የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ስልጠና እየሰጠ ነው

የእግር ኳስ ፌዴሬሽን ከክልሎች ለተውጣጡ ሰልጣኞች በፕሮጀክት አቅፎ ስልጠና እየሰጠ ነው

(ሀምሌ 15/2014 ዓ.ም፣ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ-BDU) የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከሁሉም ክልሎች ለተውጣጡ ከ15 ዓመት በታች እድሜ ያላቸው በድምሩ 30 ሰልጣኞችን በፓይለት ፕሮጀክት አቅፎ ስልጠና ሰጥቷል፡፡

በአማራ ክልል ባሕር ዳር ከተማ አንድ የወንድ እና ወልዲያ ከተማ አንድ የሴት ሰልጣኞች የፕሮጀክቱ አካል ሲሆኑ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚም ታዳጊ ወጣቶችን አቅፎ አሰልጣኝ በመመደብ ሳይንሳዊ ስልጠና በመምህራን እየሰጠ መሆኑን የስፖርት አካዳሚው ዲን ዶ/ር ዳኛቸዉ ንግሩ ተናግረዋል፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚ ለአገራችን የእግር ኳስ እድገት እያደረገ ያለውን ጉልህ አስተዋጽኦ በመገምገም የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የአካዳሚውን ከ15ዓመት በታች ተስፋ ለኢትዮጵያ ታዳጊ የእግር ኳስ ፕሮጀክት አርባ ምንጭ ከተማ ከሀምሌ 17 እስከ ነሐሴ 01/2014 ዓ.ም ድረስ በሚያካሄደው ውድድር ላይ እንዲሳተፉ እድል ተሰጥቷል ብለዋል ዶ/ር ዳኛቸዉ ንግሩ፡፡

ዶ/ር ዳኛቸዉ አክለውም የውድድሩ አላማ አቅም ያላቸው ተወዳዳሪዎችን መልምሎ ካፍ አካዳሚ በማስገባት ለ10 አመታት ስልጠናና ሁሉን አቀፍ ትምህርት በመስጠት ብሄራዊ ቡድኑን ሊተኩ የሚችሉ ታዳጊዎችን በማይነጥፍ መንገድ ማፍራት ሲሆን የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስፖርት አካዳሚም የዚህ እድል ተጠቃሚ በመሆኑ ለ3 ተከታታይ አመታት ስናሰለጥናቸው የቆዩትን ታዳጊ የእግር ኳስ ፕሮጀክት ሰልጣኞችን በውድድሩ እንዲሳተፉ በማድረግ ከሌሎች ፕሮጀክቶች የተሻለ ውጤት በማስመዝገብ በብዛት ተመርጠው ወደ ካፍ አካዳሚ እንደሚገቡ ትልቅ እምነት አለን ብለዋል፡፡

ለሁሉም ተወዳዳሪዎች አዲስ ታኬታ፣ መለያዎችን እና ካሳቶኒዎችን ሰጥተን በድል እንዲመለሱ ዛሬ ጠዋት በክብር ሸኝተናቸዋል፡፡ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብም ድጋፍ እንዲያደርግላቸው ስፖርት አካዳሚው ጥሪዉን ያስተላለፈ ሲሆን በውድድሩ እንዲሳተፉ ላደረጉ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት እና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ከልብ እናመሰግናቸዋለን ብለዋል ዶ/ር ዳኛቸዉ፡፡

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ-ባዳዩ-BDU

ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ

Wisdom at the source of Blue Nile

Thank YOU for visiting and inviting our pages, for your likes and shares!

ለተጨማሪ መረጃዎች፡-

Telegram ፡- t.me/BDU_ISC_Official

Facebook: - https://www.facebook.com/bduethiopia

YouTube ፡- www.youtube.com/c/BduEduEt

LinkedIn ፡- www.linkedin.com/school/bahir-dar-university

Twitter: - https://twitter.com/bdueduet

Tiktok:- https://vm.tiktok.com/ZMLgRxdfL

website :- www.bdu.edu.et