የዶ/ር አበባ ብርሐኔን ሕዝበ-ገለፃ ይታደሙ

የዶ/ር አበባ ብርሐኔን ሕዝበ-ገለፃ ይታደሙ። እንዳያመልጥዎ!

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፍሬ ስለሆነችውና በስራዎቿ  ዓለም-አቀፍ ታዋቂነትን ስላገኘችው ዶ/ር አበባ BBC News አማርኛ በሰኔ 2014ዓ.ም የሚከተለውን አስነብቦ ነበር።

****

80 ሚሊዮን ምሥሎችን ያሰረዘችው ኢትዮጵያዊቷ ኮግኒቲቭ ሳይንቲስት ዶ/ር አበባ ብርሃኔ

 

የክፍሏ ጎበዝ ተማሪ ነበረች።

 

ሰኔ ላይ ሰርተፍኬት ለመቀበል ቀድመው ከሚሰለፉ መካከል ናት።

 

ዛሬ በዓለም ገናና ስም ካላቸው ኮምፒውተር ሳይንቲስቶች አንዷ የሆነችው አበባ ብርሃኔ (ዶ/ር)፣ ያኔ ሰርተፍኬት የምትወስደው አባቷ እሽኮኮ ብለዋት ነበር።

 

ውጤቷ ሁሌም ያኮራቸዋል። በየትምህርት ዘመኑ መጨረሻ እሽኮኮ ብለዋት አብረዋት ሰርተፍኬት ይቀበላሉ። ከዚያ ደስታ ከረሜላ ይገዛላታል።

". . . ደስታ ከረሜላ ገዝቶልኝ ጠጅ ቤት ይወስደኝ ነበር። ከዚያ ለጓደኞቹ በኩራት ያሳየኛል። ይህ ደስ የሚለኝ ትውስታዬ ነው። ዛሬ የደረስኩበት ለመድረሴ አባቴ ትልቅ ሚና አለው። ፀጉሬን ሁሉ የሚሠራኝ እሱ ነበር. . ."

 

አባቷ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ዘጠኝ ዓመቷ ላይ ነው። በሕይወት ሳሉ ለትምህርት ፍቅር እንድታሳድር አበረታተዋታል።

 

ነዋሪነቷን በአየርላንድ፣ ደብሊን ያደረገችው አበባ፣ በቅርቡ መነጋገሪያ ያደረጋት የማሳቹሴትስ ኢንስቲቲዩት ኦፍ ቴክኖሎጂ (ኤምአይቲ) 80 ሚሊዮን ምሥሎችን እንዲያጠፋ ያደረገውና የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃንን ዘገባ የተቆጣጠረው ጥናቷ ነው።

 

ለቤተሰቧ ብቸኛ ሴት ልጅ ናት።

 

እናቷ "ሴት ልጅ ወደ ማጀት" ይሏት ነበር። የሴትን መማር እምብዛም በማይደግፍ ቤተሰብ ውስጥ ማደግ ለትምህርት ትኩረት መስጠትን ከባድ ቢያደርገውም ትምህርት ትወድ እንደነበር ትናገራለች።

 

እዚህ ጋር መምህሮቿን ሳታመሰግን አታልፍም።

በተለይ የዘጠነኛ ክፍል ፊዚክስ አስተማሪዋን።

ለሳምንታት ትምህርት ለማቋረጥ ስትገደድ ወደ ትምህርት ቤት የመለሷት እሳቸው ናቸው። ከዚያ በኋላም በተደጋጋሚ ትምህርት አቋርጣ ተመልሳለች።

 

መንገዱ ቀላል ባይሆንም ለትምህርት ያላት ፍቅር እንዳበረታት ትናገራለች።

 

ባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ ስትገባ ፊዚክስ አጠናች። ስትመረቅ አየርላንድ ነጻ የትምህርት ዕድል አገኘች።

ዓለም አሉኝ ከምትላቸው የኢትዮጵያ የዘር ሐረግ ያላቸው ኮምፒውተር ሳይንቲስቶች መካከል አንዷ ናት። ትምኒት ገብሩ፣ ረድኤት አበበ እና አበባ ብርሃኔ።

 

አበባ የኮግኒቲቭ ሳይንስ ምሁር ናት። የቋንቋ፣ የሥነ ልቦና፣ የፍልስፍና፣ የኮምፒውተር ሳይንስ፣ የአንትሮፖሎጂ (ሥነ ሰብ) እና የአርቴፍሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሠራሽ ልኅቀት) ጥምር ጥናት ነው።

 

የክፍሏ ጎበዝ ተማሪ ሳለች ጠጅ ቤት እሽኮኮ ተብላ የምትወሰደው ዶ/ር አበባ ዛሬም የትምህርት ሰው ናት።

 

". . . ብዙ ሕይወቴን በትምህርት ውስጥ ነኝ። አሁን የምሠራው በጣም የምወደውን ነገር ነው። ፍትሕ ማስፈን፣ ጥሩ መስሎ ከውስጡ ግን ችግር ያለውን ነገር ማጋለጥ ነው በፍቅር እንድሠራ የሚገፋኝ. . ."

 

በኮግኒቲቭ ሳይንስ እና አርቴፍሻል ኢንተለጀንስ [ኤአይ] አማካይ ላይ ታተኩራለች። ሥራዋ አእምሮን፣ አካባቢን፣ ማኅበረሰብን፣ ባህልን፣ ታሪክን መረዳት፣ ከዚያም ፈትሾ መተቸትን ያካትታል።

 

ከኤአይ ቅጥያዎች አንዱ ማሽን ለርኒንግ ሲሆን፣ ሰው ሠራሽ ማሽን መረጃ (ዳታ) ተመግቦ በተሻለ ቅልጥፍናና ትክክለኛነት ክንውን እንዲፈጽም የሚያስችል ዘመነኛ ቴክኖሎጂ ነው።

 

አበባ ለማሽን የሚቀርበውን መረጃ ትመረምራለች። ከሥነ ምግባር አንጻርም ትተቻለች። የዶክትሬት መመረቂያ ጽሑፏን እንደ ማሳያ እንውሰድ።

ትክክለኛ ነው ብለን መገመት የለብንም።"

ነገሩን ወደ ኢትዮጵያ አውድ እንውሰደው።

 

ሰልፊ መለጠፍ እናቁም?

 

አበባ በኢትዮጵያ በዋነኛነት የሚያሰጋት የግል መረጃ አጠባበቅ ግንዛቤ አለመኖሩ ነው።

". . . ምሳሌ ልስጥሽ፣ የማትሪክ ውጤት ሲወጣ ሰው ውጤቱን፣ መታወቂያ ቁጥሩንና ሌላም የግል መረጃውን በዘፈቀደ በበይነ መረብ እየለጠፈ ነበር። ይህ የግል መረጃ ሲለቀቅ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ተቋሞች ሀርቨስት (ይሰበስቡታል) ያደርጉታል። ከዚያም ሰዎችን ለማግለልና ለመጉዳት ይውላል። በበይነ መረብ የምንለቀው መረጃ አንዴ ከተለቀቀ በኋላ እንደማይጠፋና እየተንሳፈፈ እንደሚቆይ ማወቅ አለብን. . ."

ሌላው ጥንቃቄ ልንወስድበት የሚገባው ነገር የራስን ምሥል (ሰልፊ) በዘፈቀደ መለጠፍ ነው።

ብዙ ኢትዮጵያዊ ምን ችግር አለው? ብሎ ሰልፊ እንዳሻው ይለጥፋል። ሆኖም ምሥሉ ወደ መረጃ ቋት (ዳታቤዝ) እንደሚገባ፣ ከዚያም ማሽን ለማሠልጠን እንደሚውል መታወቅ አለበት።

አሁን ላይ ለታክሲ፣ ለባንክ ወይም ምግብ ለማዘዝም መተግበሪያ እየተጠቀምን እንገኛለን።

የግል መረጃችንን በስፋት በበይነ መረብ ስንለቅ ይህ መረጃ ይከማችና ኋላ ላይ አገልግሎት ስናገኝ የመድልዎ ሰለባ እንድንሆን ይጋብዛል።

"ወደድንም ጠላንም የሰዎችን ታሪክ፣ የገንዘብ ልውውጥ፣ ብሔር እና ሌላም የግል መረጃ በመጠቀም ብድር እንስጣቸው ወይስ አንስጣቸው? የሚለው እየተወሰነ ያለበት ዓለም ነው። ኢትዮጵያውያንም ወደዚያው መንገድ እየሄድን ነው።"

 

ብዙ ጥቁር ሴቶች በሙያው አይታዩም።

". . . ወደ 1950ዎቹ ስንሄድ ከኮምፒውተር በፊት የሒሳብ ስሌት የሚሠሩት ጥቁር ሴቶች ናቸው። ሙያው በጣም እያደገ ሲመጣ ግን ነጭ ወንዶች ወደ ላይ ወጡ። ከዚያ ለጥቁር ሴቶች ለመግባት ፈታኝ አደረጉት። ደስ የሚለው ግን አሁን ባለንበት ዘመን በጣም ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረጉ ያሉት የሐበሻ ሴቶች መሆናቸው ነው።"

 

አበባ ይህንን የምትለው ያለ ምክንያት አይደለም። በሙያዋ ከምትኮራባቸው ቅጽበቶች አንዱ እሷ ትምኒት ገብሩ እና ረድኤት አበበ የተገናኙበትን መድረክ ነው።

 

አምና ኒውፒርስ በተባለ የውይይት መድረክ ላይ ሦስቱም ንግግር እንዲያደርጉ ተጋብዘዋል።

"ጥሩ የትብብር መስመር ዘርግተናል። እንረዳዳለን፣ አብረን እንሠራለን። አለበለዚያማ ዘርፉ ለጥቁር ሴት ፈታኝ ነው። ፒኤችዲ ለመሥራት ከነጭ ወንድ በላይ ያንቺ ፈተና ይበዛል። ይህን ሁሉ አልፈን እዚህ መድረሳችን ያኮራል።"

ዓለም አሉኝ ከምትላቸው ባለሙያዎች አንዷ የሆነችው ዶ/ር አበባ

አምና በኤአይ እጅግ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ አንዷ ተብላ ተመርጣለች።

 

በኮምፒውተር ቪዥን ፈጠራ ቬንቸር የተባለው ሽልማት ተሰጥቷታል።

በሆል ኦፍ ፌም፣ በ100 ብሩህ የኤአይ ባለሙያ ሴቶች ዝርዝር ውስጥ ገብታለች።

በኤአይ ዘርፍ በአፍሪካ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ 80 ባለሙያዎች አንዷ ናት።

ከሽልማቶቿ ዋና ዋናውን ጠቀስን እንጂ ያገኘቻቸው ዕውቅናዎች እነዚህ ብቻ አይደሉም።

ለእሷ ግን ትልቅ ዋጋ ያለው ቅጽበት የፒኤችዲ መመረቂያ ጽሑፏን አቅርባ ያጠናቀቀችበት ነው።

". . . ገና ትልልቅ ሕልሞች አሉኝ። ግን ፒኤችዲዬን ዲፌንድ አድርጌ ከቫይቫ ስወጣ የነበረውን ቅጽበት አልረሳውም። ከ5 ዓመታት ሥራ በኋላ የደረስኩበት ስለሆነ ትልቁ ከፍታዬ ነው።"

ጽሑፏን አቅርባ ስትወጣ የተነሳው ፎቶ ትዊተር ላይ ከተለቀቀ በኋላ የእንኳን ደስ አለሽ መልዕክት ጎርፎላታል።

 

Manu, [27/11/2022 01:14]

የሙያ አጋሮቿ ትምኒት እና ረድኤት ያሉበት ብላክ ኢን ኤአይ ተቋም፣ ጥቁር ሴቶች በዘርፉ እንዲተሳሰሩ፣ እንዲተባበሩ መንገድ ከፍቷል።

ከጥናቶቻቸው አንዱ በአፍሪካውያን የኤአይ ባለሙያዎች የሚሠሩ ምርምሮች እንዴት ተደራሽ ይሁኑ? የሚለው ነው።

 

ስለ ሕብረተሰብ ጤና እና ስለ መድኃኒት የሚሠሩ የአፍሪካውያን ጥናቶች ሳይታተሙ ይቀራሉ። ሲታተሙም ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዕውቅና አይሰጣቸውም።

 

አበባ ቀጣይ ዕቅዷ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ እየተቋቋመ ያለውን የኮግኒቲቭ ሳይንስ ክፍል

 መደገፍ እንደሆነ ትናገራለች። አንድ ሁለቴም በዩኒቨርስቲው ግብዣ ሌክቸር ሰጥታለች።

". . . አሁን ጥናቴ በሌሎች አገሮች ተሞክሮ ላይ የተመረኮዘ ቢሆንም፣ ዞሬ ዞሬ ግቤ ወደ ማኅበረሰቤ ተመልሼ ለእኛ መሠረታዊ የሆኑ ነገሮችን መፈተሽና አስተዋጽኦ ማበርከት ነው. . ."