'ድንግሌን' መፅሐፍ ምረቃ

ድንግሌን መፅሐፍ ተመረቀ

*************************

[ነሐሴ 13/2014ዓ/ም፤ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ-ባዳዩ] የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሂዩማኒቲስ ፋኩልቲ ከባህል ማዕከል ጋር በመተባበር በመምህር ስንታየሁ ገብሩ ተፅፎ ለንባብ የበቃው ድንግሌን ልቦለድ መፅሀፍ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እና ታዋቂ አርቲስቶች በተገኙበት በዩኒቨርሲቲው ጥበብ አዳራሽ በድምቀት ተመርቋል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል ዳይሬክተር ዶ/ር አስቴር ሙሉ እንደገለጹት የባህል ማዕከሉ ኪነ-ጥበብን መሳሪያ አድርጎ ዩኒቨርሲቲውንና ከዩኒቨሪሲቲው ውጭ ያለውን ማህበረሰብ ለማስተማር እየተጋ ያለ ተቋም ነው ብለዋል፡፡

ተቋሙ በስነ-ጽሁፍ፤ በቲያትር፤ በሙዚቃ፤ በሙዚየም አስተዳደር፤ ስዕልና ቅርጻቅርጽ ስራዎች ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ ተማሪዎችና የአካባቢው ወጣቶች የኪነ ጥበብ ተሰጧአቸውን እንዲፈልጉና እንዲያሳድጉም እገዛ እያደረገ እንደሚገኝ ዶ/ር አስቴር ተናግረዋል፡፡

ዶ/ር  አስቴር አክለውም የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል ለኪነ ጥበብ ስራዎች እውቅና እንደሚሰጥ በመግለፅ በእለቱ እየተካሄደ ያለው በመምህር ስንታየሁ ገብሩ የተደረሰው ድንግሌን የተሰኘው መፅሐፍ ከብዙዎች አንዱ መሳያ መሆኑን በመጠቆም ደራሲውን እንኳን ደስ አለህ ብለዋል፡፡ አርቲስት ስለሺ ደምሴና ደራሲና ጋዜጠኛ ዘነበ ወላም በመጽሀፍ ምርቃ ፕሮግራሙ ላይ በመገኘታቸው ዶ/ር አስቴር ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የምረቃ ፕሮግራሙን የከፈቱት የሂዩማኒቲስ ፋኩልቲ ዲን ተወካይ ዶ/ር የኑስ በበኩላቸው መምህር ስንታየሁ ገብሩ ድንግሌን መጽሀፍ ጽፎ በማሳተሙ ፋካልቲአችን አርአያነት ያለውና የሚያኮራ ስራ መሆኑን እውቅና ይሰጣል ብለዋል፡፡ በዚህም የተቀዛቀዘውን የልብወለድ መጽሃፍ ህትመት እንደሚያነቃቃ ያላቸውን እምነት ተናግረዋል፡፡

ጋዜጠኛ የሺ ሀሳብ አበራ የድንግሌን መጽሃፍ ይዘት ዳሰሳ በወፍ በረር ለታዳሚው ያቀረበ ሲሆን መጽሀፉ አገር በቀል እውቀትና ማንነት ላይ መሰረት አድርጎ የተጻፈና ሁሉንም የአገሪቱ ክፍሎች ያማከለ እይታን የያዘ ነው ተብለዋል፡፡

በመጽሀፍ ምረቃ ፕሮግራሙ ላይ አርቲስት ስለሺ ደምሴና ደራሲና ጋዜጠኛ ዘነበ ወላ የተገኙ ሲሆን በመጽሃፉ ላይ ያላቸውን አስተያየትና የህይወት ልምዳቸውን ለታዳሚው አካፍለዋል፡፡

 

 

 

በድንግሌን ልቦለድ መፅሐፍ ጉዞና ፍለጋን መሰረት ያደረገ ሃይማኖትን፤ እሴትን፣ ተስፋን፣ ፅናትን፣ ማንነትን እና ኢትዮጵያዊነትን አጉልቶ የሚያሳይ የስነ-ፁሁፍ ስራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች፤ መምህራን፣ ተማሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ- ባዳዩ-BDU

💦💦💦💧💦💦💧💦💦💦

ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ

Wisdom at the source of Blue Nile

🔎🔎🔎🔎🔎🔎🔎🔎🔎🔎🔎🔎

Thank you for Inviting, like, share & visiting BDU page!

ለተጨማሪመረጃዎች፡-

Telegram ፡- t.me/BDU_ISC_Official

Facebook: - https://www.facebook.com/bduethiopia

YouTube ፡- www.youtube.com/c/BduEduEt

LinkedIn ፡- www.linkedin.com/school/bahir-dar-university

Twitter: - https://twitter.com/bdueduet

Tiktok:-https://vm.tiktok.com/ZMLgRxdfL

website :- www.bdu.edu.et