የታላቁ ባለራዕይ ሐኪም ዶ/ር አንዷለም ዳኜ የመታሰቢያ ሳምንት
Bahir Dar University, Ethiopia.
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ፣ በጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል፤ በስራቸው ለሀገራቸው አርአያ፣ በልበ ቀናነታቸውና በራዕያቸው ለብዙዎች ተምሳሌት የነበሩትን የጀግናውን ሐኪም የዶ/ር አንዷለም ዳኜን ህይወትና ስራ የሚዘክር ልዩ የመታሰቢያ ሳምንት ተዘጋጅቷል።
ይህ የመታሰቢያ ሳምንት ከነገ ጥር 20 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ለተከታታይ 10 ቀናት የሚቆይ ሲሆን፣ የተለያዩ ምሁራዊና ማህበራዊ ተግባራት ይከናወኑበታል።
ዋና ዋና የመታሰቢያ መርሃ ግብሮች
1. ምሁራዊ ሴሚናሮች (Seminars)
የዶ/ር አንዷለምን የላቀ የሙያ ስብዕና እና የአመራር ጥበብ በሚዘክሩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ውይይቶች ይካሄዳሉ፦
የአመራር ጥበብ (Leadership)፦ የአካዳሚክ ልቀት እና የሥነ-ምግባር እሴቶች።
ዓለም አቀፍ የቀዶ ጥገና አዝማሚያዎች፦ በጤና ሥርዓቱ ላይ ያላቸው ተፅዕኖና ፋይዳ።
2. የሕክምና አገልግሎት ዘመቻ (Clinical Campaign)
የዶ/ር አንዷለምን የህዝብ አገልጋይነት መንፈስ በተግባር ለመግለጽ በሚከተሉት የሕክምና ዘርፎች ነፃ የሕክምና አገልግሎት ይሰጣል፦
የጉበት እና የጨጓራ ቀዶ ጥገና (HB and GI)
የሕፃናት ቀዶ ጥገና (Pediatric Surgery)
የጆሮ፣ አፍንጫ እና ጉሮሮ ሕክምና (ENT)
የራስ እና የአንገት ቀዶ ጥገና (Head and Neck)
የመክፈቻ ቦታና ቀን
ቀን፦ ጥር 20 ቀን 2018 ዓ.ም
ቦታ፦ ጥበበ ግዮን ግቢ (በሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ)
የታላቁን ሐኪም አርአያነት በመከተልና ራዕያቸውን በጋራ በማለም፣ በዚህ ታላቅ መርሃ ግብር ላይ እንድትገኙ ተጋብዛችኋል።
ክብር ለሀገር ባለውለታዎች!
Ethiopian Institute of Textile and Fashion Technology
Bahir Dar Institute of Technology, Bahir Dar University, Ethiopia