የፈጠራ ስራ ውጤቶች ዓውደ ርዕይ

የተለያዩ የፈጠራ ስራ ውጤቶች የታዩበት ዓውደ ርዕይ ተካሄደ

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር የተሻለ የፈጠራ ስራ ያስመዘገቡ ስራ ፈጣሪዎች የተሳተፉበት ለሶስት ተከታታይ ቀናት የቆየ ዓውደ ርዕይ  በባሕር ዳር የወጣቶች ሳይንስ ካፌ አካሄደ፡፡

በዓውደ ርዕዩ ላይ የተሳተፉት በባሕር ዳር ከተማ የሚገኙ የተሻለ የፈጠራ ውጤት ያስመዘገቡ ትምህርት ቤቶችና ከተለያዩ ቦታ የመጡ ተሳታፊዎች ስራቸውን ያቀረቡ ሲሆን የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስቴም ሴንተር፣ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና ኢንተርፕርነር ዴቨሎፕመንት ተጠቃሽ ሲሆኑ ዩኒቨርሲቲው ሌሎችን በማስተባበር አውደ ርዕዩ እንዲካሄድ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል፡፡

የአብክመ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ሳሌ አያሌው ያደጉት አገራት ለሳይንስና ቴክኖሎጂ ትኩረት በመስጠታቸው ለእድገት በር ከፋች እንደሆነላቸው አውስተው በእኛ አገር ባለው ተጨባጭ ሁኔታ ሳይንስና ተክኖሎጂ ሊሰጠው የሚገባው ትኩረት ተነፍጎት እንደቆየና አሁን ላይ የቀጣይ የትኩረት አቅጫ ሆኖ ይሰራበት ዘንድ የአውደ ርዕዩ መካሄዱ የፈጠራ ስራዎችን ለማስተዋወቅ አንድ ርምጃ የሚያስኬድ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ኮሚሽነሩ በማስከተል የፈጠራ ውጤት ባለቤቶች እንዲበረታቱና ወደ ማምረት ገብተው የኩባንያ ባለቤት የሚሆኑበት መንገድ ቢመቻች በውጭ ምንዛሬ ወደ አገራችን የሚገባውን ለማስቀረትና ወደ ውጭ በመላክ የአገሪቷን ኢኮኖሚ ማሳደግ እንደሚቻል አስገንዝበው ይህ ተግባር እውን የሚሆነው በመንግስትና በማህበረሰቡ የተቀናጀ ተሳትፎ በመሆኑ ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ርብርብ ማድረግ እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡

በሶስት ቀን ቆይታው በፖሊሲው ዙሪያ የመንግስት ከፍተኛ አመራሮችና የፈጠራ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ውይይቶች የተካሄዱ ሲሆን በፈጠራ ስራ የተሻለ ልምድ ያላቸውና ውጤታማ የሆኑ ሰዎች ልምዳቸውን ለተሳታፊዎች አቅርበዋል፡፡ አቅራቢዎችም ቁልፍ የስኬት መንገዶችን በዝርዝር ተናግረው ሁሉም ባለው አቅም በይቻላል መንፈስ ከሰራ ውጤታማ መሆን እንደሚቻል አስገንዝበዋል፡፡

ለአውደ ርዕዩ ተሳታፊዎች የምስክር ወረቀት የተሰጠ ሲሆን አጠቃላይ 25 የሚደርሱ ተሳታፊዎች የፈጠራ ውጤታቸውን በማቅረብ ስራቸው ተገምግሞ ከ1-5ኛ ለወጡት ማለትም 1ኛ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስቴም ሴንተር፣ 2ኛ SOS School፣ 3ኛ ድልችቦ ትምህርት ቤት፣ 4ኛ እሸት አካዳሚ፣ 5ኛ RISPINS INTERNATION SCHOOL ተሳታፊዎች ለእያንዳዳቸው ሁሉን ያሟላ የቴክኖሎጂ መስሪያ ቁሳቁስ (Since Kite) ተበርክቶላቸዋል፡፡ ሽልማቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በምርምሩ ዘርፍ የሚሰሩት አቶ ታደሰ አንበሴ እና የአብክመ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር አቶ መላኩ ጥላሁን አበርክተዋል፡፡

አውደ ርዕዩ የአብክመ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኮሚሽን ከ2015 ዓ.ም እቅድ መካከል አንዱ እንደሆነና ጠቀሜታውም ለተሳታፊዎች የዕርስ በዕርስ ትውውቅና የእያንዳንዱ የፈጠራ ስራ በአእምሮአዊ ንብረት እንዲመዘገብ ማገዙን አቶ መላኩ ጥላሁን ገልፀዋል፡፡ አክለውም በአሁኑ ወቅት ለአገሪቱ አስፈላጊ የትኩረት አቅጣጫ የሆነው ሳይንስና ቴክኖሎጂ ስለሆነ ዩኒቨርሲቲዎችና ኢንዱስትሪዎች ተናበው በመስራት የፈጠራ ባለቤቶችን የሚያግዝ ስራ ከስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ጀምሮ በመስራት ቴክኖሎጅውን ማስረፅ ተገቢ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

በመርሃ ግብሩ ማጠቃለያ ዶ/ር ሳሌ የኑሮ ውድነትን ለመቅረፍና የፈጠራ ባለቤቶችም ትኩረት አግኝተው በስራቸው አእምሯዊ ንብረት በማስያዝ ከባንክ የገንዘብ ብድር ተመቻችቶላቸው ስራቸውን በሰፊው እንዲያከናውኑና አምራች ድርጅት እንዲያቋቁሙ የሚያግዝ ፖሊሲ ተቀርፆ ስራ ላይ ማዋል እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ- ባዳዩ-BDU

ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ

Wisdom at the source of Blue Nile

Thank you for Inviting, like, share & visiting BDU page!

ለተጨማሪመረጃዎች፡-

Telegram ፡- t.me/BDU_ISC_Official

Facebook: - https://www.facebook.com/bduethiopia

YouTube ፡- www.youtube.com/c/BduEduEt

LinkedIn ፡- www.linkedin.com/school/bahir-dar-university

Twitter: - https://twitter.com/bdueduet

Tiktok:-https://vm.tiktok.com/ZMLgRxdfL

website :- www.bdu.edu.et