ለመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የትምህርት መስክ ለመምረጥ የሚያስችል ግንዛቤ እንዲኖራቸው ገለጻ ተደረገላቸው
Selam Campus
25 Feb, 2026
ለመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የትምህርት መስክ ለመምረጥ ግንዛቤ እንዲኖራቸው የሚያስችል ገለጻ ተደረገላቸው፡፡
የካቲት 17/2018 ዓ.ም (BDU-EiTEX) በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ግቢ የተመደቡ ወደ 2500 የሚጠጉ የተፈጥሮ ሳይንስ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች የመጀመሪያውን መንፈቀ ዓመት ትምህርታቸውን በማጠናቀቃቸው እና ቀጣዩን መንፈቀ ዓመት ትምህርት መማር ከመጀመራቸው በፊት ትምህርት መስክ መምረጥ ስላለባቸው ግንዛቤ እንዲኖራቸው የሚያስችል አጠቃላይ ገለፃ መሰጠቱን የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች ፕሮግራም ምክትል ዲን አቶ የቆየ ታደለ ተናግረዋል፡፡
አቶ የቆየ አክለውም ተማሪዎቹ ትምህርት መስካቸውን መምረጥ የሚችሉት እንዴት ነው?፣ መስፈርቱስ ምንድን ነው? የሚለውን እንዲያውቁት ለማድረግ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀውን የሙያ መስክ ምደባ አፈጻጸም መመሪያ ላይ ማብራሪያ መሰጠታቸውን፤ እንዲሁም ከእያንዳንዱ ትምህርት ክፍል ተወክለው በመጡ መምህራን አማካኝነት ስለ እያንዳንዱ የትምህርት መስክ ሰፊ ትንታኔ እንደተደረገላቸውም ገልጸዋል፡፡

በመጨረሻም የተማሪ መረጃ አስተዳደር ስርዓት (SIMS) ባለሙያዎች ለተማሪዎች ስለ Portal አጠቃቀም ወይም ተማሪዎች ወጤታቸውን በበይነ መረብ እንዴት ማየት እንደሚችሉና የትምህርት መስካቸውን እንዴት እንደሚመርጡ ማብራሪያ መሰጠታቸውን ተናግረዋል፡፡
