EiTEX ወደ ስራ ፈጣሪነት የሚያሸጋግረውን አዲስ ስትራቴጂያዊ ፕሮፖዛል ይፋ አደረገ::
Selam Campus
10 Oct, 2026
EiTEX ወደ ስራ ፈጣሪነት የሚያሸጋግረውን አዲስ ስትራቴጂያዊ ፕሮፖዛል ይፋ አደረገ::
መስከረም 29/2019 ዓ.ም | BDU-EiTEX - በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (EiTEX) ተቋሙን ከባህላዊ የክፍል ትምህርት አሰጣጥ ወደ ስራ ፈጠራና ምርታማነት ለማሸጋገር የሚያስችል የትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂያዊ ፕሮፖዛል ይፋ አደረገ።

ፕሮፖዛሉን የኢንስቲትዩቱ ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር ታምራት ተስፋዬ ያቀረቡት ሲሆን፣ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስ-ገዝነት በሚሸጋገርበት በዚህ ወቅት EiTEX የሰው ኃይል፣ የመሠረተ ልማት እና የቴክኖሎጂ አቅሙን በማስተባበር የራሱን ገቢ ማመንጨት እንደሚጠበቅበት ገልጸዋል።
የስትራቴጂው 5 ዋና ዋና ምሰሶዎች፡
l ስራ ፈጠራን ያካተተ ካሪኩለም፡ ትምህርቱን ከስራ ፈጠራ ጋር ማቀናጀት።
l ሀብትና መሠረተ ልማትን መጠቀም፡ የሰላም ሹራብ፣ የናርጋ ጋርመንት እና የሰላም ቴክስታይል ፋብሪካዎችን ጨምሮ የምርትና የላቦራቶሪ ክፍሎችን ለገቢ ማመንጫነት ማዋል፤ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ተማሪዎችን ቁጥር ማሳደግ።
l ጠንካራ የኢንዱስትሪ ትስስር፡ ከንግድ ተቋማት እና ከቀድሞ ተማሪዎች ጋር አብሮ መስራት።
l የኢንኩቤሽን ማዕከላት፡ ለጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች የድጋፍ እና የሙከራ ሥርዓት ማቋቋም።
l የገበያ ትስስር፡ የተቋሙን ምርቶችና አገልግሎቶች ማስተዋወቅ።
የትግበራ ሂደት (በ3 ዓመታት ውስጥ):-
ይህ ዕቅድ በአራት ደረጃዎች ይተገበራል፡
l የነባራዊሁኔታ ግምገማ
l የስራሞዴሎች ሙከራ
l ውጤታማአሰራሮችን ማስፋፋት
l በተቋማዊ ሥርዓት ውስጥ ማካተት ናቸው።
በውይይቱ ወቅት ከመምህራንና አመራሮች ለተነሱ ጥያቄዎች በፕሮፌሰር ታምራት ተስፋዬና በተባባሪ ፕሮፌሰር አዳነ ኃይሌ ምላሽ የተሰጠ ሲሆን፤ ይህ ተነሳሽነት ኢንስቲትዩቱ ዘላቂ የገቢ ምንጭ እንዲፈጥርና የትምህርት ጥራቱን ከምርት ጋር እንዲያቀናጅ ትልቅ እድል እንደሚከፍት ተመልክቷል።
