የማህበራዊ ሳይንስ ፋኩልቲ የ2014 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ውይይት

የማህበራዊ ሳይንስ ፋኩልቲ የ2014 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ላይ ውይይት አካሄደ
*************************************************************************
(ሰኔ 29/2014 ዓ.ም፣ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ-BDU)
የማህበራዊ ሳይንስ ፋኩልቲ የ2014ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እና የ2015 የትምህርት ዘመን ዕቅድ ላይ የማጠቃለያ ውይይት በቀድሞው የሴኔት መሰብሰቢያ አዳራሽ አካሄደ፡፡
ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የማህበራዊ ሳይንስ ፋኩልቲ ዲን ዶ/ር ታዬ ደምሴ በሪፖርታቸው ሳይታቀዱ የተከናወኑ፣ ታቅደው ያልተከናወኑ፣ ያጋጠሙ ዋና ዋና ችግሮች እና በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ለመፈፀም የተቀመጡ ዋና ዋና ተግባራትን በማቅረብ ፋኩልቲው በ6 የትምህርት ክፍሎች፣ በ12 ቅድመ ምረቃ፣ በ14 ድህረ-ምረቃና በ7 የሶስተኛ ዲግሪ በድምሩ 33 ፕሮግራሞች መኖራቸውን ገልፀዋል፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ፍሬው ተገኘ በመርሃ-ግብሩ ላይ ዩኒቨርሲቲው በማሪታይም፣ በኢንጅነሪንግ እና በቴክስታይል በውጤታማነት የተጓዘባቸውን ርቀት ለታዳሚው አስታውሰዋል፡፡ ዶ/ር ፍሬው ከመምህራን ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ አሁን ያለውን ወቅታዊ ችግርበመገንዘብ ምሁራንም ግጭቶችን ለማስቀረት የሚጠበቅባቸዉን ሚና እንዳልተወጡ እና ዩኒቨርሲቲው በሚቀጥለው አመት የሚያከብረውን 60ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እንደ መልካም አጋጣሚ የመጠቀም ክፍተት እና ወረቀቶችን በማሳተም የሚፈለገውን ያህል አለመሰራቱን በውይይቱ አንስተዋል፡፡
በመጨረሻም በመምህርነት፣ በምርምር፣ በማህበረሰብ አገልግሎት፣ በስራ መሪነት፣ በአስተዳደር ሰራተኛ የተሻለ አፈጻፀም ላስመዘገቡ የዕውቅና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ-ባዳዩ-BDU
ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ
Wisdom at the source of Blue Nile
Thank YOU for visiting and inviting our pages, for your likes and shares!
ለተጨማሪ መረጃዎች፡-
Telegram ፡- t.me/BDU_ISC_Official
website :- www.bdu.edu.et