ለተመረጡ የዩኒቨርሲቲው መምህራንና የተማሪዎች አማካሪዎች የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ

Campus Name

25 Mar, 2025

ለተመረጡ የዩኒቨርሲቲው መምህራንና የተማሪዎች አማካሪዎች የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ

***********************************

(ጥር 05/2015 ዓ.ም፤ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የስልጠና ዳይሬክቶሬትና የውጤታማ ትግበራ ዳይሬክቶሬት በጋራ በመተባበር ከዩኒቨርሲቲው ሁሉም ግቢዎች ለተውጣጡ መምህራንና የተማሪዎች አማካሪዎች (advisors) በራስ የመተማመንና የስራ ፍለጋ ችሎታን የሚያዳብር የአሰልጣኞች ስልጠና ለሁለት ተከታታይ ቀናት በጥበብ ህንፃ የስልጠና አዳራሽ ተሰጠ፡፡

ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የዩኒቨርሲቲው ጠቅላላ ጥራት ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር አንዳርጋቸው ሞገስ እንደገለጹት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን በእውቀት፣ በክህሎትና በአመለካከት ብቁ አድርጎ ለማውጣትና ከሌሎች ተማሪዎች ጋር ሲነፃፀሩ ተመራጭ ሆነው እንዲገኙ ስልጠናው አስፈላጊ ስለሆነ ይህን ስልጠና ለተማሪዎች የሚሰጡ አሰልጣኞች መሰልጠናቸው ይበል የሚያስብል ተግባር መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ዶ/ር አንዳርጋቸው አክለውም ተማሪዎች ከቀለም ትምህርቱ በተጨማሪ በአመለካከትና በራስ መተማመንን አዳብረው ከወጡ ከትምህርቱ ዓለም ወደ ስራው ዓለም ሲቀላቀሉ ለሚያጋጥሟቸው መልካምም ሆነ መጥፎ አጋጣሚዎች እንደማይንበረከኩ አውስተው የግቢዎች የተማሪ አማካሪዎች (advisors) እንደመደበኛ ስራቸው በመቁጠር የተማሪዎችን ድጋፍና ክትትል ዕለት በዕለት መተግበር እንዳለባቸው በመጠቆም ሰልጣኞች ስልጠናውን በነቃ ተሳትፎ እንዲከታተሉ አሳስበዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የውጤታማ ትግበራ ዳይሬክተር ዶ/ር ቀረብህ አስረስ የስልጠናው ዓላማ ተማሪዎች ራሳቸውን እንዲያውቁና በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸውም ይሁን ተመርቀው ሲወጡ ከሌሎች በተሻለ መልኩ ተመራጭ ሆነው እንዲገኙ ታልሞ የተዘጋጀ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር ቀረብህ አክለውም ስልጠናው ለሁለተኛ ዙር እየተሰጠ መሆኑንና ከአሁን በፊት በውስን ባለሙያዎች በዘመቻ መልኩ ይሰጥ የነበረ ሲሆን በዚህ ስልጠና ግን መምህራኖች በየግቢያቸው ከመማር ማስተማሩ ጎን ለጎን ምቹ ጊዜያትን በመምረጥ ከሁለተኛ ዓመት ጀምረው ለሚማሩ ተማሪዎች ስልጠናውን እንዲሰጡ ታስቦ እየሰለጠኑ ስለሆነ የስልጠናው ተደራሽነት ሰፊ እንደሚሆንና ፋይዳውም የጎላ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በተጨማሪም ከየግቢው ያሉ የተማሪዎች አማካሪዎች (advisors) ስልጠናውን መውሰዳቸው የማማከር ክህሎታቸው እንዲጨምርና ተማሪዎች በግቢ ቆይታቸው ራሳቸውን አውቀው ተመርቀው ሲወጡም በየዝንባሌያቸው መስራት እንዲችሉ ሚናው የጎላ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

አሰልጣኞች ለሙያው ቀርብ የሆኑ የዩኒቨርሲቲው ምሁራን ሲሆኑ ሰልጣኞች ከሁሉም የዩኒቨርሲቲው ግቢዎች የተውጣጡ 20 መምህራንና 10 የተማሪዎች አማካሪዎች (advisors) ሲሆኑ ሁሉም በየፊናው ተማሪዎችን ለማብቃት ጥረት ማድረግ እንዳለበት አሳስበዋል።

ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ`

Wisdom at the source of Blue Nile

Thank you for visiting and inviting our Pages!

Thank you for your likes, comments and shares!

ለተጨማሪ መረጃዎች፡-

Facebook፡ https://www.facebook.com/bduethiopia

YouTube፡ https://www.youtube.com/@bduethiopia

Instagram፡www.instagram.com/bduethiopia

TikTok፡ https://www.tiktok.com/@bduethiopia

Telegram፡ https://t.me/bduethiopia

Twitter፡ https://twitter.com/bduethiopia

LinkedIn፡http://www.linkedin.com/school/bduethiopia

Website https://bdu.edu.et/delivery/