በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እስራኤል ሀገር ከሚገኘዉ ራቢን ህክምና ማዕከል (Rabin Medical Center) በሊንሰን ሆስፒታል(Belison Hospital) ጋር በመተባበር በስፔሻሊስትና ድኅረ-ስፔሻሊስት ሐኪሞች ከመስከረም 12, 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አራት (4) ቀናት በሚከተሉት የጤና ችግሮች ማለትም:-
1. የጉሮሮ ካንሰር
2. የጨጓራ ካንሰርና ሌሎች የጨጓራና የአንጀት በሽታዎች/ህመሞች/
3. የሐሞት ጠጠር: የጉበት እጢና ተያያዥ በሽታዎች/ህመሞች/
የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ይሰጣል:: ስለሆነም ችግሩ ያለባችሁ ሰዎች ወደ ሆስፒታላችን በመምጣት ከመስከረም 7-9 ባሉት የስራ ቀናት ቅድመ ምርመራ በማድረግና ለቀዶ ህክምና ተራ (ወረፋ) በመያዝ የእድሉ ተጠቃሚ እንድትሆኑ ጥሪዉን ያቀርባል::
Bahir Dar University
Bahir Dar, Ethiopia
Phone:- +251-0582-9 99275
P.o.box:- 79
e-mail:- collegehealthscience@gmail.com
Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2017- Bahir Dar University