ለመውጫ ፈተና ተፈታኞች በሙሉ:- የፈተና መርሀ ግብሩን በአንድ ቀን ማሸጋሸግ

Submitted by Fisseha on

ቀን፡17/2018 ዓ.ም 
ማስታወቂያ
ለመውጫ  ፈተና ተፈታኞች በሙሉ

የቅድመ ምረቃ ትምህርት መውጫ ፈተና (Exit exam) ከየካቲት 17/2018 ዓ.ም መሰጠት መጀመሩ ይታወቃል፡፡ ሆኖም በሀይል መቆራረጥ ችግር ምክንያት በዋናው ዳታ ማዕከል ላይ ችግር በመፈጠሩ አስተካክሎ እንደገና ለማስጀመር የተደረገው ጥረት ውጤት ያመጣ ቢሆንም የፈተና መርሀ ግብሩን ያዛባ ስለሆነ ሙሉ ፕሮግራሙን በአንድ ቀን ማሸጋሸግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል፡፡ ስለሆነም የካቲት 17/2018 ዓ.ም ሊሰጥ የታቀደው ፈተና ወደ የካቲት 18/2018 ዓ.ም የተሸጋሸገ ስለሆነ በተመሳሳይ እያንዳንዱ ፈተና ወደ ቀጣይ ቀን ስለተሸጋሸገ በመርሀ ግብሩ መሰረት ተፈታኞች በየተመደቡበት ግቢ ይህን አውቀው እንዲገኙና እንዲፈተኑ ስልን እናሳውቃለን፡፡ 

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ድርጅት