ለድህረ-ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

Poly Campus

25 Jul, 2025

Event Content

                                ለድህረ-ምረቃ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ 

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ  የባሕር  ዳር  ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት በ2018 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በሁለተኛ ዲግሪ እና በሶስተኛ ዲግሪ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡  ስለሆነም የመግቢያ መስፈርቱን ለሚያሟሉ እና በግል ከፍለው ወይንም በመስሪያ ቤታቸው ስፖንሰር አድራጊነት ከፍለው መማር ለሚፈልጉ አመልካቾች ትምህርት የሚሰጥባቸውን የሙያ መስኮች ከዚህ በታች በተቀመጠዉ ዝርዝር በመመልከት ለምዝገባ ቅድመ ዝግጅት እንድታደርጉ እያሳሰብን ምዝገባዉ በሚጀመርበት ጊዜ Online ማመልከት የሚችሉ መሆኑን እየገለጽን ለምዝገባ መሟላት የሚገባቸውን ዶክመንቶች፤ ለማመልከቻ (application fee) የሚከፈልባቸውን የዩኒቨርሲቲው የባንክ ቁጥሮችን እና የማመልከቻ ፎረሙን ወደ ፊት በሚለቀቀዉ ከማመልከቻ ድረ ገጹ https://studentportal.bdu.edu.et ማግኘት እንደሚችሉ ለማሳሰብ እንወዳለን:: 

#ማሳሰቢያ፤ 

# 1ኛ.  የምዝገባ ጊዜ እና ሁኔታ የNGAT የፈተና ጊዜ እንደተገለጸ የምናሳውቅ ይሆናል። 

#2ኛ. ለ2ኛ እና 3ኛ ድግሪ ተማሪዎች በዩኒቭርሲቲዉ መመሪያ መሰረት የዶርም አገልግሎት እንዲሁም 3ኛ ድግሪ ተማሪዎች የተደራጀ የቢሮ አገልግሎት የምንሰጥ መሆናችንን እናሳውቃለን። 

#3ኛ. አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና (NGAT) ማለፍ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የባሕር  ዳር  ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት  ሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት