ማዕከሉዓለምአቀፍየኢንተርፕርነርሽፕሳምንትአስመልክቶአውደጥናትአካሄደ

የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ የኢንተርፕርነርሽፕ (የሥራፈጠራ) ልማትና ማበልፀጊያ ማዕከል የዓለም አቀፍየ ኢንተርፕርነርሽፕ ሳምንትን አስመልክቶ የተለያዩ ዝግጅቶችን ያካተተ የአንድቀንዓውደ- ጥናት እና የፈጠራ ስራ ውድድር በዩኒቨርሲቲው የመሰብሰቢያ አዳራሽ አካሄደ፡፡

የፕሮግራሙን የመግቢያ ንግግር ያደረጉት የዩኒቨርሲቲው የእውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር ዶ/ር የሻምበል መኩሪያው ለተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈው ዩኒቨርሲቲው የሰነቀውን ራዕይ ከግብ ለማድረስ በርካታ አኩሪ ተግባራትን እያከናወነ ያለና ባገራችን ውስጥ ካሉ ጠንካራ ዩኒቨርሲቲዎች ጐራ የሚመደብ ሲሆን ከመማር ማስተማሩ፣ ከምርምሩና ከማህበረሰብ አገልግሎቱ ጐንለጐን በኢንተርፕርነርሽፕ ዘርፍም ማዕከል በማቋቋም ልዩ ተሰጥኦና ፍላጐት ያላቸውን የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብም ሆነ የከተማው ነዋሪዎችን በተለያየ መንገድ ድጋፍና ክትትል እያደረገ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አያይዘውም  ዩኒቨርሲቲያችን   በእውቀትና ቴክኖሎጂ በማገዝ እንዲሁም ለኢንተርፕርነርሽፕ ልዩ ትኩረት በመስጠት መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት ጉልህ አስተዋፅኦ እያበረከተ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የኢንተርፕርነርሽፕ ልማትና ማበልፀጊያ ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ወ/ሮ አለምፍሬ ደረሰ የማዕከሉን አመሰራረት ሲገልፁ በቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ መምህራን ተነሳሽነት የዩኒቨርሲቲው የበላይ አመራር ፈቅዶ እንዲሁም በኢትዮጵያ ኢንተርፐርነርሽፕ ልማት ማዕከል እገዛእንደተቋቋመና ዘርፈ ብዙ የሥራ ፈጠራ ተሰጥኦችን በመደገፍና በመከታተል በርካታ ሥራ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ማዕከሉ የተለያዩ ስልጠናዎችን ለተማሪዎች ፤ለመምህራንና አስተዳደር ሰራተኞች እንዲሁም ለማሃበረሰቡ ከመስጠት በተጨማሪ ሥራ የሚፈልጉ ወጣቶችን በማሰልጠንና የቢዝነስ ልማት ማመከር ድጋፍ በማድረግ 27 የሚሆኑ ኢንተርፐራይዞችን በማቋቋም ከ 60 በላይ ለሚሆኑ ወጣቶች ሥራ ፈጥል፡፡   የዓውደ ጥናቱ ዋና ዓላማ ለዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና ከውጭ ለመጡ እንግዶች በአገራችን የኢንተርፕርነርሽፕ ስነ-ምህዳር ያለበትን ሁኔታ፤ለኢንተርፕርነርሽፕ እድገት ስላሉ መልካም አጋጣሚዎች እንዲሁም ፈተናዎች ግንዛቤ ለማስጨበጥ ብሎም አዳዲስ የፈጠራ ስራ ያላቸውን ግለሰቦች አወዳድሮ በመምረጥና ለተመረጡት የፈጠራ ስራዎች ተከታታይ  ድጋፍ በማድረግ የፈጠራውን ባለቤቶች አላማው ለማድረግ ታልሞ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ ዳይሬክተሯ አያይዘውም ከተማሪዎች፤ ከመምህራን እና ከዩኒቨርሲቲው ተመርቀው ከወጡ ግለሰቦች 23 ዓይነት የተለያዩ አዳዲስ የኢንተርፕርነርሽፕ የፈጠራ ፕሮጀክቶች  ለማዕከሉ ቀርበው ከነዚህ መካከል የካበተ ልምድ ባላቸው ሰዎች ተገምግመው አምስቱ በዚሁ አውደ ጥናት ላይ ቀርበው እንዲወዳደሩ እንደተደረገና በውድድሩ ወቅት መቀዳድም እና መበላለጥ ያለ ስለሆነ አሸናፊዎችም ሆኑ ተሸናፊዎች ወደ ማዕከሉ በመቅረብ ተገቢውን ድጋፍ እንደሚያገኙ ተናግረዋል፡፡

የዓውደ ጥናቱ ተሳታፊዎች የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ እንዲሁም በሙያው የካበተ ልምድ ያላቸው ግለሰቦች ሲሆኑ የኢንተርፕርነርሽፕ ስነ-ምህዳር በአገራችን ምን እንደሚመስል የሚያሳይ ጥናታዊ ፅሁፍ ቀርቦ ሰፊ ውይይት በመካሄዱ በሙያው የተካኑት ባለሞያዎች ልምድ ለታዳሚው አካፍለዋል፡፡ በአዉደ ጥናቱም ስኬታማ የሆኑ ስራ ፈጣሪዎች የስራ ፈጠራ ጉዞአቸው ምን እንደሚመስልና  ለስኬት ያበቃቸዉ ቁልፍ ሚስጥር ምን እንደሆነ ገልፀው ከታዳሚው ለተነሱ ጥያቄዎች ጭምር መልስ በመስጠት ልምድ አካፍለዋል፡፡

ተሳታፊዎችም ከአውደ ጥናቱ ብዙ ቁምነገር መቅሰማቸውን ገልፀው ብዙ መሥራት እራስን ከመቻል አልፎ የሌላውንም ትኩረት እንደሚስብ በአንክሮ ተናግረዋል፡፡ በፕሮግራሙ ላይ የተመረጡት አምስቱም የሥራ ፈጠራ ዘርፎች ቀርበው በተመልካቾና በሙያው ጥልቅ እውቀት ባላቸው ሰዎች ተገምግመው ሶስቱ ያለፉ ሲሆን ሁለቱ ጅምራቸው ጥሩ ቢሆንም በፅንሰ-ሀሳብ ደረጃ ላይ ስለሆነ በቀጣይ በደንብ እንዲሰሩና ውጤታማ መሆን እንዲችሉ ከገምጋሚ ዳኞች ማሳሰቢያ ተሰጥቷል፡፡

Share