የፀረ-ሙስና ቀን ተከበረ

ለ18ኛ ጊዜ የፀረ-ሙስና ቀን ተከበረ

 (ህዳር 26/2015 ዓ.ም፣ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ-BDU) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ19ኛ ጊዜ በአገር አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ18ኛ ጊዜ የተከበረውን የፀረ-ሙስና ቀን በዩኒቨርሲቲው የመሰብሰቢያ አዳራሽ "ሙስናን መታገል በተግባር!" በሚል መሪ ቃል አከበረ፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ጉዳዮች ም/ፕሬዘዳንት አቶ ብርሃኑ ገድፍ ሁሉም ማህበረሰብ ሙስናን መፀየፍ እንደሚገባውና ከሙስና የፀዱ እጆች በየእምነታችን እንደሚያስፈልግ በአንክሮ ገልፀዋል፡፡

አቶ ብርሃኑ በማስከተል በሙስና ወንጀል የተሰማራ ሰው ሌሎች ንፁኃንን ሲያሳድድና ከተቋሙ ይልቅ የግሉን ገፅታ ለመገንባት ከፍተኛ ጥረት ስለሚያደርግ በዚያ ግርግር  ለእውነት የቆሙ ሰዎች ሳይሸማቀቁ በተገቢው ሰዓት ተገቢውን መረጃ ለሚመለከተው አካል በማሳወቅ የሙስና ወንጀልን መከላከል እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

አቶ ብርሃኑ አክለውም በሙስና ወንጀል የተሰማራ ማንኛውም ሰው በእምነቱም ሆነ በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ስለሌለው የሚያከናውናቸው ተግባራት ሁሉ ውጤታማ እንደማይሆኑ በግልፅ የታወቀ ስለሆነ በንጽህና ሰርተን ተቋማችንን ማሳደግ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው የስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኢ/ር አለማየሁ ተፈራ ባቀረቡት የውይይት መነሻ ፅሁፍ "ሙስናን መታገል በተግባር!" መሆኑን የሚያመላክቱ በርካታ ሃሳቦችን ዳሰዋል፡፡

የሙስና ወንጀል ከሌሎች የተለየ የሚያደርገው በረቀቀ ስልት የሚፈፀምና የወንጀሉን ባለቤት ለማወቅ ረጅም ጉዞን የሚጠይቅ ብሎም ተዋናዮች ወንጀሉን እንደ ነውር የማይቆጥሩ በመሆኑ ለማህበረሰቡ ዋነኛ የእሮሮ ምንጭ መሆኑን ከፅሁፉ መረዳት ተችሏል፡፡

በመድረኩ ላይ ተገኝተው የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ማኔጅግ ዳይሬክተር ኮማንደር ፈንታሁን አየለ በንግግራቸው ሙስና እንዲጎለብት ከሚያደርጉት ነገሮች አንዱና ዋናው የስራ ኃላፊዎች ቁርጠኝነት መላላት ሊሆን ስለሚችል ሁሉም ተረባርቦ ሙስናን መዋጋት እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

ኮማንደሩ አክለውም የሙስናን ወንጀል ለመከላከል የፀረ ሙስና ባለሙያ ወንጀሉን ሲያጋልጥ የተቋማት ኃላፊዎች በጥላቻ ዓይን የማየት ልምድ በማስወገድ ንፁህ ህሊና ይዘን ያለምንም እንከን ማንነታችንን ብቻ ለትውልድ ማስተላለፍ ተገቢ መሆኑን አንስተዋል፡፡

``ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ``

``Wisdom at the source of Blue Nile

Thank you for visiting and inviting our Pages!

Thank you for your likes, comments and shares!

ለተጨማሪ መረጃዎች፡-

Facebook፡ https://www.facebook.com/bduethiopia

YouTube፡ https://www.youtube.com/@bduethiopia

Instagram፡www.instagram.com/bduethiopia

TikTok፡ https://www.tiktok.com/@bduethiopia

Telegram፡ https://t.me/bduethiopia

Twitter፡ https://twitter.com/bduethiopia

LinkedIn፡http://www.linkedin.com/school/bduethiopia

Website https://bdu.edu.et/

#BDU60th_ANNIVERSARY