ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ

Campus Name

14 Oct, 2024

ለትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
-------------------------------
የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ የትምህርት ኮሌጅ በኖርዌይ የልማትና ትብብር ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ ባስጀመራቸው በስነ ትምህርት ማስትሬት ዲግሪ በሒሳብ ስነ ማስተማር (MED in Educational Sciences: Teaching of Mathematics) እና በስነ ትምህርት ማስትሬት ዲግሪ በሳይንስ ስነ ማስተማር (MED in Educational Sciences: Teaching of Science Subjects) ፕሮግራሞች በ2017 ዓ.ም. አመልካቾችን ተቀብሎ ለማስተማር ይፈልጋል፡፡ 
አመልካቾች 
1.  የሁለተኛ ዲግሪ ለመማር በትምህርት ሚኒስቴር የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና (Graduate Admission Test) ተፈትነው ማለፍ ይኖርባቸዋል  
2.  በባዮሎጅ፣ በኬሚስትሪ፣ በፊዚክስ እና በሂሳብ ትምህርት መስኮች የመጀመሪያ ዲግሪ ወይንም የሁለተኛ ዲግሪ ያላቸውና የማስተማር ልምድ ያላቸው ማመልከት ይችላሉ 
3.  በፕሮግራሞቹ ተቀባይነት ለሚያገኙ አመልካቾች ከመኖሪያ ወጭ ውጭ ለዩኒቨርስቲው የሚከፈለው የትምህርት ክፍያ (Tuition fee) እና የምርምር ገንዘብ በፕሮጀክቱ የሚሸፈንላቸው ሲሆን መጠነኛ የሆነ ወርሃዊ የኪስ ገንዘብም ይታሰብላቸዋል፡፡

አመልካቾች እስከ ጥቅምት 8 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ በዩኒቨርስቲው የማመልከቻ ድረ ገጽ https://studentportal.bdu.edu.et/ ማመልከት ይኖርባቸዋል፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ፤ ትምህርት ኮሌጅ