የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ

የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ የ2014 በጀት ዓመት የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ አካሄደ

(ሀምሌ 14/2014 ዓ.ም፣ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ BDU) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ የአስተዳደር ዘርፉን የ2014 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በኮሌጁ ግቢ አካሄደ፡፡

የግብርናና አካባቢ ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር አሳምነው ጣሰው እንደገለጹት ባሳለፍነው በጀት ዓመት ብዙውን ጊዜ አገሪቱ በገጠማት የህልውና ዘመቻ ምክንያት ከመማር ማስተማሩ ውጭ በሆነ የዘመቻ ስራ ተጠምደው መቆየታቸውን ገልፀዋል፡፡

ዶ/ር አሳምነው በማስከተል ከጦርነቱ መልስ ዘርፈ ብዙ ተግባራት መከናዎናቸውንና ኮሌጁ የዩኒቨርሲቲውን ራዕይ ለማሳካት ስራዎችን በጥራትና በፍጥነት እየተገበረ የሚገኝ ጠንካራ ተቋም መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ጉዳዮች ም/ፕሬዚዳንት አቶ ብርሃኑ ገድፍ በበኩላቸው መርሃ ግብሩን ላዘጋጁና ኮሌጁ እዚህ ደረጃ እንዲደርስ ጉልህ አስተዋፅኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበው ዩኒቨርሲቲው ከ5,500 በላይ የአስተዳደር ሰራተኞች ያሉትና ከመማር ማስተማሩ ጎን ለጎን በርካታ አኩሪ ተግባራትን የሚያከናውን ግዙፍ ተቋም መሆኑን ተናግረዋል፡፡ 

አቶ ብርሃኑ በማስከተል ሁሉም ሰራተኛ ጠንክሮ መስራት እንዳለበትና ለወደፊት ለሚመጡ የስራ ፉክክርና ውድድር በቅቶ ለመገኘት የትምህርት ወረቀት ወይም እውቀት ብቻ ሳይሆን በስራ ኮከብ ተሸላሚ ለመሆን ታታሪና ምስጉን ሰራተኛ ሆኖ መገኘት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

የበጀት አመቱን የእቅድ አፈፃፀም ዋና ዋና ተግባራት በዝርዝር ያቀረቡት የግቢው ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ታደሰ መኳንንት ሲሆኑ በአስተዳደር ዘርፉ ያሉት ተግባራትም ሆነ በመማር ማስተማሩ በኩል ምቹና ሳቢ የመማሪያ ክፍሎችን ማዘጋጀት እንደተቻለ፣ በግዥ በኩልም ከተለያዩ ክፍሎች ለሚጠየቁ ፍላጎቶች የግዥ ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ መተግበራቸውን እንዲሁም ግቢው በአረንጓዴ ተሸፍኖ ውብ፣ማራኪና ፅዱ እንዲሆን በርካታ ስራዎች መከናዎናቸውን ከቀረበው ሪፖርት ለመረዳት ተችሏል፡፡ የምድረ ግቢ ውበት ከየት ወዴት እንደተቀየረ የበፊቱንና የአሁኑን በማነጻጸር አርአያነት ያለው ስራ መሰራቱን አቶ ታደሰ በሪፖርታቸው አቅርበዋል፡፡

በሪፖርቱ ላይ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችም የተለዩ ሲሆን ጎልተው የወጡት የመጠጥ ውሃ እጥረትና የመብራት መቆራረጥ መሆናቸው ተገልፆ በቀረበው ሪፖርት ላይ ተሳታፊዎች አስተያየት እንዲሰጡ ተደርጎ ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቷል፡፡

በመርሃ ግብሩ ላይ ኮሌጁ አሁን ካለበት ደረጃ እንዲደርስ ጉልህ አስተዋፅዖ ላበረከቱ አካላት የቀድሞ የኮሌጁ ዲን የነበሩትን ዶ/ር በላይነህ አየለን ጨምሮ ስራቸውን በትጋት ለተወጡ የክፍል ኃላፊዎች፣የስራ ፈፃሚዎች፣ሹፌሮችና የቀን ሰራተኞች የእውቅናና ሽልማት ስነ ስርዓት ተካሂዷል፡፡

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ-ባዳዩ-BDU

ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ

Wisdom at the source of Blue Nile

Description: 🔎Description: 🔎Description: 🔎Description: 🔎Description: 🔎Description: 🔎Description: 🔎Description: 🔎Description: 🔎Description: 🔎Description: 🔎Description: 🔎

Thank you for Inviting, like, share & visiting BDU page!

ለተጨማሪ መረጃዎች፡-

Telegram ፡- t.me/BDU_ISC_Official

Facebook: - https://www.facebook.com/bduethiopia

YouTube ፡- www.youtube.com/c/BduEduEt

LinkedIn ፡- www.linkedin.com/school/bahir-dar-university

Twitter: - https://twitter.com/bdueduet

Tiktok:- https://vm.tiktok.com/ZMLgRxdfL

website :- www.bdu.edu.et

#BDU60th_ANNIVERSARY