የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የ2014 ዓ.ም የ9 ወር የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ እያካሄደ ነዉ።

(ሚያዝያ 19፣2014 ዓ፣ም፣ባሕር ዳር)፦ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የ2014 ዓ.ም የ9 ወር የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ እያካሄደ ነዉ።

ግምገማዉ እየተካሄደ ያለዉ በአለፉት ወራት የነበሩትን ጠንካራ ጎኖች አጠናክሮ ለማስቀጠል እንዲሁም ደካማ እና ልዩ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን በጊዜ በመለየት በመቀጣዩ ሩብ ዓመት በማሻሻል የበጀት ዓመቱን በስኬት ለማጠናቀቅ ያስችላል በሚል እምነት ነዉ።

ኮሌጁ ግምገማዉን የጀመረዉ በአካዳሚክና ምርምር ዘርፍ የስራ ክፍሎች ሲሆን በዛሬዉ እለትም የኮሌጁ ሁሉም ትምሕርት ቤቶች ማለትም የሕክምና ትምሕርት ቤት፣ የሕብረተሰብ ጤና ትምሕርት ቤት እና የጤና ሳይንስ ትምሕርት ቤት እንዲሁም የሬጂስትራርና አሉሙናይ እና የማሕበረሰብ አቀፍ አገልግሎት ዳይሬክቶሬቶችን የስራ አፈጻጸም ገምግሟል።

ግምገማዉ በነገዉ እለትም የሚቀጥል ሲሆን የድሕረምረቃና ተከታታይ ትምሕርት፣ ምርምርና ስርጸት፣ የቤተመጽሐፍት፣ ኢንፎርሜሽንና ኮሚዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ዳይሬክቶራቶችና እና የአመራር ማበልጸጊያ ፕሮግራም የ9ወር የእቅድ አፈጻጸማቸዉን የሚገመግሙ ይሆናል።

#Dedicated to #excellence #committed to #care!!!

Follow us on:

Facebook: https://www.facebook.com/cmhsbdu/
Website: http://www.bdu.edu.et/cmhs/
Telegram: https://t.me/Information-office-CMHS-BDU
Twitter: https://twitter.com/CollegeBdu?s=20

date: 
Tuesday, April 19, 2022 - 10:15

Contact CMHS

College Of Medicine and Health Sciences

Bahir Dar University

 Bahir Dar, Ethiopia

Phone:- +251-0582-9 99275

P.o.box:- 79

e-mail:- collegehealthscience@gmail.com

Institutes

Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2017- Bahir Dar University