የትምህርት እና ስነ ባህሪ ኮሌጅ አመታዊ አለም አቀፍ ጉባኤ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ትምህርት እና ስነ ባህሪ ኮሌጅ አመታዊ አለም አቀፍ ጉባኤ አካሄደ

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ትምህርት እና ስነ ባህሪ ኮሌጅ 37ኛውን አለም አቀፍ ትምህርታዊ ጉባኤውን በዋናው ግቢ መሰብሰቢያ አዳራሽ እያካሄደ ነው።

በመርሃ ግብሩ ተገኝተው ለተሳታፊዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ያስተላለፉት የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ትምህርት እና ስነ ባህሪ ኮሌጅ ዲን ዶ/ር ታደሰ መለሰ የጉባኤው ዋና ጭብጥ secondary and technical vocational education and training: practices, challenges and prospectsመሆኑን ጠቁመው  ባሁኑ ስዓት ኮሌጁ 6 የመጀመሪያ ዲግሪ፣ 12 የሁለተኛ ዲግሪ  3 የPhD ፕሮግራሞች እየሰጠ እንደሆነና 4 አዳዲስ የሁለተኛ ዲግሪ  እና 3 የ PhD ፕሮግራሞችን ለመጀመር በሂደት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል ፡፡ በጉባኤውም በኢትዮጵያ ውስጥ የሁለተኛና የቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ሥልጠና  ምርመር ላይ በአንድም ሆነ በሌላ መልኩ ተሳትፎ ያላቸው ምሁራን እና ባለሙያዎች የተገኙ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ በመርሃ ግብሩ መክፈቻ ተገኝተው  እንደተናገሩት በተባበሩት መንግስታት የተሻሻለ የልማት ግብ 4 የተመዘገበው፤  የሁሉንም ማህበረሰብ ህይወት ለመለወጥ እና ዘላቂ ልማት ለማምጣት  ሁሉን አቀፍና ፍትሃዊ ጥራት ያለው ትምህርት መሰረት እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡ ማስረጃዎች ስለ ጥራት አስፈላጊነት ያለልዩነት ቢያትቱም  በኢትዮጵያ  ስርዓተ ትምህርት የመጀመሪያ ደረጃና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ጥራት እና ብቃት  ላይ ቅሬታዎች እንዳሉ የተለያዩ ጠቋሚዎች መኖራቸውን ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል ፡፡  በመሆኑም የዚህ አመቱ ትምህርታዊ ጉባኤ ጭብጥ አሳማኝ እንደሆነ ፕሬዝዳንቱ ገልፀዋል፡፡

መርሀ ግብሩ ግንቦት 9 እና 10 የቀጠለ ሲሆን 11 የሚሆኑት ጥናታዊ ጽሁፎች ከተለያዩ የሀገሪቱ ዩኒቨርሲቲዎች በመጡ ምሁራን የሚቀርቡ ሲሆን ቀሪዎቹ 11 ጥናታዊ ፅሁፎች በዩኒቨርሲቲው ምሁራን የሚቀርቡ ናቸው፡፡