2ኛው የታዳጊ ህፃናት ፕሮጀክት ዓመታዊ የምዘና ውድድር

2ኛው የታዳጊ ህፃናት ፕሮጀክት ዓመታዊ የምዘና ውድድር ተጠናቀቀ

[ጳጉሜ 04/2014 ዓ/ም፤ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባዳዩ] 

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በባሕር ዳር እና አካባቢው የሚገኙ የታዳጊ ስፖርት ፕሮጀክቶች የሚሳተፉበት 2ኛው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የታዳጊ ህፃናት ዓመታዊ ምዘና ከነሐሴ 22 እስከ ጳጉሜ 3 በተለያዩ የስፖርት አይነቶች ሲካሄድ የቆየው ውድድር ተጠናቀቀ ፡፡

ውድድሩ በእግር ኳስ፣ በሜዳ ቴንስ እና በባድሜንተን ሲደረግ፤ 15 የእግር ኳስ ፕሮጀክት ክለቦችን በማሳተፍ ከፍተኛ ፉክክር ተደርጎበታል፡፡ በዚህም የተመልካችን ስሜት የገዛው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ ከ16ዓመት በታች የወንዶች እግር ኳስ ቡድን እና የአሀዱ እግር ኳስ ፕሮጀክት ቡድን የዋንጫ ጨዋታ አድርገው የአሃዱ ቡድን የባሕር   ዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ እግር ኳስ ፕሮጀክት አቻውን  2ለ1 በማሸነፍ ለ2ኛው የታዳጊ ህፃናት ፕሮጀክት ውድድር የተዘጋጀውን ዋንጫ አንስቷል፡፡በዕለቱ የተዘጋጀውን የፀባይ ዋንጫ የሰባታሚ ፕሮጀክት እግር ኳስ ሰፖርት ቡድን መውሰድ ችሏል፡፡

በውድድሩ ለደረጃ የተጫወቱት አደይ አበባ እና ልደታ የህፃናት ፕሮጀክት ቡድኖች ሲሆኑ አደይ አበባ ተጋጣሚውን 5ለ1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡

በእግር ኳስ ጨዋታው ጠንካራ ተወዳዳሪ የነበረው የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ ከ16 ዓመት በታች የወንዶች እግር ኳስ ቡድን 2ኛ በመውጣት የብር መዳሊያ፣ 3ኛ የወጣው አደይ አበባ ፕሮጀክት ስፖርት ቡድን የነሐስ ሜዳልያ ወስደዋል፡፡

በጨዋታው ከተመልካች እና ከስፖርት ባለሙያዎች በተሰበሰበ መረጃ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ ከ16    ዓመት በታች ወንዶች እግር ኳስ ቡድን ኮከብ አጥቂ እና ኮከብ ግብ ጠባቂ ተጫዋቾችን ሲያስመርጥ፤ የዕለቱ ኮከብ   ተጫዋች ከአሀዱ የፕሮጀክት ቡድን ተመርጧል፡፡

መርሃ ግብሩ በቆየባቸው ከነሐሴ 22 እስከ ጳጉሜ 3/2014 ዓ.ም ጉልህ አስተዋፆ ላበረከቱ የስፖርት ቤተሰቦች ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች እና ከፍተኛ ባለሙያዎች እጅ የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል፡፡