የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም

ሰልጣኞች ለችግረኛ ህፃናት እና አቅመ ደካሞች የማዕድ ማጋራት ፕሮግራም አካሄዱ

*********************************************************************

(ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ፣ ህዳር 14/3/2015 ዓ.ም) የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከሰላም ሚኒስትር ጋር በመተባበር "በጎነት ለአብሮነት" በሚል መሪ ቃል ከሁሉም ክልሎች ተውጣጥተው በብሔራዊ በጎ ፈቃድ አገልግሎት ዙሪያ ስልጠና እየወሰዱ ያሉ ከ1,200 በላይ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን ወጣቶች የቁርስ ወጭአቸውን በባሕር ዳር ከተማ በተለያዩ አካባቢዎች በጎዳና ላይ ለሚገኙ ሕፃናት እና አቅመ ደካሞች እንዲውል በማድረግ የምገባ ፕሮግራም እና የአቅመ ደካሞችን ልብስ በማጠብ ከበጎ ፈቃድ አገልግሎት ስልጠናቸው ጎን ለጎን ህብረተሰቡን የሚጠቅም በጎ ተግባር እየሰሩ መሆኑ ተገለፀ፡፡   

የአምስተኛ ዙር የብሔራዊ በጎ ፈቃድ አግልግሎት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ዘውዴ ኤጄርሳ እንደገለጹት ለአምስተኛ ዙር በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ እየሰለጠኑ ያሉ 1,200 በላይ ወጣቶች ሀገራቸውን እና ሕዝባቸውን የሚወዱ የዩኒቨርሲቲ ሙሩቃን መሆናቸውን ተከትሎ በጎነትን በማህብረሰቡ ውስጥ ገብቶ የማስተማር  ተግባር  ለመፈፀም ስልጠና እየወሰዱ መሆኑን ጠቅሰዋል፡፡ ከሚወስዱት ስልጠና ጎን ለጎን የቁርስ ወጫቸውን ጎዳና ላይ የወደቁ እና በልቶ ማደር ላልቻሉ ወገኖች የምገባ ፕሮግራም ከማድረጋቸው በተጨማሪ የአረጋዊያንን ልብስ በማጠብ፣ ደም የመለገስ እና የልብስ ማሰባሰብ በጎ ስራዎችን በህብረተሰቡ ውስጥ በመግባት እየሰሩ መሆኑን አቶ ዘውዴ  ተናግረዋል፡፡  

ስልጠናው የሚመራው በሰላም ሚኒስቴር የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር እየተሰጠ መሆኑን የተናገሩት አስተባባሪው የስልጠናው ዋና ዓላማ በሁሉም የሀገራችን ክፍሎች ባሉ ዩኒቨርሲቲዎች በተለያዩ የሙያ መስኮች ተመርቀው ያለስራ የተቀመጡ ወጣቶች የበጎ ፈቃድ ስራን ለመስራት መስፈርት ወጥቶላቸው ምዝገባ አካሂደው ስልጠናውን በአምስት ዩኒቨርሲቲዎች እየወሰዱ መሆኑን አስተባባሪው ተናግረዋል፡፡ አክለውም በተለያየ ጊዜ በሀገራችን ከውስጥም ሆነ ከውጭ የህብረተሰባችን ሰላም ለማደናቀፍ ጎጥን፣ ብሔር እና ቋንቋን መሰረት አድጎ የሚከሰቱ ግጭቶችን በማክሸፍ እና ህብረተሰቡን የአንድነት ትስስር በማጠናከር ላይ ያተኮረ ዓላማ ያለው ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በመጨረሻም ከስልጠናው በኋላ ሰልጣኖች ከመጡበት አካባቢ ውጭ በሌሎች አካባቢዎች ለአስር ወር እንደሚመደቡ እና በተመረቁበት የሙያ መስክ ከሚሰጡት አገልግሎት በተጨማሪ በስልጠናው ወቅት ያገኙት እውቀት ተጠቅመው የህብረተባችን የቀደመ የሰላም፣ አብሮነት እና የመተሳሰብ እሴትን ለመገንባት የበጎ ፈቃድ ብሔራዊ አገልግሎችን በስፋት እንደሚሰጡ ተገልጿል፡፡   

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

-------------------------------------

``ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ``

``Wisdom at the source of Blue Nile``

Thank you for visiting, inviting and sharing our Pages!

Thank you for your likes and comments too!

ለተጨማሪ መረጃዎች፡-

Facebook https://www.facebook.com/bduethiopia

YouTube https://www.youtube.com/@bduethiopia

Instagram www.instagram.com/bduethiopia

TikTok https://www.tiktok.com/@bduethiopia

Telegram https://t.me/bduethiopia

Twitter https://twitter.com/bduethiopia

LinkedIn http://www.linkedin.com/school/bduethiopia

Website https://bdu.edu.et/