በአምባሳደር ኢንጂኔር ዶ/ር ስለሽ በቀለ የተመራ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን ጎበኘ።

(ጥር 24፣ 2014 ዓ.ም፣ ባሕር ዳር)፦በበአምባሳደር ኢንጂኔር ዶ/ር ስለሽ በቀለ የተመራ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታልን በዛሬው እለት ጎበኘ።

የስራ አመራር ቦርድ አባላት የግቢውን አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ በተለይም ደግሞ የሕክምና ኦክስጅን ማምረቻ ፋብሪካን፣ የፈሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ማሽንን፣ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ማሽንን፣ የሕሙማን መጠጥ ዉሃ ማጣሪያ ማሽንን፣ የልብስ ማጠቢያ ማሽንን፣ የሕሙማን ምግብ ማብሰያን፣ ራዲዮሎጅ ክፍልን እንዲሁም የሕክምና ምርምር ላቦራቶሪን ጎብኝተዋል።

በጉብኝታቸውም ጥበበ ግዮን ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሰራቸው እና እያጠናቀቃቸው የሚገኙ ፕሮጀክቶች እጅግ ይበል የሚያሰኙ መሆናቸውን የቦርዱ ሊቀመምበር ዶ/ር ኢንጂኔር ስለሽ በቀለ ተናግረዋል።

አምባሳደሩ አክለውም ሆስፒታሉ እያከናወናቸው ያሉት ተግባራት አስደናቂና ለሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም አርያ የሚሆኑ መሆናቸውን ገልጸዋል።

date: 
Wednesday, February 2, 2022 - 21:30

Contact CMHS

College Of Medicine and Health Sciences

Bahir Dar University

 Bahir Dar, Ethiopia

Phone:- +251-0582-9 99275

P.o.box:- 79

e-mail:- collegehealthscience@gmail.com

Institutes

Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2017- Bahir Dar University