news

የዩኒቨርሲቲው ለ2ኛ አመት ተማሪዎች የማህበራዊና ትምህርታዊ ክህሎት ስልጠና ተሰጠ

Campus Name

25 Mar, 2025

የዩኒቨርሲቲው ለ2ኛ አመት ተማሪዎች የማህበራዊና ትምህርታዊ ክህሎት ስልጠና ተሰጠ  

***********************************

ዮንቨርስቲያችን የስራ ተኮር ማስተባበሪያ ማዕከል ከከፍታ(Ameref Health African)  ከሚባል ድርጅት ጋር የተማሪዎች ስራ ተኮር የማማከር አገልግሎት፣ የህይዎት ክህሎትና የስራ ተኮር ቅድመ ዝግጀት ስልጠና መስጠት፣ ለመምህራን ደግሞ የስራ ላይ የአሰልጣኞች ስልጠና እና ስራ ተኮር የማስተማር ስነ-ዘዴ እና ተመሳሳይ ስራዎችን በጋራ ለመስራት በተፈራረመው የስምምነት ውል መሰረት ለ16 መምህራን የአሰልጣኖች ስልጠና እና ለ6 መምህራን ደግሞ ስራ ተኮር የማስተማር ስነ-ዘዴና ስራ ተኮር የማማከር ስልጠና ከተለያዩ ካምፖሶችና ኮሌጆች ለተመረጡ መምህራን ስልጠናው ተሰጥቷል፡፡ መምህራንም ባገኙት ስልጠና መሰረት የመጀመሪያውን ዙር የህይዎት ክህሎት ስልጠና ለግብርና ሳይንስ እና ለሳይንስ ኮሌጅ ማትም ለ80 ተማሪዎች ለ3 ተከታታይ ቀናት(19-21/05/2015 ዓ.ም) የተሰጠ ሲሆን ስልጠናውም ወደፊት በሌሎች ካምፖሶችና ኮሌጆች የሚቀጥል ነው፡፡ የህይዎት ክህሎት ስልጠናው እንዳለቀ ለተመራቂ ተማሪዎች የስራ ተኮር ሙያዊ ስልጠና እና የስራ ላይ ቅድመ ዝግጅት ስልጠና እንደሚቀጥል የስራ ተኮር ስልጠና ይቀጥላል፡፡ የስልጠናው ዋና አላማም ተማሪዎች በትምህርት ቆይታቸው ጤናማ የህይዎት መርህን በማዳበር በትምህርታቸው እንዲሁም ከተመረቁ በኋላ በስራ አለምና በማህበራዊ ህይዎታቸው ስኬታማ ህይዎትንና ስራን እንዲያዳብሩ ይረዳቸዎል፡፡