የነጭ ሪባን እና ኤች.አይ.ቪ ኤድስ ቀን

የነጭ ሪባን እና ኤች.አይ.ቪ ኤድስ ቀን ተከበረ

(ታህሳስ 01/2015 ዓ.ም) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ዳይሬክትሬት ከኢትዮጵያ ቤተሰብ መምሪያ ማህበር ጋር በመተባበር ዓለም አቀፍ የነጭ ሪባን ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ31ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ17ኛ ጊዜ “ሴትን አከብራለሁ ጥቃቷንም እከላከላለሁ” በሚል መሪ ቃል እና የኤች አይ ቪ/ ኤድስ ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ35ኛ ጊዜ በሀገራችን ደግሞ ለ34ኛ ጊዜ “ፍትሃዊና ተደራሽ የኤች አይ ቪ/ኤድስ አገልግሎት” በሚል መሪ ቃል ተጋባዥ እንግዶች እና ተማሪዎች በተገኙበት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ግሽ አባይ ግቢ ተከበረ፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ዘርፈ ብዙ ጉዳዮች ተቀዳሚ ዳይሬክተር ዶ/ር ሙሉጎጃም ወንድይፍራው እንደገለጹት በዓሉ በሀገራችን ከህዳር 16 እስከ ታህሳስ 01 የሚከበር ሰሆን ዓላማውም በሴቶች ላይ የሚደረግ ፆታን መሰረት ያደረገ ማንኛውም  አካላዊም ሆነ ስነ-ልቦናዊ  ጥቃትን በመቃወም የሚከበር ነው ብለዋል፡፡ አክለውም በዚህ በዓል በዋናነት ወንዶች በሴቶች ላይ ጥቃት ላለማድረስ እና ጥቃት ቢደርስባቸው ሊከላከሉላቸውና አጋርነታቸውን የሚያሳዩበት ነባራዊ ሁኔታ እንዲፈጠር ማድረግ መስራ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሴቶች ሕጻናት እና ወጣቶች ዳይሬክተር ወ/ሮ ብርሃኔ መንግስቴ የነጭ ሪባን ተምሳሌትነቱ በወንዶች አጋርነት፤ ወንዶች በሴቶች ላይ የሚፈጽሙትን ጥቃት ማስቆም የሚለውን የያዘ ነው፡፡ ሴቶች እና ልጃገረዶች ከጥቃት ሰለባ ነጻ የሆነ ዓለም ውስጥ መኖር እንዲችሉ የተስፋ ተምሳሌት እንዲሆን እንዲሁም በወንዶች አጋርነትና ተሳትፎ ጥቃት ተቀባይነት እንዳይኖር መታገል፣ ዝምታው እንዲሰበር ሴቶችን ማበረታታትና በሁሉም ትብብር ለሁሉም የሰው ልጆች የተሻለ ዓለምን መፍጠር መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያ እና መቆጣጠሪያ ዳይሬክተር ሲ/ር ምህረት ጌታቸው ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እንደ ሀገር በርካታ ወገኖችን ለህልፈት እንደዳረገ እና ሁለንተናዊ ቀውስ እንዳስከተለ ይታወሳል፡፡ በመንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች በተደረገው ርብርብ ጥፋቱን መቀነስ ቢቻልም በአሁኑ ሰአት ግን እንደገና በማገርሸት ላይ ይገኛል፡፡ አብዛኞቹ የኤች.አይ.ቪ ተጠቂዎች 85 በመቶ ጥንቃቄ በጎደለው ግብረ ስጋ ግንኙነት የሚተላለፍ እንደሆነና በወንዶች እና በሴቶች ስነ-ተዋልዶ ጤና ላይም እጅግ በጣም ብዙ ተጽኖዎች እንዳሉት ገልጸዋል፡፡ ሲ/ር ምህረት አክለውም ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ፆታን፣ እድሜን፣ ዘርን፣ ቀለምን እና ቋንቋን ሳይለይ ሁሉንም ማህበረሰብ የሚጎዳ ስለሆነ ለቫይረሱ አጋላጭ ከሆኑ እንደ አልኮል፣ አደንዛዥ ዕጽ ከመሳሰሉት በመራቅ የወጣትነት እድሜያችንን በማስተዋል መምራት አለብን ብለዋል፡፡

በአሉን በማስመልከት ደም ልገሳ የተካሄደ ሲሆን በአሉን በተመለከተ እያዝናኑ የሚያስተምሩ የተለያዩ ኪነጥበባዊ ስራዎችም ቀርበዋል፡፡

``ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ``

``Wisdom at the source of Blue Nile

Thank you for visiting and inviting our Pages!

Thank you for your likes, comments and shares!

ለተጨማሪ መረጃዎች፡-

Facebook፡ https://www.facebook.com/bduethiopia

YouTube፡ https://www.youtube.com/@bduethiopia

Instagram፡www.instagram.com/bduethiopia

TikTok፡ https://www.tiktok.com/@bduethiopia

Telegram፡ https://t.me/bduethiopia

Twitter፡ https://twitter.com/bduethiopia

LinkedIn፡http://www.linkedin.com/school/bduethiopia

Website https://bdu.edu.et/

#BDU60th_ANNIVERSARY