ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስ-ገዝነት (Autonomy) የሚደረገውን ጉዞ እያፋጠነ መሆኑን ገለጸ
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት መንገሻ አየነ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት "ጋዜጣ ፕላስ" ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ዩኒቨርሲቲው ስትራቴጂካዊ ዕቅዶችን በማውጣት ወደ ራስ-ገዝነት ለመሸጋገር የሚያደርገውን ጉዞ እያፋጠነ መሆኑን ገልጸዋል።
ፕሬዚዳንቱ አክለውም ዩኒቨርሲቲው ለዚህ ታሪካዊ ሽግግር የሚያበቁ የዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝና ሂደቱን በበላይነት የሚመራ የራስ-ገዝነት ጽሕፈት ቤት በማቋቋም ወደ ተግባር መገባቱን ገልጸዋል። በአሁኑ ወቅት ተቋሙ የራሱን ውስጣዊ ምዘና በማካሄድ ላይ የሚገኝ ሲሆን በትምህርት ሚኒስቴር የተቀመጡ መስፈርቶችን በማሟላት ረገድ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ በትጋት እየሠራ መሆኑን ዶ/ር መንገሻ ጠቁመዋል