ቀን፡ 12/06/2018 ዓ.ም

ክፍት የኃላፊነት ቦታ ማስታወቂያ (በድጋሜ የወጣ)

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመካከለኛ አመራር ምርጫና አሰያየምን ለመደንገግ ባወጣዉ ማሻሻያ መመሪያ ቁጥር 05/2012 መሰረት ለ College of Agriculture and Environmental Sciences postgraduate, Research and Community Engagement V/Dean ቦታ በመመሪያው በወጣው መስፈርት መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ ለመሾም በወጣው ማስታወቂያ በቂ አመልካች አልተገኘም። በመሆኑም በድጋሜ ማውጣት አስፈልጓል፡፡

ክፍት የኃላፊነት ቦታ፡ ለ College of Agriculture and Environmental Sciences postgraduate, Research and Community Engagement V/Dean

የማወዳደሪያ መስፈርት፡-

1ኛ. የትምህርት ማእረግ/ደረጃ፡ ሌክቸረርና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት

2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማትወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተ ቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት ዕርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረከተ/ች፤

3ኛ. በሚያመለክቱበት አካዳሚክ ክፍልና ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የከፍተኛ ትምህርት ተደራሽነት፣ ፍትኃዊነት፣ጥራት፣ ተገቢነትና ዓለምአቀፋዊነትን ለማሳካት፣ አካዳሚክ ክፍሉን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለማቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ቸማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል ስትራቴጂያዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/ምትችል፤

4ኛ. የአካዳሚክ ክፍሉ ማህበረሰብ፣ የአካዳሚክ ኮሚሽኑ አባላት እንዲሁም የሚመለከታቸው ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለጻ መስጠት የሚችል/ምትችል፤

አመልካቾች፡-

ይህ ማስታወቂያ በዩኒቨርሲቲው ድህረ- ገጽ፣ ፌስቡክና ማስታወቂያ ሰሌዳዎች ከተገለጸበት የካቲት 12 /2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የትምህርትና የስራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጂያዊ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ፡

በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች +251 583 20 9653 ወይም +251 583 20 6059 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡

ኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚኒኬሽን ም/ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ