ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ርቀትና ተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም የአዲስ ተማሪዎች ቅበላ መስፈርት
ባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ርቀትና ተከታታይ ትምህርት ፕሮግራም
የአዲስ ተማሪዎች ቅበላ መስፈርት
እዉቅና ባላቸዉ ፕሮግራሞች የት/ት ሚኒስቴርን እና የዩኒቨርስቲዉን የቅበላ መስፈርቶች/መመሪያዎች በተከተለ መልኩ የተማሪዎች ቅበላ ተደርጎ ጥራት ያለዉ ትምህርት ይሰጣል፡፡
አጠቃላይ መመሪያዎች፡-
ለቅድመ ምረቃ
የብቃት ሰርተፊኬት ለሚያስፈልጋቸው የትምህርት ክፍሎች የብቃት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ
የብቃት ሰርተፊኬት ለማያስፈልጋቸው 2 ዓመት የሥራልምድ
በቀድሞው 12 ክፍል መመዝገብ አይቻልም
ለድህረምረቃ
የመጀመሪያ ዲግሪ ኦርጂናል ማስረጃና ሁለት ፎቶኮፒ
ኦፊሺያል ትራንስክርቢት ከምዝገባ በፊት ቀድሞ መድረስ አለበት፡፡
ማሳሰቢያ
የት/ት ፕሮግራሞችን እና መግቢያ መስፈርቶችን በተመለከተ ማንኛዉም ጥያቄ ካለዎት የተከታታይ እና ርቀት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ሰራተኞችን እንዲሁም የዩኒቨርስቲዉን ሬጅስትራር ባለሞያዎች ያማክሩ፡፡