ከመተከል ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን ለተደረገ ድጋፍ

“ወገን ቢረዳዳ ችግርም አይጎዳ” የሚለዉን ብሂል ተመርኩዘን የኮሌጃችንን ማኅበረሰብ የድጋፍ መዋጮ በ10/09/2013 ዓ.ም ከቤንሻጉል ጉምዝ ተፈናቅለዉ ቻግኒ ከተማ ለተጠለሉ ወገኖቻችን አስረክበን ተመልሰናል፡፡ በቦታዉ አገላብጠዉ የሚያርሱ አርሶ አደሮች በዚህ ወሳኝ የእርሻ ወቅት ጉልበታቸዉን ታቅፈዉ ተቀምጠው ማየት እጅጉን የሚያም ቢሆንም ጉዳታቸው ጉዳታችን መሆኑን ለማሳየት የተላከዉን ስጦታ በግንባር አስረክበናል፡፡ በዚህም በኮሌጃችን ማህበረሰብ አለሁ ባይነት ኮርተናል፡፡ ሁላችሁም ፈጣሪ ይስጣችሁ ተብላችኃል፡፡ በዚህ አጋጣሚ ይህ ይላክ ዘንድ ያለዕረፍት ላይ ታች ያሉት ወንድሞቻችን አቶ ይበልጣል ኤልያስ (ከማኔጅመንት)፣ አቶ ቴድሮስ ካሳየ (ከማርኬቲንግ)፣ አቶ ካሴ ደሴ (ከኢኮኖሚክስ)፣ አቶ ታፈረ ወርቁ (ከሎጅስቲክስ) እንዲሁም እህታችንን ትርንጎ ድንቁ (ከአካዉንቲንግና ፋይናስ) እንድታመሰግኑልኝ እጠይቃለሁ፡፡ ጉልበታችሁ ይባረክ፡፡

Share