የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ የውጤታማ ትግበራ ዳይሬክቶሬት

'ዴሊቬሮሎጂ' የውጤታማ ትግበራ እ.ኤ.አ ከ1997 ቶኒ ብሌየር እንግሊዝን በሚመሩበት ወቅት ተቋማት ውጤታማ አገልግሎት እንዲሰጡ ያስቻለ ሲሆን፤ በተለይ ደግሞ በጤናው ዘርፍ በእንግሊዝ የተሻለ ውጤት እንዲመዘገብ አስችሏል። ከዚህም በተጨማሪ በዩናይትድ ስቴትስ ሜሪላንድ ግዛት፣ በፓኪስታን ፑንጃብ ግዛት፣ በማላዢያ፣ በኡጋንዳ፣ በ…በመሳሰሉት አገሮች ተሞክሮ ውጤት ያስገኘ የአሰራር ሥርዓት ነው፡፡

በአገራችንም ከዚህ በፊት የተለያዩ ቅድሚያ የሚሹ ጉዳዮች ተለይተው ቅድሚያ ትኩረት ተሰጥቷቸው በአግባቡ እየተተገበረ የሚገኝ ሲሆን፤ ለአብነትም በግብርና ትራንስፎርሜሽን፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት፣ በግብርና ታክስ አሰባሰብ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትኩረት የሚሹ ዘርፎችን በመለየት የውጤታማነት ሥርዓቱ በመተግበር ላይ ነው።

በተመሳሳይ የኢፌዴሪ የትምህርት ሚኒስቴር ከ2010 በጀት ዓመት ጀምሮ የውጤታማነት ትግበራ አሰራር ሥርዓትን በትምህርትና ሥልጠና ዘርፍ ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች በመለየት ውጤታማ ለማድረግ ትግበራ ውስጥ ገብቷል። በዚህም መሰረት 80 በመቶ በላይ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሚመረቁ ተማሪዎች ከተመረቁ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ወደ ሥራ ገበታ እንዲሰማሩ ለማድረግ በቅድሚያ ውጤት እንዲመረጡ የሚያስችል አሰራር ተለይቷል። ትግበራው ውጤታማ እንዲሆን ከኢንዱስትሪ ጋር፣ ከአካባቢ ማህበረሰብ፣ ከቴክኒክና ሙያ እንዲሁም ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርቦ መሥራት የሚጠይቅ ይሆናል።

ጽንስ ሀሳቡ ተቋማት ባስቀመጡት የተለጠጠ ግብ መሠረት በቅድሚያ መፈጸም ያለባቸውን ተግባራት በመረጃና ማስረጃ አስደግፈው ቅድሚያ በመስጠት በጥራትና በፍጥነት ወደ ውጤት መቀየር ነው። ሂደቱ በተቋማት የ'ዴሊቬሮሎጂ' ቡድን ተቋቁሞ በዚሁ ሥራ ላይ ብቻ አተኩረው በሚሰሩ ባለሙያዎች ተደራጅተው የተቋማት ኃላፊዎች ዕለታዊ፣ ሳምንታዊ፣ ወርኃዊ እንዲሁም በሩብና በግማሽ ዓመት ውስጥ ጠንካራ ክትትል የሚደረጉበት አሰራር ነው። 'ዴሊቬሮሎጂ' ከቢፒ.አር፣ ቢ.ኤስ.ሲና ከሌሎች የሪፎርም ትግበራ መሣሪያዎች ጋር ጎን ለጎን ተፈጻሚ ሊሆን የሚችል ነው። በተጨማሪም በውጤታማ ትግበራ ቡድንና በሌሎች የለውጥ ትግበራ ቡድኖች መካከል ልዩነት አለ ተብሎ የሚወሰድም ከሆነ፤ ይህ ቡድን እነዚያ ቀደም ሲል የተቋቋሙ ቡድኖች መኖር አለመኖራቸውን ለመከታተልና ለማረጋገጥ ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆኑ የማስቻል ተልዕኮን የያዘ ሂደት መሆኑ ነው።

የውጤታማነት ትግበራ አሰራርን በየተቋማቱ ነባራዊ ሁኔታ በሚመች መልኩ ጥቅም ላይ ማዋል ተገቢ ነው፡፡

በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ የውጤታማ ትግበራ አሰራርን የሚመራ ቡድን የተቋቋመ ሲሆን በውስጡም አንድ የቡድን መሪን ጨምሮ በሥሩ ሦስት ከፍተኛ ባለሙያዎችን /experts/   ያካተተ ነው፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ የውጤታማ ትግበራ ቡድን የተቋቋመበት ዋና ዓላማ በ2020 እ.ኤ.አ. ከዩኒቨርስቲያችን በመደበኛው ፕሮግራም የሚመረቁ የቅድመ-ምሩቃን ወደ ሥራ ዓለም የመግባት አቅም አሁን ካለበት በግምት 72 ፐርሰንት ወደ 93 ፐርሰንት የማድረስ ዒላማን ለማሳካት ሲሆን፤ ይህንንም ዒላማ ለማሳካት ያስችላሉ ተብለው የተለዩ ሰባት ስትራቴጂዎችን ለመተግበር በሚደረገው የመላው የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ በመምራትና በማስተባበር፣ በመደገፍ ሒደት የተገኙትን ውጤቶችን፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን፣ የተወሰዱየመፍትሔ ዕርምጃዎችን በቅርበት በመከታተል በቂና ተአማኒነት ያላቸውን መረጃ እየሰበሰበ በየጊዜው (ብዙውን ጊዜ በየሳምንቱ) ለትምህርት ሚኒስቴር ሪፖርት ማድረግ ነው፡፡ ሰባቱ ስትራቴጂዎች የሚከተሉት ናቸው፡-

  1. የመምህራን ምዘና /Teacher Assessment
  2. የተማሪዎች ምዘና /Student Assessment
  3. ተከታታነት ያለውየመምህርነት ሙያ ማሻሻያ ልማት/Continuous Professional Development (including English)
  4. ለተማሪዎች የእንግሊዝኛ ቋንቋ ማሻሻያ ፕሮግራም /English Language (Students)
  5. ለተማሪዎች ስራ ማፈላለጊያ /Career Services
  6. ኢንተርንሺ / Internships
  7. ተመራቂ ተማሪዎቻችን ያሉበትን ሁኔታና የገበያውን ፍላጎት መከታተያ ጥናት Tracer Study/