የሰላም አካዳሚ መምህራን እና ተማሪዎች 130ኛውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል አከበሩ
Selam Campus
04 Mar, 2026
የሰላም አካዳሚ መምህራን እና ተማሪዎች 130ኛውን የዓድዋ ድል መታሰቢያ በዓል አከበሩ፡፡
የካቲት 20/2018ዓ/ም (BDU-EiTEX) በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ውስጥ የሚገኘው የሰላም አካዳሚ መምህራን እና ተማሪዎች በግቢው በሚገኘው የፋሽን ሾው አዳራሽ የአድዋ በዓል በደማቅ ሁኔታ አከበሩ፡፡
የአካዳሚው ርዕሰ መምህር አቶ አብርሃም ካሴ በመክፈቻ ንግግራቸው የመምህራን አንዱ ዓላማቸው ታሪክ ሰሪ ትውልድን መፍጠር መሆኑን ገልጸው፤ ይህ በዓል ለተማሪዎቹ የሀገራቸውን ታሪክ አውቀው እንዲያድጉ እና የጥንት አባቶቻችን የሰሩትን ድል እና ታሪካዊ አሻራቸውን አርአያ በማድረግ የራሳቸውን አሻራ ማስቀመጥ እና ድል ማስመዝገብ እንዲችሉ የሚያግዝ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የጥንት አባቶቻችን የጣሊያንን ሰራዊት በአድዋ ጦርነት ድል ሲያደርጉ በርካታ አሻራዎችን ጥለውልን ስላለፉ የአሁኑ ትውልድ ደግሞ የእነሱን ፈለግ በመከተል የሀገራችንን የወደፊት እጣ ፈንታ የተሻለ ለማድረግ በተሰማሩበት የስራ መስክ ውጤታማ በመሆን ግዴታቸውን መወጣት አለባቸው በማለት አቶ አብርሃም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በዝግጅቱ ላይም በተማሪዎች በዓሉን በተመለከተ
- በርካታ ግጥሞች፣
- መዝሙር፣
ድራማ እና ውዝዋዜ ቀርበዋል፡፡

