1/02/2014ዓ.ም
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዩኒቨርሲቲው ባወጣው አዲስ የመካከለኛ አመራሮች መመደቢያ መመሪያ መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ በረጅስትራርና አሉምናይ ዳይሬክተር (Director, Registrar and Alumni Management Directorate) ቦታ መተካት ይፈልጋል፡፡
የማወዳደሪያ መስፈርት
-----------------------------
1ኛ. የትምህርት ደረጃ ረዳት ፕሮፌሰር እና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት፣
2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማት በመማር ማስተማር ፣ማህበረሰብ አገልግሎት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በልዩ ልዩ ሀላፊነት እርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከተ/ች፣
3ኛ. በሚያመለክቱበት ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የከፍተኛ ትምህርትን ተደራሽነት፣ ፍትሃዊነት፣ ጥራትን፣ ተገቢነትና ዓለም አቀፋዊነትን ለማሳካት ፣ ኮሌጁን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ የተማሪ መረጃ አየያዝና ጥራት፣ የአሉምናይ ተሳትፎን ማሳደግና ዉጤታማነት መጨመር እንዲሁም ዓለም አቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ለማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል አጭር ስትራቴጅያዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/የምትችል፣
4ኛ. ከኮሌጁ የሚሰጠውን ዝርዝር ሃላፊነት በቅንነትና በታማኝነት ተቀብሎ የሚፈፅም፣
5ኛ. የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አባላት፣ የኮሌጁ ሴኔት አባላትና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለፃ መስጠት የሚችል/የምትችል፡፡
አመልካቾች፡- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን (01/02/2014ዓ.ም) ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የትምህርትና የሥራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጅያዊ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአካዳሚክና ምርምር ዋና ዳይሬክተር ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
የመመዝገቢያ ቦታ
----------------------
ጥበበ ግዮን ካምፓስ የአካዳሚክና ምርምር ዋና ዳይሬክተር ቢሮ
ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
Bahir Dar University
Bahir Dar, Ethiopia
Phone:- +251-0582-9 99275
P.o.box:- 79
e-mail:- collegehealthscience@gmail.com
Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2017- Bahir Dar University