የሕክምና ትምሕርት ቤት የአመራርነት ስልጠና እየሰጠ. ነው።

“ሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዉስጥ የምንሰራዉ ለመኖር አይደለም፤ልዩነት ለመፍጠር እንጅ።” ፕሮፌሰር የሺጌታ

(የካቲት 25፣ 2014 ዓ.ም ፣ባሕር ዳር)፦ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የሕክምና ትምሕርት ቤት ለትምህርት ቤቱ አባላት የአመራርነት ስልጠና እየሰጠ ነዉ፡፡ የስልጠናዉ ዋና አላማ በኮሌጁ የ10 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ ዉስጥ የተካተቱትን ራዕይ እና ተልዕኮዎች ማስተወዋወቅና የጋራ ማድረግ ነው።

ስልጠናዉን በንግግር የከፈቱት የኮሌጁ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር ፕሮፌሰር የሽጌታ ገላዉ ሲሆኑ በንግግራቸዉም የአደጉ አገሮች የትኩረት ደረጃቸዉ ሕዋ ሳይንስ፣ ጄኔቲክ ኤንጂኔሪንግ እና አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ላይ ሲደርስ እኛ ኢትዮጵያዉያን ደግሞ ገና ከእጅ ወደ አፍ ኢኮኖሚ ላይ ስለሆነ ሁኔታዉን ለማሻሻል ከምሁራን ክፍተኛ ድርሻ እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።

ፕሮፌሰሩ አክለዉም የሀገራችን አርሶ አደሮች ልጆቻቸዉን በማስተማር ምሁራንን በማፍራት የበኩላቸዉን ድርሻ የተወጡ መሆኑን በመግለፅ ምሁራን ግን የአርሶ አደሮችን ምርት ከመጠቀም የዘለለ የጎላ አተዋፅኦ ሲያበረክቱ እንደማይታይ አገራችን ያለችበት የድህነት ደረጃ ሊያመላክት እንደሚችል ተናግረዋል። ምሁሩ የአገራችንን ዘርፈ-ብዙ ችግሮች ለመቅረፍ የበኩሉን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ከማበርከት ይልቅ ከአልተማረዉ ማህበረሰብ ጋር አብሮ ስለችግሮች ማዉራት እንደማይጠበቅ ፕሮፌሰሩ አብራርተዋል።ፕሮፌሰሩ መልክታቸዉን በምሳሌ ሲያስረዱ “የዘመድ ቄስ፣እየፈታ ያለቅስ” እንደሚባለዉ ከምሁር የሚጠበቀዉ ቢያንስ የራሱን የቤት ስራ እተወጣ እንደሆነ ተናግረዋል።

ከአለንበት ሁኔታም የሚያላቅቀን የእኛ መልካም ስራ እንጂ የበለጸጉት አገራት እንዳልሆነ በመረዳት እስካሁን ስለሆነዉ ነገር ሁሉ እና የሚጠበቅብንን ስላተወጣን በቁጭት፣ በቁርጠኝነት፣ በተግባር በመስራት እና ፈተናወችንን በመቋቋም በርትተን መስራት እንደሚገባ በማስገንዘብ የአመራር ስልጠናዎች አላምም እነዚህን ነገሮች ማድረግ እንድንችል ማስቻል እንደሆና ዋና ስራ አስፈጻሚ ዳይሬክተሩ አብራርተዋል።

ስራዎችን በዘፈቀደ በመስራት ለስኬት ስለማያበቃ ኮሌጁ ሊተገበር የሚችል እና በስራ ሂደትም ተግባራዊነቱ የታዬ የ10 ዓመት ስትራጂክ እቅድ በማዘጋጀት እየሰራ እንደሆነ በመጥቀስ ሁሉም የስራ ክፍሎች የየራሳቸዉን እቅድ አዘጋጅተዉ መስራት እንደሚገባ ፕሮፌሰሩ አሳስበዋል።

የኮሌጁን የ10 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ እና የ3 ዓመት ስትራቴጅካዊ ተግባራት እድገት የሕክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአካዳሚክና ምርምር ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር መለሰ ገበየሁ ለተሳታፊዎች አቅርበዋል።

ከሳምንታት በፊት ለከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ከተሰጠዉ የአመራርነት ስልጠና የቀጠለና አላማዉም ሁሉንም የትምሕርት ቤቱ አባላት በማሳተፍ ብቁ ለማድረግ ከኮሌጁ የአመራር ማበልጸጊያ ማዕከል ጋር በጋራ በመተባበር የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን የሕክምና ትምህርት ቤት ዲን ዶ/ር በቃሉ ዉብሸት ተናግረዋል።

በተለያዩ ወቅቱን በዋጀ የአመራነት ርዕሶች ጉዳይ ላይም የኮሌጁ የአመራር ማበልጸጊያ ማዕከል ዳሬክተር ዶ/ር የሻምበል አጉማስ የሚሰጥ ይሆናል።

date: 
Friday, March 4, 2022 - 02:00

Contact CMHS

College Of Medicine and Health Sciences

Bahir Dar University

 Bahir Dar, Ethiopia

Phone:- +251-0582-9 99275

P.o.box:- 79

e-mail:- collegehealthscience@gmail.com

Institutes

Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2017- Bahir Dar University