የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች የኮቪድ 19 ክትባት በመዉሰድ ሌሎች ሰዎች እንዲከተቡ አበረታቱ።

(ሰኔ 13፣2014 ዓ.ም፣ ባሕር ዳር)፦ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮች የኮቪድ 19 ክትባት በዛሬዉ እለት በጥበበ ግን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በመዉሰድ ሌሎች አመራሮች፣ መምህራን፣ ሰራተኞችና ተማሪዎች እንዲከተቡ አበረታተዋል።

በክትባት ዘመቻዉ የዩኒቨርሲቲዉ ፕሬዝዳንት የተከበሩ ዶ/ር ፍሬዉ ተገኘ፣የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳት ክቡር ዶ/ር እሠይ ከበደ፣ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር ዶ/ር ተስፋየ ሽፈራዉ እና የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮምዩኒኬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት ክቡር ዶ/ር ዘዉዱ እምሩ በመሳተፍ እንደመሪ አርያ የሆነ ተግባር ፈጸመዋል።

የመሪዎችን አርያ በመከተልም ሌሎች የዩኒቨርሲቲዉ በየደረጃዉ የሚገኙ ሁሉም አመራሮች፣ መምህራን፣ ሰራተኞችና ተማሪዎች የከፍተኛ አመራሮችን አርያ ተከትለዉ የኮቪድ 19 ክትባት በመዉሰድ ራሳቸዉንና ወገናቸዉን ከበሽዉ በመታደግ የበኩላቸዉን ድርሻ ይወጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከ12 ዓመት እና ከዚያ በላይ ለሆናቸው ሰዎች የሚሰጠዉ የኮቪድ-19 ክትባት ከሰኔ 11 ጀምሮ በሆስፒታሉ እየተሰጠ የሚገኝ ሲሆን ክትባቱ በሽታ የመከላከል አቅማችዉን በማጎልበት ከህመምና ሞት ይታደጋል። በዚያዉ ልክ ለሌሎች ሰዎችም እንዳያስተላልፉ ይከላከላል፡፡

#Dedicated to #excellence #committed to #care!!!

Follow us on:

Facebook: https://www.facebook.com/cmhsbdu/
Website: http://www.bdu.edu.et/cmhs/
Telegram: https://t.me/Information-office-CMHS-BDU

date: 
Monday, June 20, 2022 - 08:45

Contact CMHS

College Of Medicine and Health Sciences

Bahir Dar University

 Bahir Dar, Ethiopia

Phone:- +251-0582-9 99275

P.o.box:- 79

e-mail:- collegehealthscience@gmail.com

Institutes

Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2017- Bahir Dar University