News

ክፍት የኅላፊነት ቦታ ማስታወቂያ

ክፍት የኅላፊነት ቦታ ማስታወቂያ 
===================
18/06/2016 ዓ.ም 

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዩኒቨርሲቲው ባወጣው አዲስ የመካከለኛ አመራሮች መመደቢያ መመሪያ መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ የኮሌጁ የጤና ትምህርት ኮርፓሬት ም/ድሬክተር (Deputy Corporate Director, Medical and Health Science Education) ቦታ መመደብ ይፈልጋል፡፡ 

የማወዳደሪያ መሥፈርት 
==============

1ኛ. የትምህርት ደረጃ ሦስተኛ ዲግሪ/ስፔሻሊቲ ሰርተፊኬት (ወይም አቻ ) እና ረዳት ፕሮፌሰር እና ከዚያ በላይ ማዕረግ ያለው/ያላት፣  
2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በጥናትና ምርምር ወይም መሰል ተቋማት፣ በመማር ማስተማር፣ ሕክምናና ማኅበረሰብ አገልግሎት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት እርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከተ/ች፣  
3ኛ. በሚያመለክቱበት ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የጤና ትምህርት  ተደራሽነት፣ ፍትሐዊነት፣ ጥራትንና ደኅንነት፣ ተገቢነትና ዓለም አቀፋዊነትን ለማሳካት፣ ኮሌጁን የጤና ትምህርት የልህቀት ማዕከል ለማድረግ እና ክሱትነቱን ለመጨመር፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለም አቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ለማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል አጭር ስትራቴጅያዊ (ስልታዊ) ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/የምትችል፣  
4ኛ. ከኮሌጁ የሚሰጠውን ዝርዝር ኃላፊነት በቅንነት፣ በትጋትና በታማኝነት ተቀብሎ  በከፍተኛ ብቃት የሚፈፅም፣ 
5ኛ. የኮሌጁ አመራሮች፣ የማኔጅመንት አባላት፣ የኮሌጁ መምሕራን ተወካዮች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለፃ መስጠት የሚችል/የምትችል፣ 
6ኛ. ከትምህርት ወይም ምርምር ወይም ሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ መደበኛ የሥራ እረፍት ላይ ያልሆነ/ች እና ለቀጣይ ሦስት ዓመት በኃላፊነት ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ/ች::

አመልካቾች፡- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን (18/06/2016ዓ.ም) ጀምሮ ባሉት ዐሥራ አምስት (15) ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚከተሉትን ሰነዶች ማለትም 
1. ማመልከቻ ደብዳቤ፣
2. ግለ ታሪክ('CV')፣ 
3. የትምህርትና የሥራ/አመራርነት ልምድ (በሰው ሀብት አስተዳድር ልማት ቢሮ የረጋገጠ) ማስረጃ ፎቶ ኮፒ  እንዲሁም
4. ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጅያዊ ዕቅድ
በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ድሬክተር ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 

የመመዝገቢያ ቦታ 
==========
ጥበበ ግዮን ካምፓስ
ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲ
ባሕር ዳር

ክፍት የኅላፊነት ቦታ ማስታወቂያ

ክፍት የኅላፊነት ቦታ ማስታወቂያ 
==================
18/06/2016 ዓ.ም 

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዩኒቨርሲቲው ባወጣው አዲስ የመካከለኛ አመራሮች መመደቢያ መመሪያ መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ የኮሌጁ የጥናት፣ ምርምር እና ማኅበረሰብ አገልግሎት ኮርፖሬት ድሬክተር (Corporate Director, Research, Development and Community Services) ቦታ መመደብ ይፈልጋል፡፡ 

የማወዳደሪያ መሥፈርት 
==============

1ኛ. የትምህርት ደረጃ ሦስተኛ ዲግሪ/ስፔሻሊቲ ሰርተፊኬት (ወይም አቻ ) እና ረዳት ፕሮፌሰር እና ከዚያ በላይ ማዕረግ ያለው/ያላት ፣  
2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በጥናትና ምርምር ወይም መሰል ተቋማት፣ በመማር ማስተማር፣ ማኅበረሰብ አገልግሎት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት እርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከተ/ች፣  
3ኛ. በሚያመለክቱበት ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የጥናትና ምርምር እና ማኅበረሰብ አገልግሎት ተደራሽነት፣ ፍትሐዊነት እና ችግር ፈችነት፣ ጥራትንና ደኅንነት፣ ተገቢነትና ዓለም አቀፋዊነትን ለማሳካት፣ ኮሌጁን ድህረ ምረቃ መር የልህቀት ማዕከል ለማድረግ እና ክሱትነቱን ለመጨመር፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት ፣ እንዲሁም ዓለም አቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ለማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል አጭር ስትራቴጅያዊ (ስልታዊ) ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/የምትችል፣  
4ኛ. ከኮሌጁ የሚሰጠውን ዝርዝር ኃላፊነት በቅንነት፣ በትጋትና በታማኝነት ተቀብሎ  በከፍተኛ ብቃት የሚፈፅም፣ 
5ኛ. የኮሌጁ አመራሮች፣ የማኔጅመንት አባላት፣ የኮሌጁ መምሕራን ተወካዮች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለፃ መስጠት የሚችል/የምትችል፣ 
6ኛ. ከትምህርት ወይም ምርምር ወይም ሌሎች ጉዳዮች ጋር በተያያዘ መደበኛ የሥራ እረፍት ላይ ያልሆነ/ች እና ለቀጣይ ሦስት ዓመት በኃላፊነት ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ/ች::

አመልካቾች፡- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን (18/06/2016ዓ.ም) ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚከተሉትን ሰነዶች ማለትም 
1. ማመልከቻ ደብዳቤ፣
2. ግለ ታሪክ('CV')፣ 
3. የትምህርትና የሥራ/አመራርነት ልምድ (በሰው ሀብት አስተዳድር ልማት ቢሮ የረጋገጠ) ማስረጃ ፎቶ ኮፒ  እንዲሁም
4. ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጅያዊ ዕቅድ
በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ድሬክተር ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 

የመመዝገቢያ ቦታ 
==========
ጥበበ ግዮን ካምፓስ
ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ 
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

Public Lecture

ማስታወቂያ

30/08/2015ዓ.ም

ማስታወቂያ/Vacancy/

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዩኒቨርሲቲው ባወጣው አዲስ የመካከለኛ አመራሮች መመደቢያ መመሪያ መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ምክትል የሚድዋይፍሪ አገልግሎት ዲሬክተር (Vice Director, Midwifery Services) ቦታ መሾም ይፈልጋል፡፡

የማወዳደሪያ መስፈርት
----------------------

1ኛ. የትምህርት ደረጃ የመጀመሪያ ዲግሪ/ከዚያ በላይ የትምህርት ደረጃ ያለው/ያላት፣
2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት/ጤና ተቋም፣ በሆስፒታል፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማት በመማር ማስተማር፣ ማህበረሰብ አገልግሎት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በልዩ ልዩ ሀላፊነት እርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከተ/ች ወይም ዉጤት ያመጣ/ያመጣች፣
3ኛ. በሚያመለክቱበት ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የነርስ አግልግሎትን እና ተደራሽነትን፣ ፍትሃዊነት፣ ጥራትን፣ ተገቢነትንና ዓለም አቀፋዊነትን ለማሳካት፣ ኮሌጁን፣ ሆስፒታሉንና ትምህርት ቤቶችን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለም አቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ለማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል አጭር ስትራቴጅያዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/የምትችል፣
4ኛ. ከኮሌጁ የሚሰጠውን ዝርዝር  ሃላፊነት በጥበብ፣ በቅንነት፣ በቁርጠኝነት እና በታማኝነት ተቀብሎ የሚፈፅም፣
5ኛ. የሆስፒታሉ አመራሮች፣ የሆስፒታሉ ማኔጅመንት አባላት፣ ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለፃ መስጠት የሚችል/የምትችል፡፡

አመልካቾች፡- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን (30/08/2015ዓ.ም) ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የትምህርትና የሥራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጅያዊ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዲሬክተር ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

የመመዝገቢያ ቦታ
------------------
ጥበበ ግዮን ካምፓስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዲሬክተር ቢሮ
ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

Friday Seminar

የረቲና ካንሰር ምንድን ነው?

የረቲና ካንሰር (በእንግሊዝኛዉ አጠራር ‹‹ረቲኖብላስቶማ/Retinoblastoma›› በህጻናትና በልጆች ዓይን ላይ የሚከሰት የካንሰር ዓይነት ሲሆን ካንሰሩ የሚጀምረዉ ከረቲና (የዉስጠኛው ዓይን ክፍል) በመሆኑ የረቲና ካንሰር ተብሎ ይጠራል።

ይህ ካንሰር የሚከሰተዉ በ13ኛዉ የዘረ-መል ግንድ (‹‹ክሮሞዞም››) ላይ በሚገኝ ዘረመል ላይ በሚደርስ ጉዳት ነዉ። ዐሥር ከመቶ (10%) የሚሆነዉ የዘረ-መል ጉዳት በቤተሰብ የሚተላለፍ ሲሆን ዘጠና ከመቶ (90%) የሚሆነዉ የዘረ-መል ጉዳት ደግሞ ባልታወቀ ምክንያት በድንገት የሚከሰት ነዉ። ከሚታወቁ የካንሰር አጋላጭ ነገሮች ለምሳሌ ሲጋራ ማጨስ፣ ወዘተ ጋርም ምንም ዓይነት ግንኙነት የለዉም።

የረቲና ካንሰር ችግሩ እንደተከሰተ ብዙም ሳይዘገይ ቢቻል ደግሞ ወዲያዉኑ በምርመራ ታዉቆ ተገቢ ሕክምና ካልተደረገለት ዕይታን ካንሰሩ ወደ ሰዉነት ከተሰራጨ ደግሞ ሕይወትን ያጠፋል።

date: 
Saturday, May 13, 2023 - 23:45

Tibebe Ghion Specialized Hospital holds a workshop to evaluate Antimicrobial stewardship(AMS) interventional outcomes on appropriateness of surgical antibiotics prophylaxis use and surgical site infection prevention practice".

(May 4, 2023, Bahir Dar): Bahir Dar University Tibebe Ghion Specialized Hospital conducted a workshop to evaluate the Mid-term outcome of AMS intervention in collaboration with USAID MTaPS (USAID Medicine, Technology and pharmaceutical service).

The hospital and collaborators evaluated the three month AMS intervention of the hospital which was implemented based on baseline data.

date: 
Friday, May 12, 2023 - 13:15

የዓለም የነርሶች ቀን የተለያዩ ተግባራትን በማከናዎን ተከበረ።

(ግንቦት 4፣ 2015 ዓ.ም፣ባሕር ዳር)፦ የዓለም የነርሶች ቀን በሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተለያዩ የበጎፈቃድ ተግባራትን በማከናዎን በዛሬው እለት ተከበረ።

የኮሌጁ መምሕራንና የአስተዳደር ሰራተኞች በዓሉን ሲያከብሩ ከአከናዎኗቸው ተግባራት መካከል የደም ግፊትና የስኳር ምርመራ እንዲሁም የግቢ ጽዳት ይገኙበታል።

#Dedicated to #excellence #committed to #care!!!

Follow us on:

date: 
Friday, May 12, 2023 - 08:15

Pages

Contact CMHS

College Of Medicine and Health Sciences

Bahir Dar University

 Bahir Dar, Ethiopia

Phone:- +251-0582-9 99275

P.o.box:- 79

e-mail:- collegehealthscience@gmail.com

Institutes

Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2017- Bahir Dar University