የእድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ

08 Oct, 2025

የእድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ


ከጥቅምት 12- 15/2018 ዓ.ም ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከእስራኤል ሐገር ከሚመጡ ከፍተኛ የቀዶ ህክምና ባለሞያዎች ጋር በመተባበር በዘመናዊ መሳሪያ የታገዘ ከፍተኛ የቀዶ ህክምና (Laparoscopic Surgery) አገልግሎት ይሰጣል::

አገልግሎት የሚሰጥባቸው ዘርፎች

------------------------------------------

1. የሐሞት ጠጠር ቀዶ ህክምና (Laparascopic cholecystectomy)

2. የጉረሮ ካንሰር እና ሌሎች የጉረሮ ህመሞች ቀዶ ህክምና (Esophageal disease and other related pathologies surgery)

3. የጨጓራ ካንሰር እና ሌሎች ተያያዥ የጤና ችግሮች ቀዶ ህክምና (Gastric cancer and other gastric pathologies surgery)

4. የቆሽት፣ የሐሞት ቱቦ እና የጣፊያ ቀዶ ህክምና (Hepatopancreaticobiliary surgery) እና

5. የአንጀት ካንሰር እና ተያያዥ የጤና ችግሮች ቀዶ ህክምና (Colorectal and other related diseases surgery) ናቸው::

ነገር ግን ሆስፒታላችን ባሉት የሰብ-ስፔሻሊስት ሀኪሞች ለማህበረሰባችን እየሰጠ ከሚገኘው አገልግሎት ውስጥ አንዱ በሆነው የሐሞት ጠጠር ቀዶ ህክምና (Laparascopic cholecystectomy) አገልግሎት የምትፈልጉ ህሙማን እስካሁን ስላልተመዘገባችሁ ከጥቅምት 10 ጀምሮ ወደ ሆስፒታላችን በመምጣት ከሌሎች የሕክምና አገልግሎት ዘርፎች ጋር ተጠቃሚ ትሆኑ ዘንድ ጥሪያችንን እንሳተላልፋለን::

የጋራ ጥረት ለማኅበረሰብ ጤንነት!

ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ