bit

የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና የቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

Poly Campus

09 Oct, 2024

Event Content

                                                  የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና የቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ
                                                                [ሚያዝያ 10/2014 ዓ.ም፣ ባህር ዳር - ኢስኮ/ባቴኢ]
በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንሰቲትዩት እና ቡሬ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ መካከል በጋራ ለመሥራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ የመግባቢያ ስምምነቱ ኢንዱስትሪዎችን ከማገዝ አንጻር በጋራ ለመሥራት ያለመ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የኢንስቲትዩቱ የም/ማ/አ/ም/ሳ/ዳይሬክተር ዶ/ር መኳንንት አገኘሁ እና የኮሌጁ ዲን አቶ አስጨንቅ ካሳ ተቋማቱን ወክለው ተፈራርመዋል፡፡ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ወቅት ዶ/ር መኳንንት እንዳሉት የትምህርት ተቋማቱ ወደ ኢንዱስትሪው ከመሄድ ባሻገር ተማሪዎችን በሥራ ክህሎት እና የፈጠራ ሙያ ከማብቃት ጀመሮ ማሕበረሰብ ተኮር ሥራ ለመስራት ኢንዱስትሪዎች የሚገጥሟቸውን እክሎች እና ችግሮች ወደ ተቋማቱ በማምጣት አብረው መሥራት ተመራጭ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ አቶ አስጨንቅ ካሳ በበኩላቸው ኮሌጁ ተግባር ተኮር ትምሕርቶችን ከማስተማር ባለፈ የቡሬ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ጋር እየሠራ መሆኑን ጠቁመው ከባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ጋር ሲሠራ የነበረውን ፕሮጀክቶች ወደላቀ ደረጃ እንዲመጣ ለማድረግ እና ኢንዱስቲሪያል ፓርኮቹን በጋራ ለማገዝ ስምምነቱ ጉልህ ድርሻ እንደሚኖረው ጠቁመዋል፡፡ በፊርማ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ኮሌጁን ወክለው የተገኙት ዶ/ር ዋለ ፍሬው በበኩላቸው ኮሌጃቸው ከዚህ በፊት Job Fair ማካሄዱን ጠቁመው የተሻለ ሲኬት እንዲመጣ የጋራ ተጠቃሚነትን መርህ ያደረገ ስምምነት መፈፀሙን አወድሰዋል። ይህም ኢንዱስትሪው የሚፈልገውን የሰው ኃይል ከማሟላት አንጻር ጉልህ ድርሻ እንዲኖረው ያደርጋል። ከዚህም ጋር ተያይዞ ታሕሳስ መጨረሻ ያዘጋጁትን የ Job Fair ሪፖርት ለባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንሰቲትዩት ያቀረቡ ሲሆን ተማሪዎችን ከማብቃት አንጻር CDC ጋር ለመሥራትም ሃሳብ እንዳላቸው ከገለጻው መልስ በነበረው የውይይት ወቅት ተጠቁሟል።
የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት
ፌስቡክ፡- www.facebook.com/bitpoly 
ቴሌግራም፡- https://t.me/bitpoly 
ዌብሳይት፡- https://bit.bdu.edu.et

bitbit