ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በጅማው የስፖርት ፌስቲቫል በድል ጀምሯል
በጅማ ዩኒቨርሲቲ አስተናጋጅነት በድምቀት የተጀመረው 10ኛው የመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስፖርት ፌስቲቫል በፉክክር ታጅቦ ቀጥሏል። በ15 የስፖርት አይነቶች 47 ዩኒቨርሲቲዎችን ባሳተፈው በዚህ ታላቅ መድረክ፣ አንጋፋው ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በመክፈቻ ጨዋታዎቹ አበረታች ውጤቶችን አስመዝግቧል።
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለይም በእጅ ኳስ እና በመረብ ኳስ ዘርፎች የበላይነትን በማሳየት ውድድሩን በድል ከፍቷል፦
• በእጅ ኳስ፦ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የወንዶች ቡድን ከአምቦ ዩኒቨርሲቲ ጋር ባደረገው ጨዋታ ተጋጣሚውን 24 ለ 6 በሆነ ሰፊ የጎል ልዩነት በማሸነፍ አስደናቂ አጀማመር አድርጓል።
• በመረብ ኳስ፦ ከጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ጋር የተገናኘው የባሕር ዳር ቡድን በጠንካራ ፉክክር ታጅቦ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት ድል ቀንቶታል።
• በቅርጫት ኳስ፦ በዲላ ዩኒቨርሲቲ እና በባሕር ዳር መካከል በተደረገው ጨዋታ ከፍተኛ ፉክክር የታየበት ቢሆንም፣ ጨዋታው በዲላ ዩኒቨርሲቲ 52 ለ 41 አሸናፊነት ተጠናቋል።
የቀን 19/05/18 መርሃ ግብር
በቀጣዮቹ ቀናትም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ዘርፎች ወሳኝ ጨዋታዎችን የሚያደርግ ይሆናል። እንደ መርሃ ግብሩ፦
• በእግር ኳስ፦ ባሕር ዳር ከመቱ ዩኒቨርሲቲ ጋር ይገናኛል።
• በባድመንተን፦ ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ ጋር ትንቅንቅ ያደርጋል።
• በቴኳንዶ፦ በ4 የተለያዩ የውድድር መርሃ ግብሮች ተሳታፊ ይሆናል።