ማስታወቂያ/Vacancy/

1/02/2014ዓ.ም

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዩኒቨርሲቲው ባወጣው አዲስ የመካከለኛ አመራሮች መመደቢያ መመሪያ መሰረት ብቁ አመልካቾችን አወዳድሮ የኅብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት ዲን (Dean, School of Public Health) ቦታ መተካት ይፈልጋል፡፡

የማወዳደሪያ መስፈርት
----------------------------
1ኛ. የትምህርት ደረጃ ረዳት ፕሮፌሰር እና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት፣
2ኛ. በከፍተኛ ትምህርት ተቋም፣ በኢንዱስትሪ፣ በምርምር ተቋማት በመማር ማስተማር ፣ማህበረሰብ አገልግሎት ወይም መሰል ተልዕኮ ባላቸው ተቋማት በልዩ ልዩ ሀላፊነት እርከን ያገለገለ/ችና ጉልህ አስተዋፅኦ ያበረከተ/ች፣
3ኛ. በሚያመለክቱበት ዘርፍ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ የከፍተኛ ትምህርትን ተደራሽነት፣ ፍትሃዊነት፣ ጥራትን፣ ተገቢነትና ዓለም አቀፋዊነትን ለማሳካት፣ ኮሌጁንና ት/ቤቱን የልህቀት ማዕከል ለማድረግ፣ ተጨማሪ ሀብት ለማስገኘት፣ እንዲሁም ዓለም አቀፋዊና አገራዊ ጉድኝቶችን ለመፍጠርና ለማስፋት በሚደረገው ሂደት አስተዋጽኦ ለማበርከት የሚያስችል አጭር ስትራቴጅያዊ ዕቅድ ማዘጋጀትና ማብራሪያ መስጠት የሚችል/የምትችል፣
4ኛ. ከኮሌጁ የሚሰጠውን ዝርዝር ሃላፊነት በቅንነትና በታማኝነት ተቀብሎ የሚፈፅም፣
5ኛ. የኮሌጁ አመራሮች፣ የኅብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት አባላት፣ የትምህርት ቤቱ የአካዳሚክ ጉባዔ አባላትና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ተጋብዘው በሚገኙበት መድረክ በአጀንዳዎች ላይ በአካል ተገኝቶ/ታ ማብራሪያና ገለፃ መስጠት የሚችል/የምትችል፡፡
አመልካቾች፡- ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን (01/02/2014ዓ.ም) ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የትምህርትና የሥራ ልምዳቸውን ማስረጃ ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ያዘጋጁትን ከአምስት ገጽ ያልበለጠ ስትራቴጅያዊ ዕቅድ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ የህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአካዳሚክና ምርምር ዋና ዳይሬክተር ቢሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

የመመዝገቢያ ቦታ
----------------------
ጥበበ ግዮን ካምፓስ የአካዳሚክና ምርምር ዋና ዳይሬክተር ቢሮ
ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

Contact CMHS

College Of Medicine and Health Sciences

Bahir Dar University

 Bahir Dar, Ethiopia

Phone:- +251-0582-9 99275

P.o.box:- 79

e-mail:- collegehealthscience@gmail.com

Institutes

Website Design and Developed by LTTU,ICT Copyright © 2017- Bahir Dar University