉ ሊሳተፍበት እንደሚገባ ገልፀዉ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲም ዘርፉን ለማሳደግ ከዩኒስኮ ጋር በጋራ እየሰራ ነዉ ብለዋል፡፡በዚህም የባህር ዳር ከተማ የትምህርት ከተማ ተብላ በዩኒስኮ እንድትመዘገብ ማድረግ ተችሏል ብለዋል፡፡ ዶ/ር ተስፋዬ አክለዉም አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ ሲዘጋጅ የጎልማሶች ትምህርት እንዲካተት ተደርጓል ብለዋል፡፡

 

በመጨረሻም የስልጠናዉ አስተባባሪ ረ/ፕሮፌሰር ዐብይ መንክር “ የጎልማሶች ትምህርትና የእድሜ ዘመን ትምህርት ማህበር ” በማቋቋም ዘርፉን ለመደገፍ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ጠቅሰዉ የሚመለከታቸዉ አካላት የማህበሩ አባል እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

              

ዘጋቢ፦ ሸጋዉ መስፍን

 

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተለያዩ መርሀ ግብሮች ያሰለጠናቸውን 457  ተማሪዎች አስመረቀ፡፡  

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ከመጀመሪያ ድግሪ እስከ ስፔሻሊቲ በተለያዩ ትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ሴት  187 እና 270 ወንድ በአጠቃላይ 457 የህክምና ተማሪዎችን የካቲት 19 /2014 ዓ.ም በዋናው ግቢ ስታዲዬም ክብር ዶ/ር አየለ ተሾመ የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ፣ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ስራ አስፈፃሚ ፕ/ሮ የሺጌታ ገላው፣ የጥበበ ግዮን ሪፈራል ሆስፒታል ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዶ/ር ሙሉነሽ አበበ፣ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ መምህራንን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት  በደማቅ ሁኔታ አስመርቀ፡፡

 

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ በዕለቱ ባስተላለፉት መልእክት ኮሌጁ ማስመረቅ ከጀመረበት 2005 ዓ.ም ጀምሮ 3486 የጤና ባለሞያዎችን በተከታታይ በማስመረቅ የህዝብ ተቋም መሆኑን አውስተው፤በዕለቱም 50   በህክምና ስፔሻሊቲ  ፣ 24  በሁለተኛ  ዲግሪ  እና 383  በመጀመሪያ ዲግሪ የሰለጠኑ ሲሆን 187ቱ ሴቶች መሆናቸውን ገልፀዋል ።

 

ፕሬዝዳንቱ አክለውም ሀገራችን ከኢትዮጵያ ስብዕና ጋር ያጣመሩ ምርጥ ሀኪሞች ቢኖሩዋትም በተለያዩ ምክንያቶች ለአንዳንድ ህክምናዎች ወደ ውጭ ሀገር እየሄዱ መታከም የተለመደ ሆኗል፡፡ ለዚህም የድንገተኛ አደጋዎችና ቃጠሎ፣ የፅኑ ህሙማን፣ የልብ እና ተዛማች ችግሮች የኩላሊት እጥበት እና ንቅለ ተከላ፣ የጉበትና ተያያዥ ህመሞች፣ የካንሰር እና ማገገሚያና ማስተማሪያ ማዕከላት ለማቋቋም የሚያስችል ቦታ ከባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር መገኘቱን አብስረዋል፡፡

አያይዘውም ይህን የፈተና ዘመን በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የጎላ ችግር ሳይኖር ለዛሬ የምረቃ ስነ ስርዓት የበቃነው በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር፣ ወጣቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሀይማኖት አባቶች በአማራ ክልልላዊ መንግስት የሚገኙ ተቋማት፣ ፀጥታ ሀይሎች እና የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ አባላት በተለይም ተማሪዎች በተደረገው ቅንጅታዊ አሰራር በመሆኑ ሁሉንም በዩኒቨርስቲው ስም አመስግነዋል፡፡    

ዶ/ር ፍሬው ተገኘ ለተመራቂ ተማሪዎች ‹‹ ከትምህርት ተቋም ትምህርት ወደ ህይወት ትምህርት ቤት የተደላደለ ሽግግር እና ሁለንተናዊ ስኬት›› እንዲገጥማቸው ተመኝተዋል፡፡

 

በምረቃት ስነ-ስርዓቱ ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዲኤታ ክቡር ዶ/ር አየለ ተሾመ እንዳሉት ሀገራችን ኢትዮጵያ ባለፉት አመታት በገጠማት የኮቪድ እና የሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታ ሳይበግራችሁ በመመረቅ ዘርፈ ብዙ ችግር ያለበትን ህብረተሰብ ለማገልገል ስለበቃችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል፡፡

አሁን ያለው መሰረተ ልማት አንደኛ እየተመረቀ ያለውን የሰው ሀይል በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ለመሸከም በማይችልበት መልኩ ሁለተኛ የጤና ስርዓታችን ፈተና ላይ ያለ መሆኑ ማለትም ለተገልጋዩም ሆነ ለአገልጋዩች ምቹ ያልሆነ የጤና ስርዓት ተሸክመን የመጣንበት ጊዜ ላይ እንገኛለን ብለዋል፡፡ ስለዚህ ያሁኑ ትውልድ ሀላፊነት ከፍ ያለ በመሆኑ በዚሁ ልክ ተዘጋጅታችሁ ወደ ጤናው ሴክተር እንዲቀላቀሉ አደራቸውን አስተላልፈዋል፡፡

 

በ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተመራቂ ተማሪዎች መካከል በከፍተኛ ነጥብ አንደኛ ራሄል ድብወርቅ ዋለ 3.99 በማምጣት አጠቃላይ የመዳሊያ ተሸላሚ ሆናለች፡፡ እንዲሁም በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከነርሲንግ እና ሚድዋይፈሪ ፣ ከላቦራቶሪ እና ከፋርማሲ አገልግሎት ክፍሎች የላቀ የስራ አፈፃፀም ላሳዩ ሰራተኞች የዕውቅና ምስክር ወረቀት ሽልማት ተበርክቷል፡፡ 

 

ዝክረ አድዋ ፤የባሕል ኮንፈረንስ ተካሄደ

*********************************

በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ሂውማኒቲ ፋኩልቲ አዘጋጅነት ዝክረ አድዋ ፤የባሕል ኮንፈረንስ "የአድዋ ድል ለኢትዮጵያ ማንነት እና የባህል ልዕልና" በሚል መሪ ቃል የካቲት 17/2014 ዓ.ም በዋናው ግቢ የመሰብሰቢያ አዳራሽ በድምቀት   ተካሄደ ።

የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት  የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ ፕሬዝዳንት  ዶ/ር እሰይ ከበደ የአድዋ ድል ሀገራችን ኢትዮጵያ በቅኝ ግዛት ያልተያዘች ብቸኛ አፍሪካዊት ሀገር እንድትሆን ያደረጋት በመሆኑ ዛሬ እኛ በየሄድንበት ሁሉ አንገታችንን ቀና አድርገን እንድንናገር አድርጎናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ የአድዋ ድል የፋሽስት ጣሊያን ኢትዮጵያን በቅኝ ግዛት የመያዝ ፍላጎት የከሸፈበት ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል የዓለም ጭቁን ሕዝቦች ያካሄዱት ፀረ-ቅኝ አገዛዝ ትግል አብይ አካል እንደነበር ማሳያ ጭምር ነው ሲሉ ዶ/ር እሰይ ተናግረዋል፡፡ የዘንድሮን 126ኛውን የአድዋ ድል በዓልን ስናከብር ካለፉት ዓመታት  የተለየ የሚያደርገው አንደኛ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን ሀገርን የማፍረስ ሴራው በዘመቻ ለህብረብሔራዊ አንድነት አማካኝነት  የከሸፈበት፣  ሁለተኛ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የመጀመሪያው ዙር ሀይል የማመንጨት ስራ የጀመረበት በመሆኑ  እና  ተቋማችን ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመሰረተበትን 60ኛ ዓመት በድምቀት ለማክበር ዝግጅት እያደረገ ባለበት ወቅት የሚከበር በዓል በመሆኑ  ከምንግዜው   በእጅጉ የተለየ በዓል መሆኑን  ተናግረዋል፡፡

በአውደ ጥናቱ ላይ ከቀረቡት ጥናታዎ ፁሁፎች መካከል ፤ የታሪክ ምሁር ፕሮፌሰር ሹመት ሲሻኝ የአድዋው ድል ሚስጢር "ስውር ማግኔት" በሚል ርዕስ  እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባሕል፣ ኪነ ጥበብ እና ቱሪዝም ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ሠርጸ ፍሬስብሃት ለአድዋ ድል; የአዝማሪዎች ሚና፣ የፍልስፍና ምሁሩ ዶ/ር ዳኛቸው  አሰፋ “ዓድዋ በቅኝ ገዢ መንፈስና በነጻነት መንፈስ መካከል የተካሄደ ትግል“ በሚል ርዕስ እንዲሁም  በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አለ ፈለገ ሰላም የስነ-ጥበብ እና ዲዛይን ትምህርት ቤት ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አገኘሁ አዳነ ደግሞ “አርበኝነት ድልና ገድል በሥነ-ሥዕል”  በሚል ርዕስ ግሩም የሆኑ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው  ከመርሀ ግብሩ ተሳታፊዎች  በርካታ ጥያቄዎች ተነስተው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

አውደ ጥናቱ 126 ኛ የዓድዋ ድል በዓልን የሚዘክረው እና የአሁኑ ትውልድ ከድሉ ብስራት ዐሻራ ምን ሊወርስ ይገባል የሚል ዓላማ ያለው እና በርካታ የዩኒቨርሲቲው መምህራን እና ተማሪዎች እንዲሁም የአስተዳደር ሰራተኞች በንቃት የተሳተፉበት ነው ።

በመጨረሻም የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሂውማኒቲ ፋኩልቲ ዲን የሆኑት ዶ/ር ሰፋ መካ በአውደ ጥናቱ የመዝጊያ ስነ-ስርዓት ላይ እንዳሉት የአድዋ ድል የአንድነትና የአሸናፊነት ድል በመሆኑ ሀገራችን አሁን ካለችበት ወቅታዊ ችግር ልትላቀቅ የምትችለው የጥንት ጀግኖች አባቶቻችን የመጣባቸውን  ሀገራዊ ችግር በጀግነትና በድል የተወጡበትን መንገድ በመከተል፤ የአሁኑ ትውልድ ያጋጠመውን የእርስ በርስ ፣አለመግባባት በማስወገድ የአድዋ የድል በዓልን በጠንካራ ሀገራዊ መንፈስ ማክበር እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ 

 

Training on the concepts of family literacy and learning, community learning centres (CLCs) and facilitation skills was held from 17-19 February/2022 in Bahir Dar.

The training was organized by the University of East Anglia's (UEA) UNESCO Chair in Adult Literacy and Learning for Social Transformation in which Bahir Dar University is a member University (along with six other universities).

 

The training is an outcome from the project entitled "Family Literacy, Indigenous Learning and Sustainable Development", which is part of a bigger project - Meeting the SDGs: creating innovative infrastructures and policy solutions to support sustainable development in Global South communities (GS-DEV) which is the title of University of East Anglia's Global Research Translation Award (ref. EP/T015411/1). The award is funded by United Kingdom Research and Innovation (UKRI) through the Global Challenges Research Fund (GCRF), part of the UK's Official Development Assistance (ODA).

 

The project has research and intervention components. One of the interventions is the provision of training on the listed topics.

 

Adult Education Experts from Regional Education Bureau, all Zones and City administrations of Amhara National Regional State, experts and facilitators all CLCs (both operational and planned), and Woreda/District level experts and facilitators have taken part in the training. There were 90 participants in the training.

 

Mr. Abiy Menkir, member of the UNESCO Chair Programme, introduced the training programme and the trainers to the participants. Next, Mr. MarewDerso, senior Adult Education Expert at the Regional Education Bureau forwarded a welcoming remark to the trainees. Then, Dr. Tesfaye Shiferaw, Research and Community Service Vice President at Bahir Dar University opened the training and addressed the trainees with key messages. Among others, Dr. Tesfaye emphasized the importance of adult literacy and learning for social development. He also reminded trainees to bring about change to their community’s lives using the inputs they get from thistraining. Admiring the establishment of the pioneer CLCs, Dr. Tesfaye indicated that more CLCs need to be established in each Zone and Districtin the region.

On February 17 (the first day), the training focused on facilitation skills whereby basic concepts related with literacy, adult education, non-formal education, etc. were discussed. It was provided in two separate sessions to allow more interaction and discussions. EndayehuTegegne, YerasworkMegerssa, Ermiyas Tsehay and AtaleTilahun were the trainers on this day. 

 

On the second day, the training introduced the concept of family literacy and learning to the participants (from conceptual clarification, to learning and administrative issues within family and intergenerational learning programmes). As this concept is relatively new, this was more of a firsthand awareness raising for most of the trainees. Ermiyas Tsehay and Tizita Lemma were the trainers on this day.

 

On the third day, the conceptual and practical aspects of community learning centres (CLCs) were discussed. As there are a handful of CLCs already established in the region (whose district focal persons, coordinators and facilitators are in this training), the training was animated with practical discussions of running/management issues, benefits and challenges of these centres. MarewDerso (from the Regional Bureau) and YerasworkMegerssa were the trainers on this day. Overall, the training was very lively with very active participation of the trainees.

 

Upon the request of the Regional Education Bureau, time was allotted for discussion on administrative issues of adult education in the region with all participants. Accordingly, Mr. Mulaw Abebe, Deputy Head of the Regional Education Bureau led the discussion. In this session, candid discussions on the challenges and opportunities of the region’s adult education sector were raised. At the end, it was emphasized that everyone should work with synergy and agreed that all parties need to play their role effectively in order to bring about improvement in the standing of the adult education sector in the region (which was currently evaluated to be poor). Mr. Mulaw said that the Regional Education Bureau is committed and eager to bring about positive changes and improvement to the adulteducation sector; but, he also called upon all participants to build their personal and professional capacities and contribute their share to the sector instead of expecting everything from the government.

 

The closing session was facilitated by Mrs. TuruwarkZalalam, Coordinator of the UNESCO Chair Programme in BDU and Mr. Mulaw Abebe. A handful of training participants presented a recap of the three-day’s training sessions. Besides, this session emphasized on a discussion of: what the participants felt about the overall training, what their takeaways are from these training sessions. In her closing remark, Mrs. Turuwark remarked on the project’s background, discussed the missions of Bahir Dar University, and reminded what every parties’ roles are in the bid towards the improvement of the adult education sector in the region.

 

Finally, Mr. Mulaw and Mrs. Turuwark, with the facilitation of Mr. Ermiyas Tsehay, the master-of ceremony for the three days, handed down certificates to the training participants. 

Bahir Dar University- BiT hosts a seminar on Asteroids and the robotic technology

(BDU, February 21, 2022)

Dr. –Ing Melak Mekonen, a system and Robotics Engineer at NASA Gorrard Flight Center, alumnus of the former Poly Technique Institute of Bahir Dar University delivered a captivating seminar on DART (Double Asteroid Reduction Test), Military and Space Robotics, and System Engineering.

To view the news in full visit: https://www.facebook.com/bitpoly/posts/1519388931795605

እንኳን ደስ አለን!

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጨት ሥራን በይፋ ጀምሯል።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲም የአንድነታችን ምልክት የሆነው የሕዳሴ ግድባችን የኤሌክትሪክ ኃይል የማመንጨት ሥራውን በይፋ በመጀመሩ የተሰማውን ደስታ እየገለፀ ለኢትዮጵያውያንና ለኢትዮጵያ ወዳጆች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት ይወዳል፡፡

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

Bahir Dar Institute of Technology-Bahir Dar University hosted a Public Speech by Dr. Taye Girma on Artificial Intelligence Challenges and Opportunities https://www.facebook.com/bitpoly/posts/1517308818670283

Pages