ክፍት የኅላፊነት ቦታ ማስታወቂያ (vacancy)

18/04/2016 ዓ.ም 

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዩኒቨርሲቲው ባወጣው አዲስ የመካከለኛ አመራሮች መመደቢያ መመሪያ መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ የጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የቀዶ ሕክምና አገልግሎት ዳይሬክተር (Director, Operations Services) ቦታ መተካት ይፈልጋል፡፡

የማወዳደሪያ መስፈርት
=============

1ኛ. የትምህርት ደረጃ  ስፔሻሊስት ሐኪምና ረዳት ፕሮፌሰር እና ከዚያ በላይ ማዕረግ ያለው/ያላት፣ 
2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በሆስፒታልና መሰል ተቋማት፣ በምርምር ተቋማት በመማር ማስተማር፣ ማኅበረሰብ አገልግሎት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በልዩ ልዩ ኃላፊነት እርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከተ/ች፣ 
3ኛ. በሚያመለክቱበት ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የጤና አገልግሎትን ተደራሽነት፣ ፍትሃዊነት፣ ጥራትንና ደኅንነት፣ ተገቢነትና ዓለም አቀፋዊነትን ለማሳካት፣ ኮሌጁንና ሆስፒታሉን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለም አቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ለማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል አጭር ስትራቴጅያዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/የምትችል፣ 
4ኛ. ከኮሌጁና ሆስፒታሉ የሚሰጠውን ዝርዝር ኃላፊነት በቅንነት በትጋትና በታማኝነት ተቀብሎ የሚፈፅም፣
5ኛ. የኮሌጁ አመራሮች፣ የሆስፒታሉ ማኔጅመንት አባላትና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለፃ መስጠት የሚችል/የምትችል፡፡

አመልካቾች፡- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን (18/04/2016 ዓ.ም) ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የትምህርትና የሥራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጅያዊ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዋና ሥራ አሥፈጻሚ ዳይሬክተር ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

የመመዝገቢያ ቦታ
==========
ጥበበ ግዮን ካምፓስ
ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

date: 
Tuesday, January 9, 2024 - 06:45

Contact CMHS

College Of Medicine and Health Sciences

Bahir Dar University

 Bahir Dar, Ethiopia

Phone:- +251-0582-9 99275

P.o.box:- 79

e-mail:- collegehealthscience@gmail.com

Institutes

Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2017- Bahir Dar University