ፕሮፌሰር ማሞ ሙጨ ህዝበ ገለፃ አደረጉ

ፕሮፌሰር ማሞ ሙጨ ህዝበ ገለፃ አደረጉ

በኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት  አጋጅነት “ ኢትዮጵያዊነትና የፈጠራ ስራዎች ማዘመን ” በሚል ርዕሰ ፕሮፌሰር ማሞ ሙጨ የኢንስቲትዩቱ  ተማሪዎች፣ መምህራን እና ተጋባዥ አንግዶች በተገኙበት ህዝበ ገለፃ አደርገዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ሣይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ታምራት ተስፋዬፕሮፌሰር ማሞ ሙጨ እና ለዕለቱ ታዳሚዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር በማቅረብ ተተኪ ትውልዶችን በዕውቀት ለማፍራት ይህን መሰል ፕሮግራሞች እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡ 

ፕሮፌሰር ማሞ ኢትዮጵያንዝም ፍልስፍና ላሁኗ ኢትዮጵያ ጥቅሙ ምንድን ነው፣ ኢትዮጵያንዝም ምንድን ነው፣ እኛ ኢትዮጵያኖች ስለ ኢትዮጵያንዝም እናውቃለን አናውቅም፣ ኢትዮጵያንዝም በአለም መድረኮች ያመጣቸው ለውጦች ምንድን ናቸው፣ ፍልስፍና ለአዲስ ባህሪያዊ ለውጦች እንዴት መጠቀም እንችላለን የሚሉ ጉዳዮችን አንስተው ውይይት ተደርጎባቸውል፡፡

ያለን ትምህርት እና እውቀት ከማናውቀው ነገር ጋር ሲወዳደር ኢምንት ነው ፤ ተማሪ መሆን ያቆመ ተማሪ ሆኖ አያውቅም የሚሉ ኃይለ ቃላትን በማንሳት እና ሰፊ ፍልስፍናዊ ገለፃን በማድረግ አነቃቂ አስተያየታቸውን አቅርበዋል፡፡

ፕሮፌሰሩ አያይዘውም ወጣቱ ትውልድ በቋንቋ እና በሐይማኖት ሳይከፋፈል የአባቶቻችን ፈለግ ተከትሎ የተሻለች ኢትዮጵያን በመገንባቱ ሂደት ጉልህ አስተዋፅኦ እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡