ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከእስራኤል ሀገር ከመጡ ከፍተኛ የቀዶ ሕክምና ባለሙያዎች ጋር በመተባበር የሕክምና አገልግሎት እየሰጠ ነው።

23 Oct, 2025

ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ከእስራኤል ሀገር ከመጡ ከፍተኛ የቀዶ ሕክምና ባለሙያዎች ጋር በመተባበር የሕክምና አገልግሎት እየሰጠ ነው።

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በፕሮፌሰር ሐኖች ካሽታን( Professor Hanoch Kashtan) በተመራ ከእስራኤል ሐገር ከመጡ ከፍተኛ የቀዶ ሕክምና ባለሙያዎች ጋር በመተባበር በዘመናዊ መሳሪያ የታገዘ ከፍተኛ የቀዶ ሕክምና (Laparoscopic Surgery) አገልግሎት እየሰጠ ይገኛል።
አገልግሎት ከሚሰጥባቸው ዘርፎች መካከል የሐሞት ጠጠር ቀዶ ህክምና (Laparascopic cholecystectomy)፣ የጉረሮ ካንሰር እና ሌሎች የጉረሮ ህመሞች ቀዶ ህክምና (Esophageal disease and other related pathologies surgery)፣ የጨጓራ ካንሰር እና ሌሎች ተያያዥ የጤና ችግሮች ቀዶ ህክምና (Gastric cancer and other gastric pathologies surgery)፣ የቆሽት፣ የሐሞት ቱቦ እና የጣፊያ ቀዶ ህክምና (Hepatopancreaticobiliary surgery) እና የአንጀት ካንሰር እና ተያያዥ የጤና ችግሮች ቀዶ ህክምና (Colorectal and other related diseases surgery) ይገኙበታል።
በሂደቱም ለታካሚዎች የላቀ የሕክምና አገልግሎት ከመስጠት ባሻገር በሆስፒታሉ ከሚሰሩ ቋሚ የሕክምና ባለሙያዎች ጋር የልምድ ልውውጥ በማድረግ እየተሰጠ ባለው ጥራት ያለው የሕክምና አገልግሎት ላይ ጉልህ አስተዋጾ ይኖረዋል ተብሎ ይታመናል።