ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሴቶች የልብስ ዲዛይን እና ስፌት ስልጠና እየተሰጠ ነው
Selam Campus
02 Dec, 2025
ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ሴቶች የልብስ ዲዛይን እና ስፌት ስልጠና እየተሰጠ ነው
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በአፓራል ፋካሊቲ ከአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ እና ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሴቶች ህፃናት እና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ለመጡ ዝቅተኛ ደመወዝ ተከፋይ 20 ሴት ሠራተኞች ለሦስት ወራት የሚቆይ የልብስ ዲዛይን እና ስፌት ስልጠና እየተሰጠ ነው፡፡

ይህ ስልጠና በዝቅተኛ ገቢ ለሚተዳደሩ ሴት ሠራተኞች የግል ሥራቸውን በመፍጠር ተጨማሪ ገቢ እንዲገኙ የሚያግዝ እንደሆነ የስልጠናው የአፓሬል ፋኩሊቲ ፋሲሊቲ ማናጀርና የስልጠናው አስተባባሪ አቶ ንጉሴ መኳንንት ገልጸዋል፡፡

ይህ ስልጠና ለሦስተኛ ዙር እየተሰጠ ሲሆን ስልጠናውም በሳምንት ሦስት ቀን፣ በቀን ለ4 ሰዓት የሚሰጥ ተግባር ተኮር ስልጣና ሆኖ ለመግቢያ የሚሆን ንድፈ ሀሳብ እንደሚሰጥ ተገልጿል።
ከዚህ በፊት የተለያዩ አጫጭር ስልጠናዎችን በማህበረሰብ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየ ቢሆንም አሁን ማንኛውም ፍላጎት ያለው አካል በተመጣጣኝ ክፍያ ስልጠናውን በመውሰድ የተጨማሪ ሙያ ባለቤት መሆን እንደሚችልና የግል ገቢንም ማሳደግ የሚያስችል ስልጣና መሆኑን የአፓሬል ፋኩሊቲ ፋሲሊቲ ማኔጀርና አሰልጣኝ አቶ ንጉሴ መኳንንት ገልጸዋል።